AM/Prabhupada 0225 - አትቀየሙ ወይንም አይዙርባችሁ፡፡
Lecture at Engagement -- Columbus, may 19, 1969
የሰው ልጅ ስልጣኔ ማተኮር ያለበት እራስን ስለማወቅ እኔ ማን እንደሆንኩ ማወቅን እና ሕይወታችንንም ከዚሁ አንፃር ማስተካከል ላይ ነው፡፡ ብሀገቫታ እንዲ ይለናል። "እራሳችንን የምናውቅበት ደረጃ ላይ ካልደረስን ግን" "የምንሰራው ሁሉ የሚሸነፍ ወይንም እንዲሁ ግዜን ማባከን ብቻ ይሆናል፡፡" በተጨማሪም የሕይወታችንን ምንም አጭር ግዜ የሚሆን እንኳን እንዳናባክን ማስጠንቀቂያው ተሰጥቶናል፡፡ እባካችሁ እነዚህን የቬዲክ ትእዛዞች ለመረዳት እና እንዴት ጥሩ እንደሆኑ ለመረዳት ሙከራ አድርጉ፡፡ አንድ ቻናክያ ፓንዲት የሚባል ታላቅ ፖለቲከኛ ነበረ፡፡ እርሱም ቻንድራ ጉብታ ተብሎ ለሚታወቀው ንጉስ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ የሚያገለግል ነበረ፡፡ ይህም አሌክሳንደር ዘ ግሬት በግሪክ ውስጥ በሚገዛበት ግዜ ነው፡፡ የንጉሱ ቻንድራ ጉፕታ ጠቅላይ ሚኒስቲርም ሆኖ ሲያገለግል እያለ ብዙ የሞራል እና የህብረተሰብ ጥሩ ትእዛዞች ነበሩት፡፡ ከጥቅሶቹ አንዱም እንዲህ ይላል፡፡ "አዩ ሻ ክሳና ኤኮ ፒና ላብያሀ ስቫርና ኮቲብሂህ" "አዩሻ" ማለት የሕይወታችሁ ግዜ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አንተ 20 ዓመት ነህ እንበል፡፡ ዛሬ ሜይ 19 ነው፡፡ ዛሬም 4 ፒም ነበረ፡፡ አሁን ይህ 4 ፒም 19 ሜይ 1969 ሂዷል ጠፍቷል፡፡ ግዜውን ምንም ብዙ ሚልዮን ዶላር ብትከፍሉም ልትመልሱት አትችሉም፡፡ ይህንን መረዳት አለብን፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ምንም ትንሽ አጭር ግዜም ብትሆን በዚህ ዓለም በስሜታዊ ደስታ ላይ እየተሰማራን ግዜያችንን እናባክናለን፡፡ ሁሌ መብላት መተኛት በወሲብ መሰማራት መከላከል በእነዚህ ላይ ሀሳባችንን በማተኮር የሕይወታችንን ጥቅም በመዘንጋት ላይ እንገኛለን፡፡ ብዙ ሚሊዮን ዶላር በመክፈል ይህችን ትንሿን ግዜ እንኳን ለመመለስ አንችልም፡፡ በዚህም መንገድ ሕይወታችን እንዴት በጣም አስፈላጊ እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡ ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴያችን የተቋቋመው ሕብረተሰቡን ይህ ሕይወት እንዴት በጣም አስፈላጊ እና እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደ አለብን ለማስተማር ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴያችን "ሳርቬ ሱክሂኖ ብሃቫንቱ" ይባላል፡፡ ሁሉን ለማስደሰት የቆመ ማለት ነው፡፡ ይህም ለሰው ልጅ ሕብረተሰብ ብቻ ሳይሆን ለእንስሶችም ጭምር ነው፡፡ የእኛ ፍላጎት ሁሉም በጣም ደስተኛ እንዲሆን ነው፡፡ ይህ ነው የክርሽና ንቃተ ማህበራችን ዓላማ፡፡ ደግሞም ተግባራዊ ነው፡፡ ሕልም አይደለም፡፡ ሁሉም ደስተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ቅር አይበላችሁ፡፡ ግራ አይግባችሁ፡፡ ሕይወታችሁ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡ እያንዳንዳችሁ በዚሁ ኑሮአችሁ ውስጥ ሕይወታችሁ ዘለዓለማዊ መሆኑን መረዳት ትችላላችሁ፡፡ ይህም በዘለዓለማዊ ደስታ እና ሙሉ እውቀት የተመሰረተ ነው፡፡ ይህ የሚቻል ነው፡፡ የማይቻል አይደለም፡፡ እኛም የምናደርገው ጥረት ሁሉ ይህንኑን መለእክት ለመላው ዓለም ለማስተላለፍ ነው፡፡ “ሕይወታችሁ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ልክ እንደ ውሾች እና እንደ ድመቶች አታባክኑት፡፡ እንደአግባቡ ሙሉ ለሙሉ ተጠቀሙበት፡፡” ይህ ነው በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ የተጠቀሰው፡፡ ይህንንም ብሀገቨድ ጊታ አሳትመነዋል፡፡ ለማንበብ ሞክሩ፡፡ በዚህም የብሀገቨድ ጊታ ቅዱስ መጽሀፍ ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ “ጃንማ ካርማ ሜ ድቭያም ዮ ጃናቲ ታትቫታሀ” በቀላሉ መረዳት ያለብን ክርሽና ማን እንደሆነ የሚያደርገውስ ምንድን ነው? ሕይወቱስ በምን የተመረኮዘ ነው? የሚኖረውስ የት ነው? ምንስ ይሰራል? “ጃናማ ካርማ” ጃንማ ማለት ትውልድ እና ሞት ማለት ነው፡፡ ካርማ ማለት እንቅስቃሴዎች ወይንም ስራዎች ማለት ነው፡፡ ዲቭያም ማለት ደግሞ መንፈሳዊ ማለት ነው፡፡ “ጃንማ ካርማ መ ዲቭያም ዮ ጃናቲ ታትቫታሀ” አንድ ሰው የክርሽናን ትውልድ እና ከዚህ ዓለም መልቀቅ ዓላማ በትክክል እና በእውነቱ የሚረዳ ከሆነ በሴሜታዊ እምነት ሳይሆን በሳይንሳዊ ሂደት ከዚያ ውጤቱ እንዲህ ይሆናል፡፡ “ዴሀም ፑናር ጃናማ ናይቲ ማም ኢቲ ኮንቴያ” (ብጊ፡ 4 9) ሽሪ ክርሽናን በትክክሉ በመረዳት ብቻ ውጤቱ ከሞት በኃላ ወደ እዚህ ወደ መከራ ወደተሞላበት ቁሳዊ ዓለም አትመለሱም፡፡ ይህም የተረጋገጠ ነው፡፡ ታድያ በዚሁ ሕይወታችሁ ይህንኑ ብትረዱ በጣም ደስተኞች ትሆናላችሁ፡፡