AM/Prabhupada 0330 - እያንዳዱ ሰው እራሱን መንከባከብ ይገባዋል፡፡

From Vanipedia


እያንዳዱ ሰው እራሱን መንከባከብ ይገባዋል፡፡
- Prabhupāda 0330


Lecture on BG 1.26-27 -- London, July 21, 1973

“በዚህ በቁሳዊ ዓለም ውስጥ ከአደጋ ነፃ ነኝ” ብለን የምናስብ ከሆነ ይህም ማለት በሕብረተሰብ በጓደኞቼ በፍቅር በሀገሬ በፖሎቲቻ እና በመላ ሕብረተሰብ የምንተማነን ከሆነ “አይደለም ይህ መሆን የለበትም” ይህ ሊሆንም አይችልም፡፡ እራሳችሁን መንከባከብ አለባችሁ፡፡ እነዚህ ሕብረተሰብ ፍቅር አገር የአገር ሰው የምትሏቸው ሁሉ ፍፁም የሆነ እርዳታ ሊያቀርቡላችሁ አይችሉም፡፡ ምክንያቱም በማያ ተጠምደን ስለምንገኝ ነው፡፡ “ዳይቪሂ ኤሻ ጉናማዪ ማማ ማያ ዱራትያያ” (ብጊ፡ 7.14)

ፕራክርቴ ክሪያማናኒ ጉናይህ ካርማኒ ሳርቫሻሀ አሀንካራ ቪሙድሀትማ ካርታሃም ኢቲ ማንያቴ“ (ብጊ፡ 3.27) በማያ ወጥመድ ውስጥ ትገኛላችሁ፡፡ ነፃነትም የላቸሁም፡፡ ሌላው ሕብረተሰብም ሁሉ እንደ እናንተ በዚሁ ወጥመድ የተጠመደ ስለሆነ እናንተንም ነፃ ሊያደርጓችሁ አይችሉም፡፡ ይህ የሚቻል አይደለም፡፡ ይህም ከዚህ ቀደም እንደሰጠሁት ምሳሌዎች የመሰላል፡፡ ይህም አይሮፕላንን ለመንዳት እንደመማር ነው፡፡ ተምራችሁም ወደ ሰማይ ላይ መብረር ትችላላችሁ፡፡ በዓየር ላይ አደጋ ከገጠማችሁ ግን ሌላ አይሮፕላን ሊያድናችሁ አይችልም፡፡ በዚህም ምክንያት ሊያከትምላችሁ ይችላል፡፡ ሰለዚህ በጣም ጥሩ የሆነ ፓይለት መሆን ይኖርባችኋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ ሁሉም ሰው በግሉ እራሱን መንከባከብ ያሰፈልገዋል፡፡ እንዴትስ ከዚህ ከማያ ወጥመድ መላቀቅ ይችላል? ይህም የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ነው፡፡ መምህር ሀሳቦች ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡ አቻርያ (በተግባር የሚታስተምር) ሀሳቦች ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡ ”በዚህ መንገድ ልትድን ትችላለህ፡፡“ ነገር ግን ትእዛዙን ተከትለህ ሟሟላት የአንተ ፋንታ ነው በእጅህም ነው፡፡ እነዚህንም የመንፈሳዊ ሀላፊነቶች በትክክል ለመወጣት ከቻልክ ተረፍክ ወይንም ነፃ ወጣህ ማለት ነው፡፡ አለበለዛ ግን ምንም እንኳን አቻርያ ትእዛዙን ቢሰጥህ የማትከተለው ከሆነ እንዴት አድርጎ ሊያድንህ ይችላል፡፡ ሊያድንህ የሚችለው በትእዛዙ ነው፡፡ ይህም የቻለውን ያህል የሰጠህ ትምህርት የተሰጠህ በረከቱ ነው፡፡ ነገር ግን አንተ ይህንን ትምህርት በጥሞና መከታተል አለብህ፡፡ ይህ አይነቱ ችግር ነው አርጁና የገጠመው፡፡ ይህም አጠቃላይ የሆነ ችግር ነው፡፡ ”ዴሀ ፓትያ ካላትራዲሱ“ ”ዴሀ ፓትያ“ ዴሀ ማለት ይህ ገላ ማለት ነው፡፡ ”አፓትያ“ ማለት ደግሞ ልቾች ማለት ነው፡፡ ”ካላትራ“ ማለት ደግሞ ሚስት ማለት ነው፡፡ ዴሀፓትያ ካላትራዲስቭ አትማ ሳይኔስቭ አሳትስቭ (ሽብ፡ 2.1.4) እንዲህ ብለንም እናስባለን፡፡ ”በወታደሮቻችን እንጠበቃለን“ ”ልጆች የልጅ ልጆች አያት የባለቤቴ አባት በባለቤቴ ወንድም ህብረተሰቤ ፍቅር ያላቸው ጓደኞች አሉኝ፡፡“ ብለን እናስባለን፡፡ ሁሉም ሰው እንዲህ በማለት ያሰባል፡፡ ”የአገሬ ሰው ሕብረተሰቤ ፍልስፍናዬ ፖለቲካዬ“ አይደለም፡፡ ምንም ነገር ሊያድናችሁ አይችልም፡፡ ”ዴሀ ፓትያ ካላትራዲሱ አሳትሱ አፒ“ እነዚህ ሁሉ ጊዝያዊ ናቸው፡፡ ይመጣሉ ይሄዳሉ፡፡ ”አሳትሱ አፒ“ ፕራማቶ ታስያ ኒድሀናም ፓሽያን አፒ ፓሽያቲ አንድ ሰው በእነዚህ በሕብረተሰብ በጓደኝነት በፍቅሩ በጣም የሚተማመን ከሆነ ”ፕራማታ“ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ፕራማታ ማለት የቀወሰ ወይንም እብድ ሰው ማለት ነው፡፡ ”ፓሽያን አፒ ታስያ ኒድሀናም“ በትክክል ለማየት አይችልም፡፡ ምንም እንኳን አባቱ ሲሞት ቢያይም በልጅነቴ አባቴ ጠለላውን በመስጠት ይንከባከበኝ ነበረ፡፡ አሁን ግን ከአጠገቤ በመለየቱ ማነው ይህንን ጠለላ ሊሰጠኝ የሚችለው? አባቴ በሕይወት ሳይኖር ጠለላውን ሊሰጠኝ ይችላልን? ማነው ይህንን ጠለላ ሊሰጠኝ የሚችለው? እናቴም ጠለላ ትሰጠኝ ነበረ፡፡ አሁን ይህንን ጠለላ ሊሰጠኝ የሚችለው ማነው? እኔ በቤተሰብ ጠለላ ስር ነበርኩ፡፡ ወንዶች ልጆቼ ሴቶች ልጆቼ ባለቤቴ ከእኔው ጋር ነበሩ፡፡ አሁን ትቻቸዋለሁ ታድያ ማነው ጠለላውን የሚሰጠኝ? በእውነቱ ከሆነ ሁልግዜ ጠለላውን የሚሰጠው ክርሽና ብቻ ነው፡፡ ሕብረተሰቡ ጓደኞቻችን እና ፍቅር ጠለላ ሊሆኑን አይችሉም፡፡ ሁሉም ረጋፊ ናቸው እና ነው፡፡