AM/Prabhupada 0331 - ትክክለኛው ደስታ ማለት ወደ እውነተኛ ቤታችን ወይንም ወደ ዓብዩ ጌታ ቤት መመለስ ማለት ነው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search
Go-previous.png የቀድሞው ገፅ - ቪድዮ 0330
የሚቀጥለው ገፅ - ቪዲዮ 0340 Go-next.png

ትክክለኛው ደስታ ማለት ወደ እውነተኛ ቤታችን ወይንም ወደ ዓብዩ ጌታ ቤት መመለስ ማለት ነው፡፡
- Prabhupāda 0331


Lecture on SB 6.2.16 -- Vrndavana, September 19, 1975

በጠቅላላ አነጋገር በዚህ በቁሳዊ ዓለም የምንገኝ ሁሉ በሀጥያት የተሞላን ነን፡፡ ይህ ነው ድምደማው፡፡ ሁላችንም፡፡ አለበላዛ ይህንን የቁሳዊ ዓለም ገላ አንይዝም ነበረ፡፡ ለምሳሌ ማንም በእስር ቤት ውስጥ ያለ ሰው ወንጀል እንደሰራ የታወቀ ነው፡፡ እያንዳንዳቸውን ለማጥናት አያሰፈልግም፡፡ በእስር ቤት ውስጥ በመሆኑ ብቻ ወንጀል ሰርቶ እንደነበረ መረዳት ትችላላችሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በቁሳዊው ዓለም የሚገኝ ነፍስ ሁሉ እንደወንጀለኛው ይቆጠራል፡፡ ነገር ግን የ ምእስር ቤቱ አስተዳዳሪ እንደ ወንጀለኛ አይቆጠርም፡፡ እንዲህ ብላችሁም መደምደም አትችሉም፡፡ “በእስር ቤት ውስጥ ያሉት ሁሉ ወንጀለኞች ሰለሆኑ አስተዳዳሪዎቹም ወንጀለኞች ናቸው፡፡” ለማለት አትችሉም፡፡ ይህ ከሆነ ስህተት አደረጋችሁ ማለት ነው፡፡ እነዚያ ሀጥያጠኞቹን ሁሉ ወደ አብዩ አምላክ ቤተ መንግስት ሊወስዷቸው የሚጥሩ ሁሉ ወንጀለኞች አይደሉም፡፡ የእነዚህ ትሁት አገልጋዮች ተልእኮ በዚህ ቁሳዊ ዓለም የሚገኙትን ወንጀለኞች ሁሉ ከዚህ ዓለም እስር ቤት ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ ወደ አብዩ አምላክ ቤትም መልሶ ለመውሰድ ነው፡፡ ማሀድ ቪቻላናም ንርናም ግሪሂናም ዲና ቼታሳም ”ግሪሂናም“ ግርሂ ማለት በዚህ ገላ ውስጥ ወይንም በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ የሚኖር ማለት ነው፡፡ የውስን ኑሮ ሲኖሩ ይገኛሉ፡፡ ድህነት የሞላበት ልብም አላቸው፡፡ የሕይወትም ዋጋ እና ጥቅም ምን እንደሆነም አያውቁም፡፡ “ና ቴ ቪዱሁ ስቫርታ ጋቲም ሂ ቪሽኑ” (ሽብ፡ 7.5.31) እነዚህንም ከማስተማር እና ከማንቃት ይልቅ ትልቁ ሰው ማሀት ወይንም መሀትማ በድንቁርና የሚያስቀምጣቸው ከሆነ ይህ ትልቅ አገልግሎትን መንሳት ማለት ነው፡፡ እነዚህ ነፍሳት መንቃት ይገባቸዋል፡፡ የመሀትማዎችም ስራ እነዚህን ነፍሳት መስበክ እና ማንቃት ነው፡፡ “በዚህ በቁሳዊ ዓለም ውስጥ ተጠምዳችሁ አትቅሩ፡፡” “ወደ መንፈሳዊ ዓለምም ኑ፡፡” ይህ ነው የመሀትማ ተልእኮው፡፡ ማሃድ ቺቻላናም ንርናም ግሪሂናም ዲና ቼታሳም እነዚህም ዓለማውያን እውቀታቸው እንደ ድሀ ይቆጠራል፡፡ “ሙድሀ” ሙድሀ እና ዱስክሪቲና ተብለውም በቅዱስ መፃህፍት ተገልፀዋል፡፡ በድንቁርናቸውም ምክንያት እነዚህ ሰዎች ሁሉ ሀጥያት በተሞላበት ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ እንዲህም ትሉ ይሆናል፡፡ “አይደለም እንዴት በድንቁርና ላይ ናቸው ያሉት ትላለህ?” “ ብዙ ዩኒቨርስቲዎች አሉ፡፡ በማስተርስ እና በዶክትሬት በፕሮፌሰርነት እየተመረቁ ነው፡፡ ታድያ እንዴት በድንቁርና ላይ ናቸው ትላለህ?” “አዎን በድንቁርና ላይ ናቸው” “እንዴት?" "ማያያፓህርታ ግያና“ ይህም እውቀት የሚሉት በማያ ሰለተወሰደባቸው ነው፡፡ እውቀቱ ቢኖራቸው ለምን በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ ቀሩ? በእውቀት የዳበረን ከሆንን ማወቅ የሚጠበቅብን ነገር ቢኖር ይህ ቁሳዊ ዓለም የተፈጥሮ ዋነኛው መኖርያችን አለመሆኑን ነው፡፡ ወደ መጣንበት ወደ ዋነኛው ቤታችን ወደ አብዩ አምላክ መመለስ ይኖርብናል፡፡ ሰለዚህ ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበራችን ይህንን እያስተማረ ይገኛል፡፡ ይህ ቁሳዊ ዓለም ዋነኛው መኖርያችን አይደለም፡፡ እዚህም ደስታኛ ለመሆን ጥረት አታድርጉ፡፡ ዱራሳያ ዬ ባሂር አትትሀ ማኒናሀ፡ ባሂር አርትሀ ማኒናሀ፡ ባሂር ማለት የቁሳዊው ዓለም ወይንም የጌታ የውጪው ሀይል ማለት ነው፡፡ ”በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ አንዳንድ ነገሮችን ብናስተካክል“ ብለው ያሰባሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በሳይንሳዊ ሂደት እራሳቸውን ደስተኞች ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ አንዳንዶቹም ደግሞ ወደ ገነት ለመሄድ ጥረት ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ አንዳንዶቹ ይህንን ወይንም ያንን ለመሆን ጥረት ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ያልተረዱት ነገር ቢኖር ግን ትክክለኛው ደስታ የሚገኘው ወደ መጣንበት ቤታችን ወደ አብዩ አምላክ ቤተ መንግስት ስንመለስ ነው፡፡ ና ቴ ቪድሁ ስቫርትሀ ጋቲም ሂ ቪሽኑም (ሽብ፡ 7.5.31) ይህንንም አያውቁም፡፡ ሰለዚህ ይህ እንቅስቃሴያችን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ትምህርት እና መመሪያ እየሰጠ ሰለሚገኝ ነው፡፡ ይህም እንዴት ወደ መጣንበት ቤት ወደ አብዩ አምላክ ቤት እንደምንመለስ ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡