AM/Prabhupada 0318 - ወደ የፀሀዩ ብርሀን ቅረቡ፡፡
Lecture on BG 4.22 -- Bombay, April 11, 1974
ቫይሽናቫ “ማትሳራሀ” አይደለም፡፡ ማትሳራሀ ማለትም... ይህም በሽሪድሀር ስዋሚ ተገልጿል፡፡ ማትሳራ ፓራ ኡትካርሳናም አሳሀናም፡፡ የዚህ ቁሳዊ ዓለም ባህርይ በሌሎች ቀናተኛ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ይህም ምንም እንኳን በሀብት የምንቀናባቸው የገዛ ወንድሞቻችንም ቢሆኑ ነው፡፡ ቅናተኝነት ያድርብናል፡፡ “ወንድሜ በጣም ሀብታም ሆኗል፡፡ እኔ ግን ሀብታም መሆን አልቻልኩም፡፡” ይህም በዚህ ዓለም ላይ ያለ ነው፡፡ ቅናት ይህም ቅናት ከክርሽና የሚጀምር ነው፡፡ “ለምን ክርሽና ብቻ ተደሳች ይሆናል? እኔም እንደ እርሱ ተደሳች መሆን እፈልጋለሁ፡፡” ይህ አይነቱ ቅናት በክርሽና የጀመረ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የመላው የቁሳዊው ዓለም ሕብረተሰብ በዚሁ በቀናተኝነት የተሞላ ነው፡፡ እኔ በአንተ እመቀኛለሁ፡፡ አንተም በእኔ ተመቀኛለህ፡፡ ይህ ነው የዚህ ዓለም ስራ እና ባህርይ፡፡ ሰለዚህ በዚህ ጥቅስ ላይ “ቪማትሳራሀ” ወይንም ቅናት የሌለው ተብሎ ተገልጿል፡፡ አንድ ሰው የክርሽና ትሁት አገልጋይ ካልሆነ እንዴት አድርጎ ከቅናት ነፃ ሊሆን ይችላል? ቀናተኛም መሆኑ አይቀርም፡፡ ይህ ነው ተፈጥሮው፡፡ ሰለዚህም ብሀገቨታም እንዲህ ብሎ ገልጾታል፡፡ “ድሀርማሀ ፕሮጂታሀ ካይታቮ ትራ ፓራሞ ኒርማትሳራናም ቫስታቫም ቫስቱ ቬድያም አትራ” (ሽብ፡ 1.1.2) ድሀርማ... እንደምናየው ብዙ የተለያዩ የሀይማኖት ስርዓቶች በዓለም ላይ አሉ፡፡ ቅናትም በግልጽ ይታያል፡፡ የእንስሶችን አንገት እያረዱ ይህ ሀይማኖት ነው ይላሉን? ለምን? አስተሳሰብህ ሰፋ ብሎ የሚያይ እና አብዩ ጌታ ናራያናን በሁሉም ቦታ የምታየው ከሆነ ለምን የፍየሎችን የላሞችን እና የሌሎች የገር እንስሶችን ጉሮሮ ስታርድ ትገኛለህ? ለእነዚህ እንስሶች ምህረት የለህ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ይህ ምህረታዊነት የአብዩ አምላክ ትሁት አገልጋይ ሳይሆኑ ሊመጣ አይችልም፡፡ “ቪማትሳራሀ” ኒርማትሳራሀ” ሰለዚህ እነዚህ ሀይማኖት የሚባሉ ሁሉ ማትሳራታ ወይንም ቀናተኝነት የተሞላባቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ “ካይታቫ ድሀርማ” ወይንም አስመሳይ እና አታላይ የሀይማኖት ፈለጎች ይባላሉ፡፡ የአብዩ አምላክ ንፁህ መንፈሳዊ ንቃት አስመሳይ ሀይማኖት አይደለም፡፡ ይህም ሰፋ ያለ አመለካከት ያለው ነው፡፡ “ቲቲክሳቫሀ ካሩኒካሀ ሱህርዳሀ ሳርቫ ብሁታናም” (ሽብ፡ 3.25.21) ይህም የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ እንደሚያስተምረን ሁሉም ሰው የሁሉም ጓደኛ እንዲሆን ነው፡፡ በክርሽና ንቃት የዳበረ እንዲህ አይነት አስተሳሰብ ከሌለው ለምን የክርሽና ንቃትን በዓለም ለሁሉም ለማስፋፋት ይቸገራል? ቪማትሳራሀ አንድ ሰው ይህ የክርሽና ንቃት በጣም ደስታን የሚሰጥ እንደመሆኑ መረዳት ይገባዋል፡፡ ይህንንም ንቃት ሁሉም ሰው እንዲደሰትበት ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም ሰው እንዲሳተፍበት ያስፈልጋል፡፡ የክርሽና ንቃት ማለት የአብዩ የመላእክት ጌታ ንቃት ማለት ነው፡፡ የሰው ልጅ ስቃይ ላይ የሚወድቀው ይኅው የአብዩ አምላክ ንቃት ሰለሚጎልበት ነው፡፡ የመከራው ሁሉ መነሻ ይኅው ነው፡፡ ”ክርሽና ባሂርሙክሀ ሃና ብሆጋ ቫንቻ ካሬ ኒካታ ስትሀ ማያ ታሬ ጃፓቲያ ድሀሬ (ፕሬማ ቪቫርታ)“ ይህ ነው ፎርሙላው፡፡ ክርሽና ልክ መርሳት እንደጀመርን ወዲያውኑ ማያ ትኖራለች፡፡ (የቁሳዊ ዓለም ምትሀት) ልክ እንደ ፀሀይ እና እንደ ጥላ፡፡ ሁለቱም አጠገብ በአጠገብ የሚገኙ ናቸው፡፡ በፀሀይ ወገን ካልሆናችሁ እና በጥላው በኩል ከሆናችሁ ጨለማነት ይኖራል፡፡ በጨለማነት ውስጥ መሆን ካልፈለጋችሁ ደግሞ ወደ ብርሀኑ ወይንም ወደ ፀሀይ ያለችበት መሄድ ትችላላችሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የክርሽናን ንቃት የማንቀበል ከሆነ የማያን ንቃት መቀበላችን የግድ ነው፡፡ የማያን ንቃት የማንቀበል ከሆነ ደግሞ የክርሽና ንቃታችንን መቀበል የማይቀር ነው፡፡ እነዚህም ጎን ለጎን የሚሄዱ ናቸው፡፡ የክርሽና ንቃት ማለትም በድንቁርና ጨለማ ውስጥ አለመቀመጥ ማለት ነው፡፡ ”ታማሲ ማ ጅዮቲር ጋማ“ ይህም የቬዲክ ስርዓት መመሪያ ነው፡፡ ”በጨለማ ውስጥ አትሁን፡፡” ይህስ ጨለማ ምንድን ነው? ይህ ጨለማ በገላችን አስተሳሰብ የተመሰረተ ዓለማዊ ኑሮ ነው፡፡