AM/Prabhupada 0226 - የአብዩ ጌታን ስም ምስጋና እንቅስቃሴዎች ቁንጅና እና ፍቅር ማስፋፋት፡
Lecture -- Los Angeles, May 18, 1972
በተግባር ስናየው ክርሽና በዚህ በቁሳዊ ዓለም ውስጥ አብሮን ሲኖር አናየውም፡፡ ልክ እንደ ትልቅ ሰው፡፡ የፋብሪካው ስራ እየተካሄደ ነው፡፡ ንግዱም እየተቀላጠፈ ነው ነገር ግን እርሱ ራሱ በፋብሪካው ውስጥ የመገኘት ግዴታ የለውም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የክርሽና ሀይል በዚህ ቁሳዊ ዓለም ላይ እየተካሄደ ነው፡፡ አገልጋዮቹ መላእክቶቹ ሁሉ በየድርሻቻው እያገለገሉ ነው፡፡ እነዚህም በቬዲክ ስነጽሁፎች ተገልፀዋል፡፡ ለምሳሌ እንደ ፀሀይ ፀሀይ ለምሳሌ በዚህ ትዕይንተ አለም ውስጥ እንደ መነሻ ሆኖ ይታያል፡፡ ይህም በብራህማ ሰሚታ ውስጥ ተገልጿል፡፡ “ያክ ቻክሱር ኤሻ ሳቪታ ሳካላ ግራሀናም ራጃ ሳማስታ ሱራ ሙርቲር አሼሻ ቴጃሃ ያሽያግናያ ብራህማቲ ሳምብህርታ ካላ ቻክሮ ጎቪንዳም አዲ ፑሩሻም ታም አሀም ብሃጃሚ” ጎቪንዳ...... ፀሀይ የአብዩ ጌታ አንዱ ዓይኑ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ሁሉንም ነገር ያያል፡፡ ከፀሀይ መሸሸግ እንደማይቻል ሁሉ ከአብዩ ጌታም ዓይን መደበቅ አንችልም፡፡ አብዩ ጌታ ሰም አለው፡፡ የተለያዩ ስሞች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በቬዲክ ስነፅሁፎች ውስጥም አብዩ ጌታ ብዙ ስሞች እንደ አሉት ተገልጿል፡፡ ከሁሉም ስሞች በላይ ግን ይህ ስም ”ክርሽና“ ዋናው ነው፡፡ ሙክህያ “ሙክህያ” ማለት ዋነኛው ማለት ነው፡፡ ይህም ቆንጆ ተደርጎ ተገልጿል፡፡ “ሙሉ በሙሉ የሚስብ” በተለያየ መንገድ እርሱ ሙሉ በሙሉ የሚስብ ነው፡፡ ሰለዚህ ይህ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ይህንን የአብዩ ጌታን ስም በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የጌታን ዝና የጌታን ስራዎች የጌታን ቁንጅና የጌታን ፍቅር እና ሁሉንም ነገር በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ቁሳዊ ዓለምም የምናያቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ በጠቅላላ በክርሽና ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡ ያለን ነገር ሁሉ፡፡ ለምሳሌ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ ከፍተኛው የሚስብ ነገር ቢኖር የወሲብ ፍላጎት ነው፡፡ ይህም የፆታ መሳሳብ በክርሽናም የሚገኝ ነው፡፡ የምንሰግደውም ለራድሀ ክርሽና ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ዓለም ላይ ያለው የወሲብ ፍላጎት እና ይህ ዓይነቱ የክርሽና በፆታ መቀራረብ አንድ አይደለም፡፡ የመንፈሳዊው የእውነት ፍፁም የሆነ ፍቅር ሲሆን የዓለማዊው ደግሞ እውነታዊ ያልሆነ እና ጊዜያዊ ነው፡፡ በመንፈሳዊው ዓለም ያለው ነገር ሁሉ እዚህ ቊሳዊ ዓለም ውስጥ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የምናየው ሁሉ ጥላው ነው እንጂ ዋነኛ ዋጋ ያለው ነገር ሆኖ አይገኝም፡፡ ለምሳሌ በልብስ ሰፊ ሱቅ ውስጥ ብዙ ቆንጆ ልብስ የለባበሱ የአሻንጉሊት ሰዎች ይገኛሉ፡፡ በጣም ቆንጆ ሴት ለብሳ ቁማ ትታያለች፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው ግድ ሰጥቶት ቁሞ የሚያይ ሰው የለም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም የሚያውቀው ይህ የሀሰት ሰው እንደመሆኑ ነው፡፡ ምንም እንኳን በጣም ቆንጆ ቢሆኑም የሀሰት ሰዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ህይወት ያላት ቆንጆ ሴትን ብዙ ሰዎች ለማየት ይመኛሉ፡፡ ምክንያቱም እርስዋ የእውነት ሰው በመሆንዋ ነው፡፡ ይህ ምሳሌ ሊሆነን ይችላል፡፡ በዚህ ዓለም ላይ የምናየውም ነዋሪ የምንለውም ገላ እራሱ የሞተ ነው፡፡ ምክንያቱም ገላ ቁሳዊ ሰለመሆኑ ነው፡፡ የቁሳዊ አካል ክምችት ነው፡፡ ከዚህችም ቆንጆ ከተባለችው ሴት ነፍስ ስትወጣ ማንም ሰው እርስዋን ለማየት ግድ አይሰጠውም፡፡ ምክንያቱም ይህችው ሴት ልክ እንደ በልብስ ቤት ውስጥ እንደምትገኘው አሻንጉሊቷ ስለምትቆጠር ነው፡፡ ሰለዚህ ዋናው የምትስበን ነገር መንፈሳዊዋ ነፍስ ናት፡፡ ሌላው ሁሉ ከቁሳዊ አካል እና ከሞተ ንጥረ ነገር የተሰራ ነው፡፡ ሰለዚህ በዚህ ዓለም የላይ የሚታየው ሁሉ ብልጭልጭ እና እውነት ያለሆነ ነው፡፡ እውነተኛው ዓለም መንፈዋዊው ዓለም ነው፡፡ መንፈሳዊውም ዓለም በእውን የሚኖር ነው፡፡ ብሀገቨድ ጊታን የሚያነቡ ሁሉ ይህንን ለመረዳት ይችላሉ፡፡ መንፈሳዊው ዓለም በዚህ ቅዱስ መጽሀፍ ውስጥ ተገልፆ ይገኛል፡፡ “ፓራስ ታስማት ቱ ብሀቮ ንዮ ቭያክቶ ቭያክታት ሳናታናሀ” (ብጊ፡ 8 20) ብሀቫ ማለት ፍጥረት ማለት ነው፡፡ ከዚህ ከምናየው የትእይንተ ዓለም ፍጥረት ባሻገር ሌላ ፍጥረት አለ፡፡ ይህንን ፍጥረት የምናየው በሰማይ እስከምናያቸው ፍጥረታት ብቻ ነው፡፡ ሳይንቲስቶችም ወደ ታላቁ ፕላኔት ለመሄድ ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን እሰከ 40,000 ዓመታት ሊወስድብን ይችላል ብለው የገምታሉ፡፡ ታድያ ማነው ለ40,000 ዓመታት በመኖር እዚያ ደርሶ ለመምጣት የሚችለው? ቢሆንም ግን እነዚህ ፕላኔቶች አሉ፡፡ ሰለዚህ የመንፈሳዊውን ዓለም ስፋት ይቅርና የዚህን የእራሳችንን ትእይንተ ዓለም ስፋት እና ርዝመት እንኳን ለክተን ለማወቅ አንችልም፡፡ ሰለዚህ እውቀቱን ለማግኘት ስልጣን ካለው ሰው መስማት ይገባናል፡፡ ይህም ባለ ስልጣን ሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ይህንንም ቀደም ብለን ገልፀናል፡፡ ማንም ከክርሽና በላይ እውቀት ያለው ሊኖር አይችልም፡፡ ክርሽናም ይህንን እውቀት ሰጥቷል፡፡ "ፓራስ ታስማት ቱ ብሀቮ ንዮ (ብጊ፡ 8 20) “ከዚህ ቁሳዊ ትእይንተ ዓለም ባሻገር ሌላ መንፈሳዊ የሆነ ሰማይ አለ” በዚህም መንፈሳዊ ሰማይ ውስጥ በቁጥር ሊተመኑ የማይችሉ መንፈሳዊ ፕላኔቶች ይገኛሉ፡፡ ይህም የመንፈሳዊ ሰማይ እዚህ ከምናየው ሰማይ በጣም በጣም የተለቀ ነው፡፡ ይህ ቁሳዊ ትእይንተ ዓለም አንድ አራተኛ ቢሆን መንፈሳዊው ዓለም ደግሞ ሶስት አራተኛ ይሆናል፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ በደንብ ተገልጾልናል፡፡ “ኤካምሼና ስትሂቶ ጃጋት” (ብጊ፡ 10 42) ሌላው መንፈሳዊ ዓለም ሶስት አራተኛ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ የአብዩ ጌታ ፍጥረት መቶ ቢሆን ሀያ አምስት ከመቶው እዚህ ሲሆን ሰባ አምስት በመቶው ደግሞ በመንፈሳዊው ዓለም ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በጣም ጥቂት የሚሆኑ ነፍሳት በዚህ ትእይንተ ዓለም ይገኛሉ፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነፍሳት የሚገኙት ግን በመንፈሳዊው ዓለም ነው፡፡