AM/Prabhupada 0236 - ብራህማናዎች እና ሳንያሶች መለመን ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ሻትርያዎች እና ቫይሻዎች መለመን አይገባቸውም፡፡

From Vanipedia


A Brahmana, a Sannyasi can Beg Alms, but not a Ksatriya, not a Vaishya - Prabhupāda 0236


Lecture on BG 2.4-5 -- London, August 5, 1973

ሰለዚህ ቼታንያ መሀፕራብሁ እንዲህ አለ፡፡ "ቪሻዪራ አና ክሆይሌ ማሊና ሃያ ማና (ቼቻ አንትያ 6 278) "እነዚህ ታላላቅ ሰዎች "አና" ወይንም ሀብት ከእነርሱ ስለወሰዱ ህሊናቸው ጥቁር ሆነ" እኔ ከአንድ በጣም ዓለማዊ ከሆነ ሰው ሀብት ብወስድ እኔም እንደ እርሱ ዓለማዊ መሆን እጀምራለሁ፡፡ ቀስ በቀስ እኔም እንደ እርሱ ዓለማዊ ሰው እሆናለሁ፡፡ ሰለዚህ ቼታንያ መሀብራብሁ አስጠንቅቆናል፡፡ "እነዚያ ቪሻዪ የሆኑ ወይንም የአብዩ አምላክ ትሁት አገልጋዮች ያልሆኑትን" "ቀርባችሁ ዓለማዊ ነገሮችን አትቀበሉ፡፡ ይህም አእምሮዋችሁን ሰለሚበክለው ነው" ሰለዚህ በቬዲክ ባህል ብራህማናዎች እና ቫይሽናቫዎች ገንዘብ በቀጥታ አይቀበሉም፡፡ የሚቀበሉትም ብሂክሻ ነው፡፡ ብሂክሻ ይቻላል፡፡ ልክ እዚህ ጥቅስ ውስጥ እንደተጠቀሰው፡፡ "ብሀይክሽያም" "ሽሬዮ ብሆክቱም ብሀይክሽያም አፒሀ ሎኬ" (ብጊ 2 5) ለመጠየቅ ይቻላል፡፡ ቢሆንም ግን ይኅው "ብሂክሻ" አንዳንድ ግዜ በጣም ዓለማዊ ለሆነ ሰው የተከለከለ ነው፡፡ ነገር ግን "ብሂክሽያ" ለመነኩሴዎች እና ለብራህማናዎች የተፈቀደ ነው፡፡ ሰለዚህ አርጁና እንዲህ ብሏል "እነዚህን ታላላቅ ሰዎች ለመግደል ከምንበቃ" "እነዚህን ታላላቅ የሆኑ ጉሩዎች (መንፈሳዊ መምብራን) ማሃኑብሀቫን" ሰለዚህ "ብሀይክሽያም" ለሻትሪያዎች..... ብራህማናዎች (ቀሳውስት) እና ሳንያሲዎች (መነኩሴዎች) እርዳታ ለመለመን ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ክሻትርያዎች እና ቫይሻዎች ለመለመን አይችሉም፡፡ አርጁና ሻትርያ ነበረ፡፡ ሰለዚህም እንዲህ አለ "ብራህማና ብሆን ይሻለኛል" "መምህራኖቼን ገድዬ ቤተ መንግስት ከመውረስ በየበሩ እያንኳኳሁ መለመን ይሻለኛል" ይህ ነበር የአርጁና መልእክት በዚህም እንደምናየው አርጁና በምትሀት ውስጥ ገብቶ እንደነበረ ነው፡፡ ይህም ማለት ለጦርነት የመጣበትን ዓላማ እና ሀላፊነት ዘነጋው ማለት ነው፡፡ ክሻትርያ እንደመሆኑ ሀላፊነቱ መዋጋት ነው፡፡ ተቀናቃኞቹ ይቅሩና ልጆቹ እንኳን ቢሆኑም መዋጋት ይጠበቅበታል፡፡ ክሻትርያ ጠላት ሆኖ የቀረበውን ልጁን እንኳን ለመግደል ወደ ኋላ አይልም፡፡ እንደዚሁም ክሻትርያ የሆነ ልጅ አባቱ እንኳን በጠላትነት ቢቀርብ ለመግደል ወደ ኋላ አይልም፡፡ ይህ ነው የክሻትርያዎች ጥብቅ ሀላፊነት ምንም ጥርጣሬ እንዲያድረባቸው አይፈለግም፡፡ ክሻትርያ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው አይገባም፡፡ ሰለዚህም ክርሽና እንዲህ አለ፡፡ "አንተ ፈሪ አትሁን፡፡ ለምንድነው ለመግደል ፍርሀት ያደረብህ?" እንደዚህም ዓይነት ውይይቶች ቀጠሉ፡፡ ክርሽናም ትክክለኛውን የመንፈሳዊ ትእዛዞች ሊሰጠው በቃ፡፡ በእንዲህም አማካኝነት በሁለቱም ጓደኛሞች በሀከል ውይይቱ ቀጠለ፡፡ ይኅው ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡