AM/Prabhupada 0241 - ስሜቶቻችን ልክ እንደ እባብ ይቆጠራሉ፡፡
Lecture on BG 2.3 -- London, August 4, 1973
ገነት በቬዲክ ስነፅሁፎች ውስጥ እንደተጠቀሰው “ትሪ ዳሻ ፑር” ተብሎ ነው፡፡ ትሪ ዳሻ ፑር ማለት 33 ሚልዮን የሚሆኑ መላእክቶች አሉ ማለት ነው፡፡ እያንዳንዳቸውም የራሳቸው የሆነ ፕላኔት አላቸው፡፡ ይህም ትሪ ዳሳ ፑር ተብሎ ይታወቃል፡፡ ትሪ ማለት ሶስት ማለት ነው፡፡ ዳሻ ማለት ደግሞ አስር ማለት ነው፡፡ ሰላሳ ሶስት ማለት ነው፡፡ ትሪ ዳሻ ፑር አካሻ ፑስፓቴ አካሻ ፑሽፓ ማለት በሀሳብ ያለ ማለት ነው፡፡ በሀሳብ የሚታይ፡፡ በሰማይ ያለ አበባ፡፡ አበባ በአትክልት ስፍራ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው አበባን በሰማይ ቢያይ ይህ በሀሳብ የተቀረፀ መሆኑ ነው፡፡ ሰለዚህ ለአብዩ ጌታ ትሁት አገልጋይ ይህ ወደ ገነት መሄድ ልክ በሰማይ እንደሚታየው አበባ ሆኖ ያገኘዋል፡፡ “ትሪ ዳሻ ፑር አካሻ ፑስፓያቴ ካይቫልያም ናራካያቴ” “ግያኒ እና ካርሚ” እና “ዱርዳንተንድሪያ ካላ ሳርፓ ፓታሊ ፕሮትክሃታ ዳምስትራያቴ” ከዚያም ዮጊ፡፡ ዮጊዎች እየሞከሩ ነው፡፡ ዮጊ ማለት “ዮጋ ኢንድርያ ሳምያማ” ስሜታችንን መቆጣጠር ማለት ነው፡፡ ይህም የዮጋ ልምምድ ነው፡፡ ስሜቶቻችን በጣም ሀይለኞች ናቸው፡፡ ልክ እንደ እኛም ቫይሽናቫዎች፡፡ በመጀመሪያ ምላሳችንን ለመቆጣጠር እንሞክራለን፡፡ ዮጊዎችም እንደዚሁ ስሜቶቻቸውን ለመቆጣጠር ይሞክራሉ፡፡ ታድያ ለምንድነው ዮጊዎች ስሜቶቻቸውን ለመቆጣጠር የሚሞክሩት? ምክንያቱም ስሜቶቻችን ልክ እንደ እባብ ናቸው፡፡ እባቦች ..... በምላሳቸው በነኩ ቁጥር አንድ እንስሳ ለሞት ይጋለጣል፡፡ አደጋ ይኖራል ሞትም ይኖራል፡፡ ይህም በምሳሌ ታይቷል፡፡ ልክ እንደ ወሲብ ፍላጎት ወሲብ በታሰበ ቁጥር ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ በአሁኑ ግዜ ሁሉም ነገር ቀላል ሆኗል፡፡ ከዚህ ቀደም ግን በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ በተለይ በህንድ አገር ውስጥ፡፡ ስለዚህም አንዲት ልጃገረድ ሁልግዜ እንደተጠበቀች ነው፡፡ ምክንያቱም ከወንዶች ጋር የምትቀላቀል ከሆነ ወሲብ ላይ የወደቁ ከሆነ እርግዝና ይመጣል፡፡ ከዚይም እርሷን ለመዳር በጣም አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ልክ በእባብ እንደተነካው ፍጥረት። የቬዲክ ስርዓት ሰለዚህ ነገሮች በጣም ጥብቅ ነው፡፡ ምክንያቱም ዓላማው ሁሉ እንዴት ወደ አብዩ አምላክ ቤተ መንግስት ለመመለስ እንደምንችል ነው፡፡ ስሜትን ለማርካት ብቻ አይደለም፡፡ መብላት መጠጣት መደሰት ብቻ አይደለም፡፡ ይህ የሰው ልጅ የሕይወቱ ዓላማ አይደለም፡፡ ሰለዚህ ሁሉ ነገር ፕላን የተነገረው ከዚያ አንፃር ነበረ፡፡ “ቪሽኑ አራድህያቴ” “ቫርናሽራማቻራቫታ ፑሩሼና ፓራሀ ፑማን ቪሽኑር አራድህያቴ ፓንትሀ ናንያት ታት ቶሻ ካራናም” (ቼቻ ማድህያ 8 58) ”ቫርናሽራማ“ እነዚህ ብራህማና ክሻትርያ ቫይሽያ ሁሉም የድርሻቸውን የክፍፍል ህግጋት መጥሞና መከተል ይገባቸዋል፡፡ ብራህማና እንደ ብራህማና መሆን አለበት፡፡ ክሻትርያም እንደዚሁ ክርሽናም እንዲህ ብሏል “አንተ ክሻትርያ ነህ፡፡ ለምንድነው እንደዚህ አይነት ተንኮለኛ ወሬ የምታወራው?” ናይታት ትቫዪ ኡፓፓድያቴ (ብጊ2 3) በሁለት መንገድ ይህንን ማድረግ አይገባህም፡፡ እንደ ክሻትርያ ይህንን ማድረግ አይገባህም፡፡ የእኔ ጓደኛ እንደመሆንህም ይህንን ማድረግ አይገባህም፡፡ ”ይህ ነው ያንተ ድክመት፡፡“ ይህ ነው የቬዲክ ስልጣኔ ማለት፡፡ እንደ ክሻትርያነትህ ተዋጋ፡፡ ብራህማና ሊዋጋ አይችልም፡፡ ብራህማና “ሳትያ ሻሞ ዳማሀ” ተብሎ ይታወቃል፡፡ ልምምድ የሚያደርገውም እንዴት እውነተኛ እንደሚሆን እና እንዴት ንፁህ እንደሚሆን ነው፡፡ እንዴትስ ስሜቶቹን እንደሚቆጣጠር ነው፡፡ እንዴትስ አእምሮውን እንደሚቆጣጠር ነው፡፡ እንዴት ቀለል ያለ ኑሮ እንደሚኖር፡፡ እንዴትስ የቬዲክን እውቀት እንደሚማር፡፡ እንዴትስ በሕይወቱ የተማረውን በተግባር እንደሚያውል፡፡ እንዴት በዓላማው ውስን ሆኖ እንደሚረጋ፡፡ እነዚህ ብራህማናዎች ናቸው፡፡ እንደዚሁም ክሻትርያዎች በውጊያ ይሰማራሉ፡፡ ይህ አስቨላጊ ነው፡፡ “ቫይሽያ ክርሺ ጎ ራክስያ ቫኒጅያም” (ብጊ 18 44) ሰለዚህ እነዚህን ሁሉ መከተል ይገባናል፡፡