AM/Prabhupada 0366 - እያንዳንዳችሁ ጉሩ “መምህራን” መሆን ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ስሜት የማይሰጥ ነገር እንዳትናገሩ፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

እያንዳንዳችሁ ጉሩ “መምህራን” መሆን ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ስሜት የማይሰጥ ነገር እንዳትናገሩ፡፡
- Prabhupāda 0366


Lecture on SB 6.1.21 -- Honolulu, May 21, 1976

ቼታንያ መሀፕራብሁ እንዲህ ብሎ ተቀብሏል “ክርሽና ቱ ብሀገቫን ስቫያም” (ሽብ፡ 1.3.28) ያሬ ዴክሃ ታሬ ካሃ ክርሽና ኡፓዴሽ“ (ቼቻ፡ማድህያ 7.128) የቼይታንያ መሀፕራብሁ ወይንም ይህ የክርሽና ንቃት ቅስቀሳ... ይህ ቅስቀሳስ ምንድን ነው? እርሱም እንዲህ አለ “እያንዳንዳንችሁ ጉሩ መሆን ይገባችኋል“ ተንኮለኛም ጉሩዎች ሳይሆን ትክክለኛ ጉሩ፡፡ ይህንን ፈልጎ ነበረ፡፡ የዓለም ሕዝብ በጨለማ ውስጥ ሰለሚገኝ በብዙ ሚሊዮን የሚገኙ ጉሩዎች ለማስተማር ያስፈልጋሉ፡፡ ስለዚህም ቼይታንያ መሀፕራብሁ እንዲህ አለ ”እያንዳንዳችሁ ጉሩ ሁኑ“ አማራ አግያ ጉሩ ሆይ ታራ ኤ ዴሽ ወደ ውጪ አገርም መሄድ አያስፈልጋችሁም፡፡ በያላችሁበት እራሳችሁ ጉሩ ሆናችሁ አስተምሩ፡፡ ምንም ችግር የለውም፡፡ “ኤይ ዴሻ” እንዲህ አለ “ኤይዴሻ” ሀይሉ ካላችሁ በየአገሩ በመሄድ ማስተማር ትችላላችሁ ነገር ግን አስፈላጊ አይደለም፡፡ በያላችሁበት ሰፈር በየትኛውም አገር ወይንም ባላችሁበት ከተማ ጉሩ ሆናችሁ ማስተማር ትችላላችሁ፡፡ ይህ የቼይታንያ መሀፕራሁ ሚሽን ነው፡፡ “አማራ አግናያ ጉሩ ሆይ ታራ ኤ ዴሻ” “ ይህ አገር ይህ ቦታ” “ነገር ግን ብቁነቱ የለኝም፡፡ እንዴት ጉሩ ለመሆን እችላለሁ?" ብቁነት አያስፈልግም ”ቢሆንም ጉሩ መሆን እችላለሁን?" አዎን “እንዴት” ያሬ ዴክሃ ታሬ ካሃ ክርሽና ኡፓዴሽ (ቼቻ፡ማድህያ 7.128) “ያገኛችሁትን ሁሉ ክርሽና ምን እንዳለ ትእዛዙን ስጧቸው” “በዚህ መንገድ ጉሩ መሆን ትችላላችሁ፡፡” “ብዙ ሰዎች ጉሩ ለመሆን በጭንቀት ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ ተንኮለኞች ግን ጉሩ እንዴት መሆን እንደሚቻል እውቀቱ የላቸውም፡፡ ይህም ቀላል ነገር ነው፡፡” ብዚ ጉሩዎች ከህንድ አገር ወደ እዚህ አገር ይመጣሉ፡፡ ሁሉም ግን ተንኮለኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ክርሽና ያዘዘውን እና የሰጠውን ሰለማያስተምሩ ነው፡፡ ምናልባት ለመጀመሪያ ግዜ ይህ በክርሽና ንቃት እንቅስቃሴያችን ተጀምሯል፡፡ ከዚህ ሌላ ግን እነዚህ ተንኮለኞች የሚያስተምሩት የተለየ ትምህርት ነው፡፡ የጥልቅ ሀሳብ ልምምድ ወይንም ይህ ወይንም ያ ሁሉም ማታለል ብቻ ነው፡፡ ትክክለኛ ጉሩ ማለት ክርሽና የሰጠውን ትምህርት ማስተማር ማለት ነው፡፡ የራሳችንን ዓይነት ትምህርት መፍጠር አይገባንም፡፡ ይህ መሆን የለበትም፡፡ ይህ የቼይታንያ መሀፕራብሁ ትእዛዝ ነው፡፡ አዲስ ነገር መፍጠር አያስፈልግም፡፡ ትእዛዙ ሁሉ ተሰጥቷል፡፡ እናንተም መድገም ብቻ ነው ያላችሁ፡፡ “ይህ እንዲህ ነው” ይኅው ነው፡፡ ታድያ ይህ የሚያስቸግር ነውን? አባት ለልጁ ”ይህ ማይክራፎን ነው“ ይላል፡፡ ልጅም እንዲህ ማለት ይችላል፡፡ “አባቴ ይህ ማይክራፎን ነው ብሏል” ማለት ይችላል፡፡ በዚህም መንገድ ልጁ ጉሩ ይሆናል፡፡ ባለስልጣኑ አባት እንዲህ አለ “ይህ ማይክራፎን ነው፡፡” አንድ ትንሽ ልጅ “ይህ ማይክራፎን ነው፡፡” ማለት ብቻ ነው የሚችለው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ክርሽና “እኔ አብዩ ጌታ ነኝ” ብሏል “ክርሽና አብዩ ጌታ ነው” ብዬ ብናገር ችግሬ ምኑ ላይ ነው? ይህም ክርሽና የበላይ ስለመሆኑ እስከአላታለልኩኝ ድረስ ነው፡፡ አለበለዛ ግን ማታለል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እውነቱን እንደ አለ ባስቀምጥ “ክርሽና የመላእክት ሁሉ ጌታ ነው” “እርሱም የሁሉም ነገር ባላቤት ነው፡፡ እርሱም እንዲሰገድለት ይገባል፡፡” ብዬ እውነቱን ብናገር ችግሩ ምን ላይ ነው? የእኛም ተልእኮ እዚህ ላይ ነው። እናንተ ወደ ክርሽና ንቃተ ማህበር የመጣችሁ ሁሉ የምንጠይቃችሁ ነገር ቢኖር ይኅው ነው፡፡ እያንዳንዳችሁ ጉሩ ሁኑ ነገር ግን ስሜት የማይሰጥ ነገር አትናገሩ፡፡ ይህንን ነው የምንጠይቃችሁ፡፡ ክርሽና የተናገረውን ብቻ ለመድገም ሞክሩ፡፡ በዚህም መንገድ ብራህማና ትሆናላችሁ፡፡ ጉሩም ለመሆን ትበቃላችሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡