AM/Prabhupada 0204 - እኔ የማገኘው የመንፈሳዊ አባቴን በረከት ነው፡፡ ይህም ቫኒ ይባላል፡፡
Morning Walk -- July 21, 1975, San Francisco
ፕራብሁፓድ:ከሁለቱም ጋር መተባበር እና መጎዳኘት አለባችሁ: “ጉሩ ክርሽና ክርፓያ ፓያ ብሃክቲ ላታ ቢጅ” (ቼቻ ማድህያ 19 151) ሁለቱም:“ጉሩ ክሪፓ” እና “ክርሽና ክሪፓ” በአንድነት መሆን አለባቸው: እንደዚህም በረከቱን ታገኛላችሁ: ጃይአድዌይታ:ጉሩ ክሪፓን ለማግኘት እኛም:በጣም እንመኛለን:
ፕራብሁፓድ:ማን? ጃይአድዌይታ:እኛ:ሁላችንም:
ፕራብሁፓድ: አዎን:“ያስያ ፕራሳዶ ብሃጋቫት ፕራሳዳህ” ጉሩ ክሪፓ ካገኛችሁ:ክርሽና ክሪፓን አውቶማቲካሊ ታገኛላችሁ: ናራያና:ጉሩ ክሪፓ ሊመጣ የሚችለው:መንፈሳዊ አባትን በማስደሰት ብቻ ነውን ፕራብሁፓድ?
ፕራብሁፓድ:አለበለዛ እንዴት ሊሆን ይችላል?ናራያን:ምን አልከኝ?
ፕራብሁፓድ:አለበለዛ እንዴት በረከቱ ሊመጣ ይችላል? ናራያና:እነዛስ ተማሪዎችህ አንተን ለማየት እድል የሌላቸው:ወይንም አንተን ለማናገር እድል የሌላቸውስ:እንዴት ምርቃትህን ማግኘት ይችላሉ?
ፕራብሁፓድ:አንተ የምትለው ቫኒ እና ቫፑ ነው:በውን ባትገናኘው እንኳን:ትእዛዙን እና ቃሉን ተቀበል:ይህም ቫኒ ይባላል: ናራያና:ታድያ አንተን እንደአስደሰቱ እንዴት ያውቃሉ ሽሪላ ፕራብሁፓድ?
ፕራብሁፓድ:ቃሎቹን እና ትእዛዙን የምትከተሉ ከሆነ:እርሱም ተደስቷል ማለት ነው: የማትከተሉ ከሆነ ግን እንዴት ሊደሰት ይችላል? ሱዳማ:ያም ብቻ ሳይሆን:የአንተ በረከት:በአለም ላይ እየተሰራጨ ነው:አንድ ግዜ የነገርከንንም ብንጠቀምበት:ውጤቱ ሊታወቀን ይችላል:
ፕራብሁፓድ: አዎን: ጃይ አድዌይታ:ጉሩ በሚለውም እምነት ካለን:ወዲያውኑ ትእዛዙን እንፈጽማለን:
ፕራብሁፓድ:አዎን: የእኔ ጉሩ ማሃራጅ ከዚህ አለም ያለፈው:በ1936 ነው:እኔ ደግሞ ይህንን የአለም አቀፍ እንቅስቃሴ የጀመርኩት:በ1965 ነው:ይህም ከ30 አመት በኋላ ነው: ታድያ?አሁኑም የጉሩዬን ምርቃት እያገኘሁኝ ነው: ይህ ቫኒ ይባላል:ጉሩ በውን ባይኖርም:ቫኒ ወይንም ትእዛዙን ብትከተሉ:ምርቃቱን ሁሌ ታገኛላችሁ: ሱዳማ:ይህም ማለት:ከጉሩ ምንም ግዜ መለያየት አይኖርም ማለት ነው:ይህም ትእዛዙን እስከተከተሉ ድረስ ማለት ነው:
ፕራብሁፓድ:መለያየት የለም “ቻክሁ ዳን ዲሎ ጄይ” የሚቀጥለው ምንድን ነው? ሱዳማ:”ቻክሁ ዳን ዲሎ ጄይ ጃንሜ ጃንሜ ፕራብሁ ሴይ“
ፕራብሁፓድ:ጃንሜ ጃንሜ ፕራብሁ ሴይ:ታድያ መለያየቱ የት አለ? መንፈሳዊ አይንህን የከፈተው ጉሩ:ከትውልድ ትውልድ ጌታህ ነው: ፓራማሃምሳ:ከመንፈሳዊ አባትህ ጋር ጠንካራ መለያየት አይሰማህንምን?
ፕራብሁፓድ:ያን መጠየቅ አያሰፈልግህም: