AM/Prabhupada 0234 - የዓብዩ ጌታ አገልጋይ መሆን ታላቁ ሙያ ነው፡፡
Lecture on BG 2.4-5 -- London, August 5, 1973
ፕራህላድ መሀራጅ......ሽሪ ነረሽናግሀዴቭም ለፕራህላድ መሀራጅ እንዲህ አለው፡፡ "አሁን ከእኔ የፈለግኀውን ዓይነት ምርቃት ለመውሰድ ትችላለህ፡፡" ፕራህላድ መሀራጅም እንዲህ ብሎ መለሰ "እኛ ዓለማውያን ነን" "የተወልድኩበት አባቴ በጣም ዓለማዊ ሰው ነው፡፡" "እኔም ከእርሱ ከዓለማዊው አባቴ በመወለዴ እኔም ዓለማዊ ነኝ፡፡" "አንተ ደግሞ አብዩ የመላእክት ሁሉ ጌታ ምርቃትህንና በረከትህን ልታወርድልኝ ትፈልጋለህ፡፡" እኔም ይህንን በደንብ አውቃለሁ፡፡ የፈለግሁትን ነገር እንደምታቀርብልኝ አውቃለሁ፡፡ ”ግን ይህ ምን ዋጋ አለው? ለምን ብዬስ ለዚህ ዓለም ሀብት እጠይቅሀለሁ? አባቴንም አይቸዋለሁ፡፡“ “በዚህ ቁሳዊ ዓለም ላይ በጣም ሀይል የነበረው ሰለመሆኑ እንደ እነ ኢንድራ ቻንድራ ቫሩና የመሳሰሉት መላእክቶች ሁሉ ቀዩን ዓይኖቹን ብቻ ሲያዩ ይርበደበዱ ነበር፡፡ በዚህም ሀይሉ ትእይንተ ዓለምን መቆጣጠር ጀመረ፡፡ በጣም ሀይለኛ ነበረ፡፡ ”ብዙ ሀብት ያለው ሀይል ዝና ሁሉ ነገር በሙሉ ደረጃ ያለው ነበረ፡፡ ነገር ግን አንተ በሴኮንድ ውስጥ ልታጠፋው ችለሀል፡፡“ “ታድያ አንተ ይህንን የመሰለ ሀብት ለምን ታቀርብልኛለህ? በዚህስ ሀብት ምን አደርግበታለሁ?” ይህንንም ምርቃት እና ሀብት ከአንተ ወስጄ ልቤ ቢያብጥስ? ”ከዚያም ሁሉን ነገር አንተን በመቀናቀን ልጠቀምበት እችል ይሆናል፡፡ ከዚያም አንተ መጥተህ በሴኮንድ ውስጥ ልታጠፋኝ ትችላለህ፡፡“ ”ሰለዚህ ይህንን አይነት ብዙ ሀብት የሚሰጥን ምርቃት አትስጠኝ፡፡“ የሚሻለው ግን የአንተን አገልጋዮችን የማገለግልበት ምርቃት ብትሰጠኝ ነው የሚሻለኝ፡፡ የአንተ የቀጥታ አገልጋይ ሳይሆን የአንተ አገልጋዮች አገልጋይ እንድሆን ምርቃቱን ስጠኝ፡፡ ከዚያም ከብዙ ፀሎት እና አብዩ ጌታን ከአስደሰተው በኋላ ነረሽንጋዴቭ በጣም ንዴት ላይ ሰለነበረ በፀሎቱ ካረካው በኋላ እንዲህ ብሎ ጠየቀው፡፡ ”ጌታዬ ሆይ አንድ ለየት ያለ ምርቃት ግን ልጠይቅህ እወዳለሁ“ እንደምታውቀው አባቴ በጣም ሀይለኛ ተቀናቃኝ ጠላትህ ነበረ፡፡ የሞተበትም ምክንያቱ በዚሁ ነው፡፡ ”አሁን የጠይቅህ ነገር ቢኖር ግን ይቅርታ እንድታረግለት እና ከዚህ ቁሳዊ ዓለም ነፃነቱን እንድትሰጠው ነው፡፡“ ይህ ማለት ነው ቫይሽናቫ ልጅ ማለት! ለእራሱ የሚሆን ምንም ነገር አልጠየቀም፡፡ ምንም እንኳን አባቱ የአብዩ ሽሪ ክርሽና ከፍተኛው ጠላቱ መሆኑን ቢያውቅም እንኳን ለአባቱ በረከቱ እንዲወርድለት ጠየቀ፡፡ “ይህ ድሀ አባቴ ነፃ ይውጣ” ጌታ ነረሽንጋዴቭም አረጋገጠለት፡፡ “ውድ ፕራህላድ ልጄ ሆይ ነፃ የወጣው አባትህ ብቻ ሳይሆን” ”የአባትህ አባትም የእርሱም አባት እስከ 14 ትውልድ ድረስ ሁሉም ነፃ ወጥተዋል፡፡“ ምክንያቱም አንተ የተወለድከው ከዚህ ቤተሰብ ሰለመሆኑ ነው፡፡ ሰለዚህ ማንም ሰው ቫይሽናቭ በመሆኑ እና የአብዩ ጌታ አገልጋይ በመሆን ለቤተሰቡ በጣም ትልቅ የሆነ አገልግሎት አድርጓል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በእርሱ ቤተሰብነት ብቻ አባቱም እናቱም መላ ቤተሰቡ ሁሉ ከዚህ አለም ነፃ ሰለሚወጡ ነው፡፡ ለምሳሌ በልምድ እንደ አየነው አንድ ወታደር በጦርነት ላይ ያለ እንድሜው ቢሞት መላ ቤተሰቡ ሁሉ በመንግስት እንክብካቤ ስር ይኖራሉ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ድቮቲ ወይንም ትሁት አገልጋይ መሆን ትልቅ ደረጃ ያለው ነው፡፡ ድቮቲ ወይንም ትሁት አገልጋይ ሁሉም ነገር ያለው ነው፡፡ “ያትራ ዮጌሽቫሮ ሃሪህ ያትራ ድሀኑር ድሃራህ ፓርትሀህ” (ብጊ፡ 18 78) ክርሽና እና ትሁት አገልጋዩ በአንድነት ሲኖሩ ሁልግዜ ድል እና ውዳሴ ያሉ ናቸው፡፡ ይህን የተረጋገጠ ነው፡፡