AM/Prabhupada 0233 - የክርሽና ንቃታችንን የምናገኘው በጉሩ እና በክርሽና በረከት ነው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

We Get Kṛṣṇa Consciousness Through the Mercy of Guru and Kṛṣṇa - Prabhupāda 0233


Lecture on BG 2.4-5 -- London, August 5, 1973

ክርሽና እንደ አሪሱዳና የመሰሉ ጠላቶች ነበሩት፡፡ እነዚህንም መግደል አስገድዶታል፡፡ ክርሽና ሁለት ዓይነት ተልእኮ አለው፡፡ "ፓሪትራናያ ሳድሁናም ቪናሻያ ቻ ዱስክርታም" (ብጊ፡ 4 8) አጥፊዎች እነዚህ አጥፊዎች ናቸው፡፡ እነዚህም የሰይጣናዊ ባህርይ ያላቸው የክርሽና ተቀናቃኞች ናቸው፡፡ ከክርሽናም መወዳደር ይፈልጋሉ፡፡ የክርሽናንም ንብረት ሁሉ ለመካፈል ይፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ መገደል የሚገባቸው የአብዩ የመላእክት ጌታ ሽሪ ክርሽና ጠላቶች ናቸው፡፡ ታድያ ይህን ዓይነቱን የሰይጣናውያንን ሕይወት ማጥፋት የተደገፈ ነው፡፡ አለበለዛ ግን መግደል አይደገፍም፡፡ ከዚህም ቀጥሎ ያለው ጥያቄ “የጌታን ጠላቶች መግደልን እንቀበል ይሆናል” ታድያ ጉሩ ወይንም የመንፈሳዊ መምህሬን እንዴት ለመግደል ትእዛዝ ሊሰጠኝ ይችላል? “ጉሩን አሀትቫ” ለምሳሌ ክርሽና ጉሩን (መምህርን) እንድንገድል ያዘዘን ቢሆን መግደል ይጠበቅብናል፡፡ ይህን ነው ፍልስፍናው፡፡ የአብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽናን ትእዛዝ ተከትለን ማድረግ ማለት ነው፡፡ ክርሽና አድርግ ያለውን ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ክርሽና መንፈሳዊ መምህራችንን እንድንገድል ካዘዘን ይህንን ማድረግ ይገባናል፡፡ ይህ የክርሽና ንቃት ነው፡፡ በእርግጥ ክርሽና መምህራችንን (ጉሩ)እንድንገድል አይጠይቀንም፡፡ ምክንያቱም ጉሩ እና ክርሽና አንድ ናቸው፡፡ “ጉሩ ክርሽና ክርፓያ (ቼቻ፡ 19 151) የክርሽና ንቃታችንን ልናዳብር የምንችለው በጉሩ እና በክርሽና በረከት ነው፡፡ ትክክለኛ ንፁህ የሆነ ጉሩ መገደል አይገባውም፡፡ ነገር ግን አታላይ ጉሩ መገደል ይገባዋል፡፡ ይህ ውሸተኛ እና አታላይ ጉሩ መገደል ይገባዋል፡፡ ልክ እንደ ፕራህላድ መሀራጅ፡፡ ፕራህላድ መሀራጅ ነረሽንጋዴቫ አባቱን ሲገልበት ዝም ብሎ ቁሞ ያይ ነበር፡፡ አባቱ እንደ ጉሩ ይጠበቅ ነበር፡፡ ”ሳርቫ ዴቫማዮ ጉሩህ“ (ሽብ፡ 11 17 27) እንደዚሁም ሁሉ አባት እንደ ጉሩ ይቆጠራል፡፡ በቁሳዊው ዓለም እንደ ጉሩ ይቆጠራል፡፡ ታድያ ፕራህላድ መሀራጅ እንዴት ነርሺንጋዴቭ አባቱን እንዲገል ፈቀደ? ሁሉም እንደሚያውቀው ሂራንያካሺፑ አባቱ እንደሆነ ነው፡፡ እናንተ እዚያው ቆማችሁ አባታችሁ ሲገደል ብታዩ ዝም ትላላችሁ? አትቀናቀኑም? ሀላፊነታችሁ ይህ ነውን? አባታችሁ ሲጠቃ መቀናቀን አለባችሁ፡፡ አቅም ባይኖራችሁም መቀናቀን አለባችሁ፡፡ ሕይወታችሁንም መሰዋት ይጠበቅባችኋል፡፡ ”ለምን በደጃፌ ላይ አባቴ ሲገደል ዝም ብዬ አያለሁ?“ ይህ ነው የእኛ ሀላፊነት፡፡ ነገር ግን ፕራህላድ መሀራጅ አባቱ ሲገደል አልተቀናቀነም፡፡ እንዲህ ብሎም እንደ ብሀክታ ወይንም የጌታ አገልጋይ መናገር ይችል ነበረ፡፡ ”ጌታዬ ሆይ አባቴን ይቅር በለው፡፡“ ነገር ግን አባቱ እንደማይገደል ያውቃል፡፡ ”አባቴ ሊገደል አይችልም፡፡ የሚገደለው የአባቴ ገላ ነው፡፡“ አባቱ ከተገደለም በኋላ ለአባቱ ደህንነት መለመን ጀመረ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ነረሽንጋዴቫ በንዴት ላይ እያለ የአባቱን ገላ በመግደል ተሰማርቶ ነበረ፡፡ ፕራህላድም የአባቱ ገላ አባቱ እንደአልሆነ ያውቅ ነበር፡፡ ነፍሱ ግን አባቱ እንደሆነ ያውቃል፡፡ ያስብም የነበረው አብዩ ጌታ እንዲገለው ስለፈለገ ገላውን በመግደል ደስታውን ያግኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን የአባቴን ነፍስ ለማዳን ጥረት አደርጋለሁ፡፡