AM/Prabhupada 0319 - ዓብዩ ጌታን ተቀበሉ፡፡ የዓብዩ ጌታም አገልጋይ መሆናችሁን በመረዳት አገልግሉ፡፡
Room Conversation with Sanskrit Professor, other Guests and Disciples -- February 12, 1975, Mexico
እንግዳ፡ ድሀርማ ማለት የሀይማኖት እምነት ወይንም ስራ ማለት ነውን?
ፕራብሁፓድ፡ አይደለም ድሀርማ ሀላፊነት ነው፡፡ ቫርናሽራማ ድሃርማ፡፡ ይህም የቀረ ሆኗል፡፡ ስለዚህም አሁን የቀረው ሀላፊነት በክርሽና ንቃት መዳበር ነው፡፡ ክርሽና እንዲህም ብሏል፡፡ "ሳርቫ ድሀርማን ፓሪትያጅያ" በመጀመሪያም እንዲህ አለ፡፡ "ድሀርማ ሳምስትሀ ፓናርትሀያ" አዎን እንዲህ አለ "ዩጌ ዩጌ ሳምብሀቫሚ" እንዲህ አለ "የሀይማኖትን መመሪያዎች እንደገና ለመመስረት ከዘመን ዘመን ወደ እዚህ ምድር እመጣለሁ፡፡" ከዚያም በመጨረሻ እንዲህ አለ፡፡ "ሳርቫ ድሀርማን ፓሪትያጅያ" ይህም ማለት እነዚህ ድሀርማዎች ወይም ሀይማኖት ተብለው በዚህ አለም የሚካሄዱት ሁሉ በፍጹም እውነት የተመሰረቱ ሰለአልሆኑ ነው፡፡ ሰለዚህም ብሀገቫታ እንዲህ ይላል "ድሀርማህ ፕሮጂታ ካይታቮ ትራ (ሽብ፡ 1.1.2) በዚህም ጥቅስ እንደተጠቀሰው "ሁሉም ዓይነት አስመሳይ ሀይማኖቶች ሁሉ እርግፍ ተደርገው ተወግደዋል፡፡" አስመሳይ ሀይማኖት ማለት ምን ማለት ነው? አስመሳይ... ልክ እንደ ወርቅ፡፡ ወርቅ ማለት ወርቅ ነው፡፡ ታድያ ይህ ወርቅ በሂንዱ ሰው እጅ ቢሆን የሂንዱ ወርቅ ይባላልን? እንደዚሁም ሁሉ ሀይማኖት ማለት ለአብዩ የመላእክት ጌታ መታዘዝ ማለት ነው፡፡ ታድያ የሂንዱ ሀይማኖት የታለ? የክርስቲያን ሀይማኖት የታለ? የእስላም ሀይማኖት የታለ? አብዩ ጌታ በሁሉም ቦታ አለ፡፡ እኛም የእርሱ የትእዛዝ ተከታዮች መሆን አለብን፡፡ ይህም አንድ ሀይማኖት ነው፡፡ ለአብዩ አምላክ ታዛዥ መሆን ማለት ነው፡፡ ለምንድነው ብዙ የተለያዩ ሀይማኖቶች የፈጠሩት? ሂንዱ ሀይማኖት እስላም ሀይማኖት ክርስትያን ሀይማኖት ይህ ሀይማኖት ያ ሀይማኖት... ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የተለያዪ አስመሳይ ሀይማኖቶች ናቸው፡፡ ትክክለኛ ሀይማኖት ማለት ለአብዩ አምላክ መታዘዝ ማለት ነው፡፡ “ድሀርማም ቱ ሳክሳድ ብሀገቫት ፕራኒታም” (ሽብ፡ 6.3.19) ልክ እንደ ሕግ፡፡ የአገር ሕግ በመንግስት የተደነገገ ነው፡፡ ይህም ሕግ የሂንዱ ሕግ የእስላም ሕግ የክርስትያን ሕግ ሊሆን አይችልም፡፡ ሕጉ ለሁሉም አንድ ነው፡፡ ለመንግስት ሕግጋት ታዛዥ መሆን ከሁሉም ይጠበቃል፡፡ ይህ የመንግስት ሕግ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ሀይማኖት ማለት ለአብዩ አምላክ መታዘዝ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ሰለ አብዩ አምላክ መረጃው ከሌለው እውቀቱ ከሌለው ሀይማኖቱ የቱ ላይ ነው? ይህ አስመሳይ ሀይማኖት ይባላል፡፡ ስለዚህም በብሀገቨታም እንዲህ ተብሎ ተገልጿል፡፡ “ድሀርማ ፕሮጂታ ካይታቮ ትራ” (ሽብ፡ 1.1.2) “እነዚህ አስመሳይ ሀይማኖቶች ሁሉ ከዚህ ስነፅሁፍ ተወግደዋል፡፡” ክርሽናም ይህንን ደግሞ ተናግሮታል፡፡ “ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ: (ብጊ፡ 18.66) ”እነዚህን አስመሳይ የሃይማኖት ፈለጎች ሁሉ እርግፍ አድርገህ ተዋቸው፡፡“ ”ለእኔ ሙሉ ልቦናህን ብቻ ስጥ፡፡ ሀይማኖት ማለት ይህ ነው፡፡“ በአስመሳይ ሀይማኖት ውስጥ ሆነን በግምት አብዩ አምላክን ለመረዳት ምን ዋጋ ይኖረዋል? ይህ ሀይማኖት አይባልም፡፡ ይህም እንደ አስመሳይ ሕግ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ሕግ አስመሳይ ሊሆን አይችልም፡፡ ሕግ በመንግስት የተደነገገ እና የተሰጠ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ሀይማኖት ማለት በአብዩ አምላክ የተሰጠ ትእዛዝ ማለት ነው፡፡ ይህ ሀይማኖት ይባላል፡፡ ይህንንም ከተከተልን ሀይማኖታዊ ልንባል እንችላለን፡፡ የማንከተል ከሆነ ግን የሰይጣንን ፈለግ ተከተልን ማለት ነው፡፡ ሁሉን ነገር ቀለል አድረገን ካቀረብነው ሁሉም ሰው በምድር ሊቀበለው ይችላል፡፡ ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ ሁሉን ነገር ቀለል ለማድረግ ነው፡፡ አብዩ አምላክን ተቀበል፡፡ የአንተ ደረጃ የአብዩ አምላክ አገልጋይ መሆኑን ተቀበል፡፡ አብዩ አምላክን በትህትና አገልግል፡፡ ይኅው ነው፡፡ ሶስት ቃላቶች ብቻ፡፡