AM/Prabhupada 0193 - መላው የመንፈሳዊው ሕብረተሰባችን እነዚህን መፃህፍቶች በማዳመጥ ላይ ይገኛል፡፡
Room Conversation with Professor Durckheim German Spiritual Writer -- June 19, 1974, Germany
ዶክተር ፒ ጄ ሳኅር፡ እባክዎን ሰለ ቴክኒካችሁ ብታስረዱን የአብዩ አምላክን ሰሞች ስትዘምሩ እንዴት እንደምትዘጋጁ ምን መደረግ እንዳለበት ብትገልፁልን ጀርመንኛ ይህንንም ከመዘመር በተጨማሪ ምን መደረግ እንደአለበት እንዴት ዝግጅት እንደሚደረግ ብትገልፁልን በጠቅላላው ትምህርታችሁ እንደሚያሰተምረው?
ፕራብሁፓድ፡ አዎን ይህ የብሀክቲ ማርግ ይባላል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ሽራቫናም ወይንም ማዳመጥ ያሰፈልጋል፡፡ ለምሳሌ እነዚህ መፃህፍቶች የተጻፉት ህብረተሰቡ ለማዳመጥ እድል እንዲያገኝ ነው፡፡ ይህ የመጀመሪያው ስራ ነው፡፡ ሰለ አብዩ የመላእክት ጌታ የማናዳምጥ ከሆነ በቀላሉ ወደ ግምታዊ አስተሳሰብ እንገባለን፡፡ ሰለዚህ ስለ አምላክ ማዳመጥ ይገባናል፡፡ ወደ 80 የሚሆኑም መፃህፍቶች አትመናል፡፡ ይህም ስለ አምላክ የመስማትን ዕድል ለመስጠት ነው፡፡ በጥሞናም ካዳመጥንም በኃላ ይህንኑ ለሌሎች መግለፅ ይገባናል፡፡ ይህም “ኪርታናም” ይባላል፡፡ ሽራቫናም ኪርታናም በዚሁም ሁኔታ የመስማት እና የመዘመር ወይንም የመግለፅ ስርዓት ሲካሄድ..... ኪርታናም ማለት መግለጽ ማለት ነው። ለምሳሌ የእኛ ሕብረተሰብ ከእነዚህ መፅሀፍት በማዳመጥ እየተማረ ነው፡፡ ከዚያው እየወጡ በማስተማር ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ኪርታና ይባላል፡፡ በእዚህም ሁለት ስርዓቶች በማዳመጥ እና በመዘመር ማሰታወስ ይመጣል፡፡ ይህም ስማራናም ይባላል፡፡ ይህም ማለት በማስታወስ ሁልግዜ ከአምላክ ጋር ቅርብ ሆነን እንገኛለን፡፡ ዶክተር ፒ ጄ፡ ሰለዚህ ሁልግዜ “አስታውሰኝ”
ፕራብሁፓድ፡ አዎን አዎን “ሽራቫናም ክርታናም ቪሽኖ ስማራናም ፓዳ ሴቫናም” (ሽብ፡ 7 5 23) ከዚያም ሙርቲዎችን መስገድ የሎተስ እፅዋት ለመሰለው የጌታ እግሩም አበባ ማቅረብ የአበባ ጋርላንድ መስጠት ማልበስ፡፡ ”ፓዳ ሴቫናም አርቻናም ቫንዳናም“ ፀሎት አቅርብ በትሁት መንፈስም አገልግል፡፡ እንደዚህም የመሳሰሉ 9 ስርዓቶች አሉ፡፡ ዶክተር ፒ ጄ፡ እኛም በክርስትና እምነት እነዚህን የመሳሰሉ ስርዓቶች አሉን፡፡ ጀርመንኛ
ፕራብሁፓድ፡ አዎን የክርስቲያኑም ስርዓት ፀሎት ማድረጉ ይህም የፍቅር አገልግሎት ወይንም ብሀክቲ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ጀርመንኛ ካል ዩግ ዘመን ማለት መዋጋት መበጣበጥ ማለት ነው፡፡ ማንም ሰው የእውነትን ፈለግ ለመከተለ ፍላጎቱ ያለው አይገኝም፡፡ መዋጋት ብቻ ነው የምናየው፡፡ “በእኔ አስተያየት ይህ” የምለውም “የእኔ አስተያየት እንዲህ ነው” ያልከውም “የእርሱ አስተያየት” ብዙ የሞኝ አስተያየቶች አሉ፡፡ እርስ በእርሳቸውም ይዋጋሉ፡፡ ይህ ነው ዘመኑ፡፡ የፀና አስተያየት የለም፡፡ እያንዳንዱ ሰው የእራሱ የተለየ አስተያየት አለው፡፡ ሰለዚህ ውጊያ የማይቀር ነው፡፡ ምክንያቱም ሁሉም “እንደዚህ ነው የማስበው ሰለሚል ነው” ታድያ እንደዚህ ማሰቡ ዋጋው ምንድን ነው፡፡ ይህ የካሊዩጋ ዘመን ምልክት ነው፡፡ ምክንያቱም የፀና የእውቀት መመሪያ ሰለሌለ ነው፡፡ አንድ ሕፃን ልጅ “አባት ሆይ በእኔ አስተያየት አንተ ማድረግ የሚገባህ እንዲህ ነው” ብሎ ቢናገር አባቱ ሊቀበለው ይችላልን? ሕፃኑ እውቀት ከሌለው እንዴት አድርጎ አስተያየት ሊሰጥ ይችላል፡፡ ታድያ በዚህ በካሊ ዩጋ ዘመን እያንዳንዱ ሰው የእራሱ የሆነውን አስተያየት አዘጋጅቶ አስቀምጧል፡፡ ሰለዚህም ብዙ ብጥብጥ እናያለን፡፡ ለምሳሌ የተባበሩት መንግስታት ውስጥ ብዙ መሪዎች ለመሰባሰብ ሲሄዱ እናያለን፡፡ የሚያመጡት ግን ባንዲራ መጨመርን ብቻ ነው። ይኅው ነው፡፡ መዋጋት ይህ ህብረተሰብ የብጥብጥ ህብረተሰብ ሆኖ ብቻ እናየዋለን፡፡ ፓኪስታኒዎች ሂንዱዎች አሜሪካኖች ቭየትናሞች ለመተባበር የተመሰረተ ነበረ ነገር ግር የብጥብጥ ማህበር ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይኅው ነው፡፡ ሁሉም ነገር፡፡ ሁሉም ሰው ፍጹም በለመሆኑ የእራሱን ትክክል ነው ብሎ የሚያሰበውን እውቀት ለማስተላለፍ ይሻል፡፡ ጀርመን ሴት፡ እንደምትለው ከሆነ ካሊ ዩጋ ሁል ግዜ የሚኖር ነውን? ፕራሁፓድ፡ አይደለም፡፡ ማለትም ሞኞች ሰዎች ይህን አስተሳሰብ ያስፋፉበት ዘመን ነው ለማለት ነው፡፡ መስማማትን እንዳይፈጥሩ መዋጋትን ሲጨምሩ ይታያሉ፡፡ ምክንያቱም ምንም የፀና እውቀት ስለሌላቸው ነው፡፡ ሰለዚህም ብራህማ ሱትራ ሰለ ፍፁም የሆነው እውነት ለመጠየቅ በጣም ጉጉት እንዲኖረን ያሰፈልገናል፡፡ “አትሀቶ ብራህማ ጂግናሳ” መልሱም በሚቀጥለው ተጠቅሷል፡፡ “ይህ ብራህማ ወይንም ፍፁም የሆነው እውነት ጌታ የሁሉም ነገር መነሻ ምንጭ ነው፡፡ ”አትሀቶ ብራህማ ጂግናሳ ጃንማዲ አስያ ያታሀ“ (ሽብ፡ 1 1 1) አሁን መነሽው ምን እንደሆነ ..... ሁሉም ሰው የሁሉም ነገር መነሻው ምን እምደሆነ ለማወቅ ትግል ላይ ነው፡፡ መሆን ያለበት ዓላማችን ይህ ነው፡፡ እነዚህንም የፍልስፍና ጥቅሶች ብተከተሉ ውጊያው ሁሉ ይቆማል፡፡ ረጋ እና የማያወላውል ይሆናላችሁ፡፡ እንደ ጥቅሱ “ታትቫ ጂግናሳ” “ታትቫ ጂግናሳ ማለት ሰለ ፍፁም ሰለሆነው እውነት መጠየቅ ማለት ነው፡፡ ቁጭ በሉ ምክንያቱም በህብረተሰቡ ውስጥ ዓዋቂ የሆኑ ሰዎች መኖር አለባቸው፡፡ እነዚህም ሰለ ፍፁም ሰለሆነው እውነት የሚወያዩ መሆን አለባቸው፡፡ ሌሎችንም የሚያሰተምሩ መሆን አለባቸው፡፡ "ጓደኞቼ ሆይ ፍፁም የሆነው እወነት ይህ ነው” እንደዚህ መሆነ አለበ፡፡ ይህም በህብረተሰብ የሚያሰፈልግ ነው፡፡ እዚህ ግን በእውነቱ እንደምናየው ሁሉም ሰው ፍፁም እወነተኛ መሆን የፈልጋል፡፡ ይህም ብጥብጥ ያመጣል፡፡