AM/Prabhupada 0247 - ትክክለኛ ሀይማኖት ማለት አብዩ ፈጣሪ አምላክን መውደድ ማለት ነው፡፡
Lecture on BG 2.9 -- London, August 15, 1973
ብሀገቨድ ጊታ የሚደመድመው በዚህ ጥቅስ ነው፡፡ “ሳርቫ ድሀርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ” (ብጊ፡18 66) ብሀገቨታ ደግሞ ከዚሁ ነጥብ ይጀምራል፡፡ ሰለዚህ ብሀገቨድ ጊታ የሽሪማድ ብሀገቨታም ቀዳማዊ ትምህርት ነው፡፡ ብሀገቨታም የሚጀምረው “ድሀርማ ፕሮጂታ ካይታቫሀ አትራ” በዚህም በሽሪማድ ብሀገቨታም ሁሉም ዓይነት የማታለያ ሀይማኖቶች ተወግዘዋል፡፡ “ፕሮጂታሀ” ሰለዚህ የተያያዙ ናቸው፡፡ ትክክለኛ ሀይማኖት ማለት አብዩ የመላእክት ጌታን መውደድ ማለት ነው፡፡ ይህም ትክክለኛ ሀይማኖት ነው፡፡ ሰለዚህም ብሃገቨታም እንዲህ ይለናል፡፡ “ሳ ቮይ ፑምሳም ፓሮ ድሃርሞ ያቶ ብሀክቲር አድሆክሳጄ” ይህም ማለት ይህንን ወይንም ያንን ሀይማኖት ተከተል ማለት አይደለም፡፡ የተገለገውን ሀይማኖት መከተል ትችላላችሁ፡፡ ለውጥ አይኖረውም፡፡ ሂንዱ ክርስትያን ወይንም እስላም መሆን ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን መፈተን አለ፡፡ ልክ ኤም ኤ ዲግሪውን ተፈትኖ እንደአለፈ ተማሪ፡፡ ማንም ሰው አይጠይቅም፡፡ “ከየት ኮሌጅ ነው የተመረቅኅው?" ማስተርስህን ጨርሰሀልን? በጣም ጥሩ፡፡ ማወቅ የምንሻውም ባችለር ወይንስ ማስተርስ ሰለመያዙ ነው፡፡ ማንም ሰው እንዲህ ብሎ አይጠይቅም፡፡ ”ከየት ኮሌጅ ነው የተመረቅኅው? በየት አገር ነው ተምረህ ማስተርስህን የያዝከው?" በማለት ብዙ ሰው አይጠይቅም፡፡ እንደዚህም ሁሉ ማንም ሰው እንዲህ በማለት መጠየቅ ይገባዋል፡፡ “ምን ዓይነት የሀይማኖት እምነት አለህ?" አንድ ሰው ማየት የሚገባው ግን ይህ ሰው ምን ያህል የአብዩ ጌታን ፍቅር እንዳዳበረ ነው፡፡ ይህ ነው ሀይማኖት ማለት፡፡ ምክንያቱም የሀይማኖት እዚህ ተጠቅሷል፡፡ ”ሳርቫ ድሀርማን ፓቲትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ“ (ብጊ፡18 66) ይህ ሀይማኖት - ብሀገቨታም እንዲህ ይላል “ድሀርሞህ ፕሮጂሂታ ኮይታቫሀ አትራ” የሚያታልሉ ሀይማኖቶች ሁሉ ከብሀገቨታም ተሽቀንጥረው ወጥተዋል፡፡ የቀሩትም “ኒርማትሳራናም” ለአብዩ ጌታ ምቀኝነት የሌላቸው ብቻ ናቸው፡፡ “ለምን ጌታን ማፍቀር አለብኝ? ለምን ለጌታ መስገድ አለብኝ? ለምን ጌታን መቀበል አለብኝ?” የሚሉ ሁሉ ሰይጣናዊ ናቸው፡፡ ሽሪማድ ብሀገቨታም የተፃፈው አብዩ ጌታን በጥሞና በማገልገል ፍቅራቸውን ለማዳበር ለሚሹ ብቻ ነው፡፡ “አሆይቱኪ አፕራቲሃታ ዬናትማ ሳምፕራሲዳቲ” ሰለዚህ የሕይወታችን መሳካት የሚለካው ምን ያህል አብዩ አምላክን ለመውደድ ባደረግነው እርምጃ ነው፡፡ በዚህም እርምጃ ልባችን የረካ የሆናል፡፡ “ያም ላብድህቫ ቻፓናም ላብሀም ማንያቴ ናድሂካም ታታሀ” አብዩ ጌታን ወይንም ክርሽናን ያገኘን ከሆነ.....ክርሽና ማለት አብዩ የመላእክት ጌታ ማለት ነው፡፡ ለአብዩ ጌታ ሌላ ዓይነት ስም ካላችሁ ደግሞ ያም የሚቀበል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጌታን አብዩ ጌታን አብዩ ሰውን ይህንን አብይ ሰው ካላችሁ...... ምክንያቱም አንድ ሰው መውደዳችን አይቀረም፡፡ የመውደድ አዝማሚያችን በተፈጥሮ ያለ ነው፡፡ በሁላችንም ያለ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ የተሳሳተ ነው፡፡ ሰለዚህም ክርሽና እንደዚህ ይላል፡፡ “እነዚህን በሀሰት ይምትወዷቸውን ሁሉ አስወቅዱ እና ያላቸሁን ፍቅር ወደ እኔ አተኩሩ” ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም (ብጊ፡18 66) በዚህ በቁሳዊው ዓለም መንገድ ያላችሁ ፍቅር ፈፅሞ ሊያስደስታችሁ አይችልም፡፡ “ዬናትማ ሳምፕራሲዳቲ” በእርግጡም ለመደሰት ከፈለጋችሁ ክርሽናን ወይንም አብዩ የመላእክት ጌታን ማፍቀር ይገባችኋል፡፡ የቬዲክ ፊሎሶፊ እንደዚህ ብሎ ይደመድማል፡፡ እራሳችንን ለማስደሰት ወይንም አእምሮዋችንን ለማርካት ስንፈልግ ይህም ሊገኝ የሚችለው አብዩ ጌታን ስናፈቅር ብቻ ነው፡፡ ሰለዚህ አብዩ የመላእክት ጌታን እንድናፈቅር የሚያደርገን እና የሚያስተምረን ሀይማኖት በአንደኛ ደረጃነት ተመድቦ ይገኛል፡፡ ይህ ነው በአንደኛ ደረጃ ላይ ተመድቦ የሚታየው ሀይማኖት፡፡ “ሳቮይ ፑምሳም ፓሮ ድሀርሞ ያቶ ብሀክቲህ” (ሽብ፡ 1.2.6) ይህም በፍቅር እንጂ በልባችን ሌላ ምኞት ኑሮ መሆን የለበትም፡፡ ልክ በዚሁ ዓለም እንደምናየው፡፡ “እወድሀለሁ አንተም ትወደኛለህ” ከኋላው ግን የግል ጥቅም ይኖረዋል፡፡ ”አሆይቱኪ አፕረቲሀታ“ አሆይቱኪ ማለት ምንም ፍላጎት የሌለው ማለት ነው፡፡ ”አናብሂላሲታ ሱንያም“ (ብሀክቲ ራሳምርታ ሲንድኁ 1 1 11) ሁሉንም ዓለማዊ ምኞታችንን ሁሉ ዜሮ ማድረግ፡፡ ዜሮ! ይህንንም ከብሀገቨድ ጊታ መማር እንችላለን፡፡