AM/Prabhupada 0181 - ከአብዩ የመላእክት ጌታ ጋር በቅርብ መዛመድ ይገባኛል፡፡



Evening Darsana -- August 9, 1976, Tehran

ፕራብሁፓድ:መንፈሳዊ ትምህርትን ለመከታተል:በመጀመሪያ ደረጃ:እምነት እንዲኖር ያስፈልጋል:“ከአምላክ ጋር በቅርብ መጠጋት እችላለሁ” ይህንንም አይነት እምነት ከሌለን:መንፈሳዊ ትምህርት እንወስዳለን ማለቱ ጥያቄ የለውም: እንዲያው ባላችሁበት ለመቅረት ደስተኛ ከሆናችሁ “አማላክ አብይ ነው:እርሱም አለሙ ላይ ይሁን:እኔም አለሜ ላይ ልቀመጥ የምንል ከሆነ” ይህ ፍቅር የለውም: አምላክን ለማወቅ:በጣም ጉጉት እንዲኖረን ያስፈልገናል: የሚቀጥለውም ደረጃ:አማላክን እንዴት ማወቅ ትችላላችሁ:በአማላክ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ጋር ህብረት ካልፈጠራችሁ እንዴት አምላክን ማወቅ ትችላላችሁ? እነዚህም አምላክን ከማገልገል ሌላ ስራ የላቸውም: ለምሳሌ እኛም እንደምናስተምረው:ይህም ስራችህ አምላክን ለማገልገል ነው:ሌላ አላማ የለውም: ፕላኑም እንዴት ሰዎች አምላክን እንደሚረዱ:እንዴት እንደሚጠቀሙ:እንዲህ እያደረጉም ብዙ ፕላኖች አምላክን ለማገልገል ያዘጋጃሉ: ስለዚህ እኛም ከእነዚህ አየነት ሰዎች ጋር ማህበር መፍጠር አለብን:ምክንያቱም ሰለ አምላክ እምነታቸው ከፍ ያለ እና:እውቀቱንም በአለም ለማስፋፋት እየሞከሩ ስለሆነ ነው: መቀላቀል እና ማህበር ማድረግ አለባችሁ:ተገናኟቸው: በመጀመሪያ ደረጃ ግን እምነት እንዲኖራችሁ ያስፈልጋል:“በዚህ ህይወቴ:ስለ አምላክ:በደንብ ለመረዳት እችላለሁ” ከዚያም በአምላክ ስራ በጣም ከሚሯሯጡ ሰዎች ጋር ማህበር ፍጠሩ: ከዚያም እንደነሱ ስራ መስራታችሁን ቀጥሉ: ከዚያም ሰለ አለማዊ ህይወት ያላችሁ አስተሳሰብ ያከትማል: ከዚያም ለመንፈሳዊ ኑሮ እየቀረባችሁ ትመጣላችሁ:ከዚያም ጣእሙ እየጨመረ ይመጣል: በዚህ መንገድም የአማላክን ፍቅር ማዳበር ትችላላችሁ: አሊ:እኔ እምነት አለኝ

ፕራብሁፓድ:ይህ መጨመር አለበት: የመጀመሪያው እምነት በጣም ጥሩ ነው: ግን ያ እምነት እያደገ ካልመጣ:ወደፊት መራመድ አይቻልም: ፓሪቭራጃክአቻርያ:እምነትንም የማጣት አደጋ አለ:

ፕራብሁፓድ:አዎን: ወደፊት ለመራመድ ጥረት ካላደረክ: አደጋ ይኖራል:ያለችህንም ትንሽ እምነት ታጣለህ:ሊጠፋ ይችላል: