AM/Prabhupada 0176 - ክርሽናን የምታፈቀሩ ከሆነ ክርሽና ለዘለዓለም ቅርባችሁ ሆኖ ይገኛል፡፡
Lecture on SB 1.8.45 -- Los Angeles, May 7, 1973
እኛ ብዙ ሚስጥራዊ የሆኑ ኃይሎች አሉን፡፡ ነገር ግን እነዚህ ኃይሎች በውስጣችን እንዳሉ አናውቅም፡፡ ይህም ምሳሌ ተሰጥቶናል፡፡ ለምሳሌ የወንዱ አጋዘን ከሆዱ ስር የሚገኘው የብልቱ ወገን (መስክ)ጥሩ ሽታ ሴትዋን ለመሳብ ይበትናል፡፡ እርሱ ግን ይህ ቆንጆ ሽታ ከየት መጣ ብሎ፡ ወዲህም ወዲያም ሲዘል ይገኛል፡፡ ከይት ነው ይህ ቆንጆ ሽታ የሚመጣውም ብሎ በጣም ይገረማል፡፡ ነገር ግን ይህ ቆንጆ ሽታ የሚመጣው ከሆዱ ስር እንደሆነ ሊረዳ አልቻለም፡፡ አያችሁን? ሽታው የሚመንጨው ከራሱ ነው፡ ነገር ግን ከየት ነው የሚመጣው እያለ፡ በፍለጋ ላይ ተሰማርቷል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛም ራሳችን፡ ብዙ የሚስጥራዊ ኃይሎች አሉን፡፡ ነገር ግን ሰለመኖራቸው አልተረዳንም፡፡ ነገር ግን የሚስጥራዊ ኃይሎችን የማዳበር ልምምድ ብታደርጉ፡ አንዳንዶቹን በደንብ ለማዳበር ትበቃላችሁ፡፡ ለምሳሌ ወፎች መብረር ሲችሉ እኛ ደግሞ መብረር አንችልም፡፡ አንዳንድ ግዜ የመብረብ ምኞትም ይመጣብናል፡፡ “ልክ እንደ እርግብ ክንፍ በነበረኝ” “ወደተፈለገው ወዲያውኑ ለመሄድ እበቃ ነበር”፡፡ ነገር ግን ይህም ሚስጥራዊ ኃይል በውስጣችንም ይገኛል፡፡ የሚስጥራዊ ኃይልም ዮጋ ልምምድ ብታደርጉ፡ በአየር ውስጥም ለመብረር ብቁ መሆን ትችላላችሁ፡፡ ይህ የሚቻል ልምድ ነው፡፡ “ሲድሃ ሎካ” ወይንም የሚስትራዊ ፕላኔይ የሚባልም ፕላኔት አለ፡፡ በዚህም በሲድሃ ሎካ ፕላኔት ያሉ ነዋሪያን ሁሉ፡ የሚስጥራዊ ኃይል ያላቸው ነዋሪዎች ናቸው፡፡ እኛ ወደ ጨረቃ እንኳን ለመሄድ ብዙ የመንኮራኩር ብልጽግና ያሰፈልገናል፡፡ የሲድሃ ሎካ ፓላኔት ነዋሪዎች ግን፡ ያለመንኮራኩር፡ እንደ አሻቸው፡ ወደ አየር በረው ለመሄድ ኃይል ያላቸው ናቸው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የሚስጥራዊ ኃይል በሁሉም ያለ ነው፡፡ ነገር ግን በልምድ መበልጸግ ያለበት ኃይል ነው፡፡ “ፓራሽያ ሳክቲር ቪቪድሃይቫ ስሩያቴ” (ቼቻ ማድህያ 13 65) እኛ ብዙ ያልበለጸጉ ኃይሎች አሉን፡ ነገር ግን በልምምድ ማዳበር እንችላለን፡፡ ልክ እንደ ክርሽና ንቃታችሁ፡፡ የዛሬ 4 ወይንም 5 ዓመት በፊት፡ ስለ ክርሽና ምንም የምታውቁት ነገር አለነበረም፡፡ ነገር ግን የክርሽናን ንቃት በትጋት ስለአዳበራችሁት፡ አሁን ማን አምላክ እንደሆነ፡ ምን አይነት ግኑኝነት እንደአለን ልትረዱ ችላችኋል፡፡ ይህም የሰው ልጅ ህይወት የተሰጠን፡ ይህንኑን የአምላክን ፍቅር ለማዳበር ነው እንጂ፡ ምግብ ለመፈለግ፡ መጠለያ ለመፈለግ ወይንም ለግብረ ስጋ ግንኙነት ለመራወጥ ብቻ አይደለም፡፡ እነዚህም ነገሮች ሁሉ ግዜ ያሉ ናቸው፡፡ “ታስያይቭያ ሄቶህ ፕራያቴታ ኮቪዶ ና ላብያቴ” (ሽብ 1 5 18) እንዚህ ነገሮች ከጥያቄዎቻችን ሁሉ አብይ የሆኑ አይደሉም፡፡ ምክንያቱም ሁሉግዜ ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ለወፎች እና ለአውሬዎች እንኳን በቂ የሆነ ምግብና መጠለያ አለ፡፡ ለሰው ልጅ ይቅርና፡፡ ነገር ግን የሰው ልጅ ተንኮለኛ ሁኗል፡፡ የሰው ልጅ ሃሳብ ሁሉ፡ በምግብ፡ በመጠለያ፡ በግብረ ስጋ እና በመከላከያ ጉዳዮች ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ ይህም የተሳሳተ በትክክል ያልተመራ ስልጣኔ ነው፡፡ እንዚህንም የኑሮ አሰፈላጊ ነገሮችን ለማግኘት፡ ብዙ ችግር የለውም፡፡ ውሾች እና ወፎች እንኳን ለዚህ ችግር እንደሌላቸው አንረዳም፡፡ ለምንድን ነው ታድያ የሰው ልጅ ህብረተሰብ እነዚህን ለማግኘት ብዙ ድካም የሚያደርገው? በዚህ ምድር ላይ ይህ ትልቁ ችግራችን አይደለም፡፡ አብዩ ችግራችን እንዴት ሞትን፡ እርጅናን፡ እና በሽታን እንዴት ለማቆም እንደምንችልን ማወቅን ነው፡፡ ይህም ችግር በክርሽና ንቃተ ማህበራችን ተፈትቶ እናገኘዋለን፡፡ የክርሽናን ማንነት እንኳን በትክክሉ ብንረዳ፡ “ትያክትቫ ዴሃም ፑናር ጃንማ ናይቲ” (ብጊ 4 9) ከዚህም በኋላ ወደ እዚህ አለማዊ ምድር ለመወለድ አንገደድም፡፡ ስለዚህም ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበራችን በጣም ጥሩ ነው፡፡ ከክርሽና ጋር ያለንን ጓደኝነት ብናጠናክር፡ ከክርሽና ጋር በቀጥታ ለመነጋገርም እንበቃለን፡፡ ልክ ንጉስ ዩዲስቲር ማሃራጅ እንደገለጸው፡ “ክርሽና ሆይ ለጥቂት ግዜም ቢሆን ከእኛ ጋር ቆይልን” ነገር ግን የክርሽናን ፍቅር በተገቢው ካዳበራችሁ፡ ለጥቂት ቀናት ይቅርና፡ ለዘለአለም ከእርሱ ዘንድ ለመሆን ትችላላችሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡