AM/Prabhupada 0242 - ወደ መጀመሪያው የሥልጣኔ ስርዓት ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

It is Very Difficult to Take us Back to the Original Process of Civilization - Prabhupāda 0242


Lecture on BG 2.3 -- London, August 4, 1973

ፕራብሁፓድ፡ ትላንትና ሰለማኑ ስናነብ እንደነበረው ወይንም ቫይቫይሽቫታ ማኑ ወደ ካርዳማ ሙኒ መጥቶ እንደነበረው ”ጌታዬ እንደምናውቀው የአንተ ጉብኝት ማለት...." መመርመር ማለት ምንድን ነው? አገልጋይ፡ መፈተሽ ፕራብሁፓድ፡ እየፈተሸ አዎን እየፈተሸ ነበር፡፡ "የአንተ ጉብኝት ማለት እየፈተሽክ ነው ማለት ነው፡፡ እንደ ቫርናሽራማ ..." ብራህማናውም እንደ ብራህማናነት ሀላፊነቱን እምደሚወጣ ክሻትርያውም እንደ ክሻትርያነቱ ሀላፊነቱን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ለመመርመር ነው፡፡ ይህ ነው የንጉስ ጉብኝት ማለት፡፡ የንጉስ ጉብኝት ማለት በህዝብ ገንዘብ የደስታ ዙረት አይደለም፡፡ በየቦታው ለደስታ ዙሮ መመለስ ማለት አይደለም፡፡ ንጉሱም አንዳንድ ግዜ በድብቅ በመምጣት ይህ የቫርናሽራሙ ሀላፊነት በደንብ በመካሄድ ላይ እንደአለ በመጎብኘት ላይ ይገኝ ነበረ፡፡ ሀብት በትክክል እንደተያዘ እና ሰዎች እንደ ሂፒ ግዜያቸውን በማጥፋት ላይ እንዳሉ እና እንደሌሉ ጉብኝት ያደርግ ነበረ፡፡ ይህም መሆን አይገባዋም፡፡ ይህም መደረግ አይገባውም በማለትም ትዕዛዝ ይሰጥ ነበረ፡፡ አሁን በመንግስታችሁም የፍተሻ ፕሮግራም አለ፡፡ ይህም ሰዎች ሰራ ፈት መሆን አለመሆናቸውን የሚያጠቃልል ነው፡፡ ነገር ግን ብዙ ያልተፈተሹ ነገሮች ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን መንግስት ሁሉን ነገር የመፈተሽ ሀላፊነት አለው፡፡ “ቫርጋሽራማቻራቫታ” ብራህማና ሁሉን የሚጠበቅበትን በተግባር ማዋል ይገባዋል፡፡ በሀሰት ግን ብራህማና መሆን ወይንም በሀሰት ክሻትርያ መሆን አይቻልም፡፡ ሰለዚህ ይህ ነበር የንጉሱ ሀላፊነት ወይንም የመንግስት ሀላፊነት፡፡ በአሁኑ ግዜ ሁሉ ነገር የተገላቢጦሽ ነው፡፡ ሁሉም ነገር ተግባራዊ አስፈላጊነት ያለው ሆኖ አይገኝም፡፡ ሰለዚህ ቼይታንያ መሀፕራብሁ እንዲህ ብሎ ነበር “ከለዉ” ሀሬር ናማ ሀሬር ናማ ሀሬር ናማይቫ ኬቫላም ካላዉ ናስትኤቫ ናስትኤቫ ጋቲር አንያታሀ“ (ቼቻ፡ አዲ 17 21) በአሁኑ ግዜ ወደ ዋነኛው የቀድሞው የስልጣኔው ግዜ ለመመለስ በጣም ያዳግተናል፡፡ ሰለዚህ ለቫይሽናቫ ከዚህ በፊትም እንደአስረዳሁት ”ትሪ ዳሳ ፑር አካሻ ፑስፓያቴ ዱርዳንቴንድሪያ ካላ ሳርፓ ፓታሊ“ ሰለዚህ ስሜቶቻችንን መቆጣጠር ይህ ”ዱርዳንታ“ ይባላል፡፡ ዱርዳንታ ማለት ሀይል ያለው ማለት ነው፡፡ ስሜቶቻችንን ለመቆጣጠር በጣም በጣም አዳጋች ነው፡፡ ሰለዚህም የዮጋ ስርዓት የሚስጢራዊ የዮጋ ስርዓቶች ተደንግገዋል፡፡ እነዚህም እንዴት ስሜቶቻችንን ለመቆጣጠር እንደምንችል የሚረዱ ስርዓቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን ለትሁት አገልጋይ..... ለምሳሌ ምላሳችን የሀሬ ክርሽናን ቅዱስ ስም ለመዘመር እና ለክርሽና በፍቅር የቀረበለትን ምግብ ለመብላት ስንጠቀምበት እንገኛለን፡፡ ይህም የፍፁም ትክክለኛ ዮጊ ተግባር ነው፡፡ ሰለዚህ ትሁት አገልጋይ ወይንም ብሀክታ በስሜቶቹ ምንም ሊረበሽ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ብሀክታ እያንዳንዱን የስሜት አካሎች እንዴት አድርጎ ለአብዩ ጌታ ደስታ እንደሚጠቀምባቸው እውቀቱ አለው፡፡ “ህርሺኬና ህርሺኬሻ ሴቫናም ( ቼቻ፡ ማድህያኧ19 170) ይህም ብሀክቲ ይባላል፡፡ ህርሺካ ማለትም ስሜቶች ማለት ነው፡፡ ስሜቶቻችንም ሁሉ ለህርሺኬሻ ወይንም ክርሽናን ለማገልገል የምንጠቀምባቸው ከሆነ ዮጋን ለመለማመድ የሚያስፈልግ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ስሜቶቻችን ሁሉ በአብዩ ጌታ የፍቅር አገልግሎት ሰለሚቆለፉ ነው፡፡ ሌላ ስራም አይኖራቸውም፡፡ ይህም ከፍተኛ አገልግሎት ነው፡፡ ሰለዚህ ክርሽናም እንዲህ ይላል፡፡ ”ዮጊናም አፒ ሳርቬሻም ማድ ጋቴናንታራትማና ሽራድሃቫን ብሀጃቴ ዮ ማም ሳ ሜ ዩክታታሞ ማታሀ (BG ብጊ፡6 47) ”አንደኛ ደረጃ ዮጊ የሚባለውም እኔን ሁልግዜ የሚያስታውሰኝ ሰው ነው“ ሰለዚህ ይህን የሀሬ ክርሽናን ቅዱስ ስም ሁሌ በመዘመር አንደኛ ደረጃ ዮጊዎች ሊያደርገን ይበቃል፡፡ ሰለዚህ ስርዓቱ ይህ ነው፡፡ ክርሽናም አርጁናን እንዲህ እንዲያደርግ ነው የመከረው፡፡ ”ለምንድነው በዚህ የአእምሮ ድክመት ስትወላውል የምትገኘው?“ አንተ በእኔ እንክብካቤ ስር ነህ፡፡ እኔም እንድትዋጋ እያዘዝኩህ ነው፡፡ ለምንድነው ወደ ኋላ ለመሸሽ የምትፈልገው? ይህ ነው ድምደማው፡፡ በጣም አመሰግናለሁ፡፡