AM/Prabhupada 0222 - ይህንን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ወደፊት ከመግፋት አታቁሙ፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search
Go-previous.png የቀድሞው ገፅ - ቪድዮ 0220
የሚቀጥለው ገፅ - ቪዲዮ 0225 Go-next.png

Don't Give Up Pushing on this Movement -
Prabhupāda 0222


His Divine Grace Srila Bhaktisiddhanta Sarasvati Gosvami Prabhupada's Disappearance Day, Lecture -- Los Angeles, December 9, 1968

ይህ በጣም አስደሳች የሆነ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ”አሀም ትቫም ሳርቫ ፓፔብህዮ ሞክሽያሚ ማ ሹቻሀ“ (ብጊ፡ 18 66) በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ አብዩ አምላክ እንዲህ ብሏል፡፡ ”የሰው ልጅ ስቃይ ሁሉ የሚመጣው ከሀጥያታዊ ስራው አንፃር ነው፡፡“ ድንቁርናም የሀጥያት ሁሉ መነሻ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው አያውቅ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ እንደኔ ዓይነቱ እንግዳ በአሜሪካ ውስጥ መጥቶ ሰለ አገሩ ብዙ ላያውቅ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ለምሳሌ ህንድ አገርን እንውሰድ፡፡በእናንተ አገር ውስጥ መኪና የሚነዳው በቀኝ በኩል ነው፡፡ ነገር ግን በሕንድ አገር ልክ በለንደን እንደምታዩት መኪና የሚነዳው በግራ በኩል ነው፡፡ ይህም እንግዳ ይህንን አያውቅም እንበል፡፡ በዚህም ባለማወቅ በግራ በኩል እየነዳ አደጋ አጋጠመው እንበል፡፡ በፖሊስም ተይዞ ታሰረ እንበል፡፡ እንዲህም በፖሊስ ጣቢያ ሊናገር ይችላል፡፡ ”ጌታዬ መኪና በቀኝ በኩል እንደሚነዳ አላውቅም ነበረ፡፡“ ይህ ምሕረት እንዲደረግለት ሊያበቃው አይችልም፡፡ ሕጉም ይቀጣዋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ድንቁርና የህግጋትን መስበር ምክንያት ሊሆን ይችላል ወይንም የሀጥያት ሁሉ መነሻ ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ ሰው በሀጥያታዊ ሰራ በተሰማራ ቁጥር ወደፊት ስቃይ ውስጥ ገብቶ መቸገሩ የማይቀር ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ መላ ዓለም በዚህ ድንቁርና ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ በዚህም ድንቁርና ምክንያት ሕይወቱ ሁሉ በበጐ እና በክፉ ስራ ተወሳስቦ ይገኛል፡፡ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ ከመንፈሳዊነት የራቀ ምንም ዓይነት ጥሩ ነገር ሊኖር አይችልም፡፡ ሁሉም መጥፎ ሆኖ ይገኛል። ጥሩ የሆነ እና መጥፎ የሆነ ምግባር ውስጥ ሁሌ ተሰማርተን እንገኛለን፡፡ በብሀገቨድ ጊታ ቅዱስ መጽሀፍ ውስጥ እንደምንረዳው ይህ ዓለም ”ዱክሀላያምአሻሽቨታም“ (ብጊ፡ 8 15) ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህ የመከራ ዓለም ነው፡፡ እንዴትስ በዚህ በመከራ ሁኔታ ላይ እየኖርን “ይህ ጥሩ ነው” ”ይህ ጥሩ አይደለም“ እንላለን? ሁሉም ነገር መጥፎ ነው፡፡ እነዚያም እውቀቱ የሌላቸው ሁሉ በቁሳዊው ውስን ሕይወት ውስጥ ተወሳስበው የተለያዩ ነገሮች ሲያመርቱ ይታያሉ፡፡ ”ይህ ጥሩ ነው ይህ መጥፎ ነው“ በማለት ሲያማርጡ ይገኛሉ፡፡ የማያውቁት ነገር ቢኖር ግን በዚህ ዓለም ውስጥ ከመንፈሳዊ እውቀት ጋር ያልተያያዘ ነገር ሁሉ መጥፎ እንደሆነ አይረዱም፡፡ አንድ ሰው ሰለዚህ ቁሳዊ ዓለም የተቃረነ አስተያየት እንዲኖረው ያሰፈልጋል፡፡ በዚህም አስተያየት መነሻ በመንፈሳዊ ሕይወት ኑሮ ወደፊት ለመራመድ ይችላል፡፡ ”ዱክሀላያም አሽሽቫታም“ (ብጊ፡ 8 15) ይህ ዓለም መከራ የተሞላበት ነው፡፡ ተንትናችሁም ብታጠኑት የምታገኙት እና የምትገመግሙት መከራ እንደሞላበት ብቻ ነው፡፡ ሰለዚህ ይህን የቁሳዊ ዓለም መከራ እና ችግርን ሁሉ የምንሽሽበትን መንገድ መያዝ ይኖርብናል፡፡ የክርሽና ንቃታችንንም በማዳበር እራሳችንን ወደ መንፈሳዊው ደረጃ ከፍ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ በዚህም ሂደት ወደ መንፈሳዊው የአብዩ አምላክ ቤተመንግስት የምንሄድበት መንገድ ይፈጠራል፡፡ ”ያድ ጋትቫ ና ኒቫርታንቴ ታድ ድሀማም ፓራማም ማማ“ (ብጊ፡ 15 6) አንዴ ከተመለስንም ወደ እዚህ የመከራ ዓለም ደግመን አንመጣም፡፡ ይህም የመንፈሳዊ ቤተ መንግስት የአብዩ አምላክ ከፍተኛው መኖርያ ነው፡፡ ሰለዚህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ገለፃ ተሰጥቷል፡፡ ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበር በዚህ ቅዱስ መጽሀፍ የተመሰረተ ስልጣን ያለው ነው፡፡ በጣምም አስፈላጊ ነው፡፡ እናንተም ይህንን እንቅስቃሴ የምትከተሉ አሜሪካኖች ወንዶች እና ልጃገረዶች ይህንን እንቅስቃሴ ኮስተር ብላችሁ ተከታተሉ፡፡ ይህ የጌታ ቼይታንያ እና የእኔ መንፈሳዊ መምህር ተልእኮ ነው፡፡ እኛም ይህንን ተልእኮ ለማሳካት በድቁና ስርዓት ተከታትሎ የመጣውን መልእክት በማስተላለፍ ላይ እንገኛለን፡፡ እናንተም እኔን ልታግዙኝ ቀርባችኃል፡፡ የምጠይቃችሁ ነገር ቢኖር እኔ በቅርቡ ከዚህ ዓለም ለቃቂ ነኝ፡፡ እናንተም ትኖራላችሁ፡፡ ሰለዚህ ይህንን እንቅስቃሴ ወደፊት ከመግፋት ወደ ኋላ አትበሉ፡፡ በዚህም ስራ ከጌታ ቼታንያ በረከቱን ታገኙታላችሁ፡፡ በረከቱንም ከመንፈሳዊ መምህሬ ከክቡር ብሀክቲሲድሀንታ ሳራስቫቲ ጎስዋሚ ፕራብሁፓድም ታገኙታላችሁ፡፡