AM/Prabhupada 0252 - እኛ ከሁሉም ነገር ነፃ የሆንን አድረገን እናስብ ይሆናል፡፡



Lecture on BG 2.6 -- London, August 6, 1973

እነዚህ በቁሳዊ ዓለም መንፈስ የተሞሉ ዓለማውያን ሁሉ ሞኝነት ተንኮለኝነት እና ቀጣፊነት የተሞላባቸው ሆነው የዓለማዊ መንፈስ እንቅስቃሴዎችን ሲያስፋፉ ይታያሉ፡፡ የሚያስቡትም ይህንን የመሰለ የዓለማዊ እንቅስቃሴን በማስፋፋት ደስተኞች እንሆናለን ብለው ሰለሚያስቡ ነው፡፡ ይህ ግን አይደለም፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡ “ዱራሳያ ዬ” መሪዎቻቸውም..... "አንድሀ ያትሀንድሄር ኡፓኒያማናስ ቴ ፒሻ ታንትርያም ኡሩ ዳምኒ ባድሀህ“ (ሽብ፡ 7 5 31) በዚህ ዓለም ሁላችንም በጥብቅ የታሰርን ነን፡፡ ይህም እጆቻችን እግሮቻችንም ሳይቀር ነው፡፡ ነገር ግን ነፃ ነን ብለን እናስባለን፡፡ በተፈጥሮ ህግጋት የታሰርን ሆነን በሀሰት ነፃ ነን ብለን እናስባለን፡፡ ሳይንቲስቶች አብዩ አምላክን በምርምራቸው ሊያስወግዱት ሲሞክሩ ይታያሉ፡፡ ይህም የሚቻል አይደለም፡፡ እኛ በዚህ በቁሳዊው ዓለም ህግጋት ተጠምደን እንገኛለን፡፡ ቁሳዊው ዓለም ማለት ደግሞ የክርሽና ተወካይ ማለት ነው፡፡ “ማያ ድህያክሼና ፕራክርቲ ሱያቴ ሳቻራቻራም (ብጊ፡ 9 10) ፕራክርቴ ክሪያማናኒ ጉናይር ካርማኒ ሳርቫሻሀ” (ብጊ፡ 3.27) ሰለዚህ እኛም ልክ እንደ አርጁና ሁሌ በጭንቀት ላይ እንገኛለን፡፡ ምን እንስራ ምን አንስራ? በማለት እንገኛለን፡፡ ነገር ግን ይህንን መመሪያ ብንወስድ “ለክርሽና ማድረግ አለብን” በዚህም ባህርይ ከክርሽና መመሪያ ብንወስድ እንዲሁም ከክርሽና ተወካዮች መመሪያ ብንወስድ እና በተግባር ብናውለው ይህ “ካርማ ባንዳና” (በቁሳዊ ዓለም መተሳሰር) ይጠፋል፡፡ “ካማኒ ኒርዳሄቲ ኪንቱ ቻ ብሀክቲ ብሀጃም (ብሰ፡5 54) አለበለዛ ግን በምናደርገው የዓለማዊ ስራ ሁሉ ተተሳስረን እንገኛለን፡፡ ለመውጣትም በጣም ያዳግተናል፡፡ ሰለዚህ የአርጁና ጭንቀት ”ልዋጋ ወይንስ አልዋጋ“ እንዲህ ሆኖ ሊገለጽ ይቻላል፡፡ ”አዎን ለክርሽና መዋጋት ይኖርብሀል፡፡ ከዚያም ሁሉም ነገር ትክክል ይሆናል“ ”ካማ ክርሽና ካርማርፓኔ“ ልክ እንደ ሀኑማን ለጌታ ራማቻንድራ ተዋጋ፡፡ ለእራሱ ጥቅም ግን አልተዋጋም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የአርጁና ጋሪ በሀኑማን ባንዲራ ያሸበረቀ ነበረ፡፡ ይህንንም ሀላፊነት ይውቀዋል፡፡ ሀኑማን ታላቁ ተዋጊ ከራቫና ጋር ትልቅ ውጊያ አካሂዶ ነበር፡፡ ይህም ለእራሱ ጥቅም አልነበረም፡፡ ዋናው ፍላጎቱ እንዴት ሲታጂን ከራቫና እጅ ፈልቅቆ ለማውጣት እንደሚችል ነበረ፡፡ ጠቅላላ ቤተሰቡንም በመግደል ሀሳቡ ሁሉ እንዴት እንደሚወጣ እና ሲታን አምጥቶ እንዴት ሀጌታው ከራማቻንድራ ጎን እንደሚያስቀምጣት ነበረ፡፡ ይህ ነው የሀኑማን እና የትሁት አገልጋዮች መመሪያ፡፡ የራቫና መመሪያ ደግሞ ”ሲታን ከራማቻንድራ እጅ ነጥቆ ወስዶ እንዴት ሊደሰትባት እንደሚችል ነበረ“ የራቨናም መመሪያ ይኅው ነው፡፡ የሁኑማን መመሪያ ደግሞ ”ሲታን ከራቨና እጅ አጥቶ እንዴት ከጌታው ከራማቻንድራ ጎን ሊያስቀምጣት እንደሚችል ነው፡፡“ ይህችኑ ሲታ፡፡ ሲታ ማለት ”ላክሽሚ“ ማለት ነው፡፡ ላክሽሚ ማለት ደግሞ የናራያና ወይንም የአብዩ የመላእክት ጌታ ሀብት ማለት ነው፡፡ ሰለዚህም መመሪያ በደንብ መረዳት ይገባናል፡፡ እንደ ራቫና የመሳሰሉ ዓለማዊ የሆኑት ሰዎች ሁሉ የአብዩ አምላክን ሀብት በመውሰድ ለእራሳቸው የግል ጥቅም ሊያውሉት ነው ምኞታቸው፡፡ ሰለዚህ እንደምንም ብለን ትሁት አገልጋይ መሆን ይገባናል፡፡ በእርግጥ እንደ ራቫና ከመሳሰሉት ጋራ ለመዋጋት አቅሙም ላይኖረን ይችላል፡፡ ይህም በጣም ጠንካራዎች ሰለአልሆንን ሊሆን ይችላል፡፡ ሰለዚህ ለማኝ የመሆንን መመሪያ ለመውሰድ መርጠናል፡፡ ”ጌታዬ አንተ ጥሩ ሰው ትመስላለህ፡፡ እባክህ አንድ ነገር ስጠን፡፡ አንድ ነገር አበርክትልን“ ይህም የአብዩ ጌታን ሀብት በመውሰድ ሕይወትህን በማበላሸት ላይ ሰለምትገኝ ነው፡፡ ይህንንም በማድረግ ወደ ሲኦል ልትሄድ ትችላለህ፡፡ ”ሰለዚህ በምንም ዓይነት መንገድም ቢሆን የዚህ የበጎ እንቅስቃሴ አባል ብትሆን ልትድን ትችላለህ፡፡“ ይህ ነው የእኛ መመሪያ፡፡ ለማኞች ባንሆንም መመሪያችን ይህ ነው፡፡ በአሁኑ ደረጃ እንደ ራቫና ዓይነቶች ዓለማውያንንን ለመዋጋት አቅሙም ላይኖረን ይችላል፡፡ አለበለዛ የወሰዱትን ሀብት ሁሉ ተዋግተን ለማስመለስ እንችላለን፡፡ ነገን ግን ይህ የሚቻል አይደለም፡፡ ሀይሉም ላይኖረን ይችላል፡፡ ሰለዚህ የለማኝነትን መመሪያ ወስደናል፡፡ እናመሰግናለን፡፡