AM/Prabhupada 0191 - ክርሽናን በቁጥጥር ማዋል፡፡ ይህ የቭርንዳቫን ሕይወት ነው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search
Go-previous.png የቀድሞው ገፅ - ቪድዮ 0188
የሚቀጥለው ገፅ - ቪዲዮ 0193 Go-next.png

Control Kṛṣṇa - That is Vrndavana Life - Prabhupāda 0191


Lecture on SB 6.1.52 -- Detroit, August 5, 1975

ፕራብሁፓድ፡ በሁለቱም በክርሽና እና በጉሩ (መንፈሳዊ አባት) በረከት የአንዱን ብቻ በረከት ለመውሰድ አትሞክሩ፡፡ "ጉሩ ክርሽና ክርፓያ ፓይ ብሀክቲ ላታ ቢጅ" በጉሩ በረከት እና ምርቃት አንድ ሰው ክርሽናን ለማግኘት ይችላል፡፡ "ክርሽና ሴይ ቶማራ ክርሽና ዲቴ ፓሮ" ጉሩን መቅረብ ማለት ክርሽናን ከእርሱ መለመን ማለት ነው፡፡ "ክርሽና ሴይ ቶማራ" ምክንያቱም ክርሽና የድቮቲዎች ወይም የአገልጋዮቹ ክርሽና ነው፡፡ ክርሽና ጌታ ነው፡፡ ነገር ግን ይህንን ጌታ ማነው ሊቆጣጠረው የሚችለው? እነዚህም አገልጋዮቹ ናቸው፡፡ ክርሽና የሁሉም የበላይ ተቆጣጣሪ ነው፡፡፡ ነገር ግን ክርሽና ራሱ በአገልጋዮቹ ቁጥጥር ነው፡፡ ይህም ክርሽና "ብሀክቲ ቫትሳላ" ሰለሆነ ነው፡፡ ልክ እንደ ታላቅ የሆነ አባት፡፡ የፍርድ ቤት የበላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰለዚህም አንድ ታሪክ አለ፡፡ አንድ ግላድ ስቶን የተባለ ጠቅላይ ሚኒስቴርን አንድ ሰው ሊጎበኘው መጥቶ ነበረ፡፡ ግላድ ስቶንም አንድ ግዜ ስራ ስለያዝኩኝ ትንሽ ጠብቅ ብሎት ነበር፡፡ እንግዳውም ለረጅም ሰዓታት በመጠበቁ ሰለሁኔታው መጠየቅ ጀመረ፡፡ "ይህ ሰው ምን እያደረገ ነው?" በማለት የሚያደርገውን ለማየት ፈለገ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴሩም ልጁን እንደፈረስ በትከሻው አድርጎ ሲያዝናናው ተገኘ፡፡ አያችሁን? ይህ አይነት ስራ ይዞት ነበረ፡፡ ይህም ፕራይም ሚኒስቴር መላ የብሪቲሽ ግዛትን የሚያስተዳድር ነበረ፡፡ ነገር ግን ይኅው ጠቅላይ ሚኒስቴር በልጁ ፍቅር ቁጥጥር ስር ውሎ ነበረ፡፡ ይህም በፍቅር መገዛት እንደሆነ ያስረዳናል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ክርሽና የሁሉም የበላይ ጌታ ነው፡፡ "ኢሽቫራ ፓራማ ክርሽና ሳክ ቺት አናንዳ ቪግራሀ አናዲር አዲር ጎቪንዳ ሳርቫ ካራና ካራናም" (ብሰ 5 1) እርሱ የሁሉም የበላይ ተቆጣጣሪ ነው፡፡ ቢሆንም ግን እርሱ በአገላጋዩ ቁጥጥር ስር የዋለ ነው፡፡ "ሽሪማቲ ራድሀራኒ“ በቁጥጥር ስር ነው፡፡ ይህም የቀድሞ ታሪክ በቀላሉ ልንረዳው ያማንችለው ነው፡፡ ክርሽና ግን በፍቃዱ በአገልጋዩቹ ፍቅር ቁጥጥር ስር ለመዋል መረጠ፡፡ ይህ የክርሽና ባህርይ ነው፡፡ ይህም ልክ እንደ እናቱ ያሾዳ ሊመሳሰል ይችላል፡፡ እናቱ ያሾዳ ክርሽናን በማሰር በቁጥጥሯ ሰር ለማድረግ ትሻለች፡፡ ”አንተ ቀበጥ ልጅ አሁንስ አስርሀለሁ፡፡“ እናቱ ያሾዳ በእጇ አርጩሜ ይዛለች፡፡ ክርሽና እያለቀሰ ይገኛል፡፡ ይህንንም ከሽሪማድ ብሀገቨታም ቅዱስ መፃህፍት ልትረዱት ትችላላችሁ፡፡ በኩንቲስ ፀሎት እንደምናየው ክርሽናን በማወደስ ላይ ትገኛለች፡፡ ”ውድ ክርሽና ሆይ አንተ የሁሉም የበላይ ነህ፡፡“ ”ነገር ግን በያሾዳ አርጩሜ ስር ሆነህ በማልቀስ ላይ ትገኛለህ፡፡ ይህንን ማየት እፈልጋለሁ፡፡“ ሰለዚህ ክርሽና ”ብሀክታ ቫትሳላ“ ተብሎ ይታወቃል፡፡ እርሱ የሁሉም የበላይ ተቆጣጣሪ ነው፡፡ ነገር ግን እንደ እናቱ ያሾዳ ወይንም እንደ አገልጋዩ ራድሀራኒ ወይንም እንደ ጎፒ አገልጋዮቹ ወይንም እንደ አገልጋይ እረኞቹ የመሳሰሉት ሁሉ ክርሽና በፍቅራቸው በቁጥጥር ስር ሊያውሉት ይችላሉ፡፡ ይህ የቭርንዳቨን ሕይወት ነው፡፡ ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ እናንተን ወደ እዚሁ ቭርንዳቫን ሊወስዳችሁ የሚሞክር ነው፡፡ ሞኞች ግን ከዚህ ዓላማ በመራቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ የዚህንም የክርሽና ንቃተ ማህበር ታላቅ አገልግሎት የተገነዘቡ ሰዎች አይደሉም፡፡ ይህም ማህበር ለሰው ልጅ ታላቅ የሆነውን ጥቅም ለመስጠት የተሰማራ ነው፡፡ የማህበሩም አገልጋዮች አላማ ከአማላክ ጋር አንድ ለመሆን ሳይሆን አማላክን በፍቅር በቁጥጥር ስር ለማዋል መብት ለመስጠት ነው፡፡ ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡