AM/Prabhupada 0206 - በቬዲክ ባህል ግዜ ገንዘብ የሚባል ነገር አልነበረም፡፡



Morning Walk -- October 16, 1975, Johannesburg

ፕራብሁፓድ፡ ሁሉን ሰው ተንኮለኛ ቢሆኑም ተቀበሏቸው፡፡ ከዚያም አስተምሯቸው፡፡ ይህ ነው የሚፈለገው፡፡ ሁሉም ተንኰለኞች እንደመሆናቸው ተቀበሏቸው፡፡ “ይህ አዋቂ ነው ይህ ተንኮለኛ ነው” እያሉ መለያየት አያሰፈልግም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉን ተንኰለኞች ሁሉ ተቀበሏቸው፡፡ ይህ አስፈላጊ ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ ይህ ያስፈልጋል፡፡ በአሁኑ ግዜ ይህ ዓለም ተንኮለኞች የሞሉበት ነው፡፡ የክርሽና ንቃትንም ለመቀበል ፍላጎት ካደረባቸው ከእነርሱ መሀል ያሉትን መምረጥ ትችላላችሁ፡፡ ልክ እኔ እንደማስተምረው፡፡ እናንተ በእኔ ትምህርት ብራህመና (ቀሳውስት) ለመሆን በቅታችኋል፡፡ አንድ ሰው ብራህመና ለመሆን ብቁ ፍላጎት ካለው እንደ ብራህመና አድርጋችሁ መመደብ ትችላላችሁ፡፡ ሌላው እንደ ክሻትርያ (ተከላካይ) ሆኖ የተማረ ከሆነ እንደ ክሻትርያ አድርጋችሁ መድቡት፡፡ በዚህም መንገድ “ቻቱር ቫርንያም ማያ ስርስ” ሀሪኬሻ፡ ታድያ ይህም ክሻትርያ ሁሉን ሰው በስሩ እንደ ሱድራ (የቀን ሰራተኛ) አድርጎ ያሰራዋል፡፡ ከእነዚህም መምረጥ ይገባናል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ምን አልክ? ሀሪኬሽ፡ በመጀመሪያ ይመርጣል

ፕራብሁፓድ፡ አይደለም አንተ ራስህ መምረጥ አለብህ፡፡ ጠቅላላውን ህዝብ እንደ ሱድራ አድርገህ ተቀበል፡፡ ከዚያም ሀሪኬሽ፡ ምረጥ

ፕራብሁፓድ፡ ምረጥ ከዚያም ሌሎቹ ሁሉ ብራህማና ክሻትርያ እና ቫይሻ ያልሆኑት ሁሉ ሱድራ ናቸው፡፡ ይኅው ነው፡፡ በቀላሉ ይኅው ነው፡፡ እንደ ኤንጂኔር ሆኖ ለመማር ካልቻለ እንደ ተራ ሰው ሆኖ መኖር ይችላል፡፡ ጉልበት የሚባል ነገር የለም፡፡ በዚህ መንገድ ነው ህብረተሰብን ለማደራጀት የሚቻለው፡፡ በጉልበት የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ሱድራም በህብረተሰብ ውስጥ ያስፈልጋል፡፡ ፑስታ ክርሽና፡ በአሁኑ ዘመን ትምህርት የመማሩ ዓላማ ኤንጂኔር ለመሆን እና ገንዘብ ለማግኘት ነው፡፡ በቬዲክ በሀልስ ግዜ የትምህርቱ ዓላማ ምንድን ነበር?

ፕራብሁፓድ፡ በዚይን ግዜ የገንዘብ ፍላጎት አለነበረም፡፡ ብራህማና ሁሉን የሚያሰተምረው በነፃ ነበር፡፡ ገንዘብ የሚያሰፈልግበት አልነበረም። ማንም ሰው ቢሆን እንደ ብራህመናም ሆነ እንደ ክሻትርያ ወይንም እንደ ቫይሻ ትምህርትን ለመውሰድ ይችላል፡፡ ቫይሻ ትምህርት አያሰፈልገውም፡፡ ክሻትርያ ትንሽ ያሰፈልገዋል፡፡ ብራህመና ግን ብዙ ትምህርት ያሰፈልገዋል፡፡ ቢሆንም ግን ይህ ትምህርት ነፃ ነው፡፡ አንድ ሰው ይህን ብራህመና ወይንም ጉሩ (መንፈሳዊ መምህር) ማግኘት አለበት፡፡ ይህ ነው የሚያሰፈልገው፡፡ ይህ ነው ህብረተሰብ ማለት፡፡ በአሁኑ ግዜ ግን አንድ ሰው ትምህርትን ሲፈልግ ገንዘብ ያሰፈልገዋል፡፡ ነገር ግን በቬዲክ ሕብረተሰብ ውስጥ ለትምህርት ገንዘብ አያሰፈልግም ነበር፡፡ ትምህርት በነፃ ነው፡፡ ሀሪኬሽ፡ ታድያ የህብረተሰብ ዓላማ ደስተኛ ለመሆን ነውን?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ይኅው ነው፡፡ ሁሉም ይህንን እየፈለገ ነው፡፡ “ደስታን የት ነው የምናገኘው?” ይህ ነው ደስታ ሊሆን የሚችለው፡፡ ህዝቡ በሰላም ሲኖር በመኖሪያ ሁኔታቸውም ደሰታኛ ከሆኑ ይህ ደስታን ሊያመጣ ይችላል፡፡ እንዲህ ነው እንጂ “በከተማ ትላልቅ ህንፃዎች ብንሰራ ደስተኛ እንሆናለን” በማለት አይደለም፡፡ ከዚህም ትልቅ ሕንፃ ዘሎ ወድቆ ሕይወትን ማጥፋትም አለ፡፡ ይህ እየተካሄደ ነው፡፡ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ሊያስብ ይችላል፡፡ “ትልቅ ህንፃ በከተማ ቢኖረኝ ደሰተኛ ለመሆን እችላለሁ” ከዚያም ብዙ ጭንቀት ሲያስቸግረው ዘሎ ወድቆ ሕይወቱን ያጠፋል፡፡ ይህ ደስታ ነውን? ይህም ማለት እነዚህ ተንኮለኞች ሁሉ ደሰታ ምን እንደሆን አያውቁም፡፡ ሰለዚህ በምድር ላይ ሁላችንም የክርሽናን መመሪያ ማወቅ ያሰፈልገናል፡፡ ይህም የክርሽና ንቃት ይባላል፡፡ ቀደም ብለህ እንደተናገርከው በዚህ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ሕይወትን የማጥፋት ችግር አለ ብለሀል፡፡ ፑስታ ክርሽና፡ አዎን

ፕራብሁፓድ፡ ለምን? ይህ አገር ብዙ የወርቅ ክምችት ያለበት አገር ነው፡፡ ታድያ ለምን ሰዎች እራሳቸውን ይገላሉ? ቀደም ብለህ እንደተናገርከውም እዚህ ድሀ ለመሆን አይቻልም፡፡ ፑስታ ክርሽና፡ አዎን እዚህ ድሀ ለመሆን ጥረት ማድረግ ያሰፈልግሀል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ቢሆንም ግን ሰዎች ሕይወታቸውን እያጠፉ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ሀብታም ነው፡፡ ታድያ ለምንድነው ሰዎች ሕይወታቸውን የሚያጠፉት? መመለስ ትችላለህን? ዲቮቲ (አገልጋይ)፡ ማዕከላዊ የሆነ ደስታ የላቸውም፡፡ ፕራብሁፓዳ፡ አዎን ደስታ የላቸውም፡፡