AM/Prabhupada 0370 - እኔ እንደሚሰማኝ ከሆነ ለተደረገው ሁሉ ምስጋናው ለኔ ብዬ አልገምትም፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

እኔ እንደሚሰማኝ ከሆነ ለተደረገው ሁሉ ምስጋናው ለኔ ብዬ አልገምትም፡፡
- Prabhupāda 0370


Conversation with Prof. Kotovsky -- June 22, 1971, Moscow

ማንም ዓይነት ኦርቶዶክስ የሆነ ሂንዱ ሊመጣ ይችላል፡፡ በእኛም የቬዲክ መረጃ መሳሪዎቻችን በእጃችን ይገኛል፡፡ ስለዚህም ማንም ለመቀናቀን ሊመጣ አይችልም፡፡ የክርስቲያን ቀሳውውትም እንኳን ቢሆኑ.... በአሜሪካ የሚገኙት የክርስትያን ቀሳውስቶች አቀራረቤን ወደውታል፡፡ እንዲህም ይላሉ፡፡ “እነዚህ ልጆች የእኛ ልጆች ናቸው፡፡ አሜሪካዊም እና ክርስቲያንም ወይንም ይሁዳዊ ናቸው፡፡” “እንደምናያቸው አሁን አብዩ ጌታን ለማወቅ ቅን ፍላጎት ይታይባቸዋል፡፡ እኛ ልንረዳቸው አልቻልንም ማለት ነውን?" ይህንንም እየተቀበሉት ይታያሉ፡፡ አባቶቻቸው እና ወላጆቻቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፡፡ “እንዲሁም ለጥ በለው እጅ እየነሱ እንዲህ ይላሉ” ”ስዋሚጂ የአንተ በአገራችን መምጣት ትልቅ በረከታዊ ሀብት ነው፡፡ ሰለ አብዩ ጌታም መንፈሳዊ ንቃት እያሰተማርክ ትገኛለህ፡፡“ ከዚህም ባሻገር በሌሎች አገሮችም እንደመጣ በመጋበዝ ላይ እገኛለሁ፡፡ በሕንድ አገርም እንደዚሁ፡፡ የተለያዩ የመንፈሳዊ ድርጅቶች ይህንን የተረጋገጠ እውነት እየመሰከሩ ነው፡፡ ከእኔ በፊት በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ስዋሚዎች ከህንድ መጥተው ነበረ፡፡ ነገር ግን ይህንን የክርሽና ንቃት በመስጠት አንድ ሰው እንኳን ለመቀየር አልቻሉም፡፡ ይህንንም እየመሰከሩ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ለሚታየው ለውጥ ምስጋናው ለእኔ ይገባል ብዬ አላስብም እርግጠኛ የምሆነው ግን ይህንን የቬዲክ እውቀት ሳይቀየር እንደ አለ ሰለአበረከትኩት ያለ ምንም መበረዝ ሰለአስተማርኩት ውጤታማ ሆኗል ብዬ እደመደማለሁ፡፡ ይህ ነው የእኔ አስተዋፅኦ፡፡ ለምሳሌ ትክክለኛው መድሀኒት በእጃችሁ ካለ እና እንደ ትእዛዙ ለበሽተኛው የምትሰጡት ከሆነ በሽተኛው እንደሚድን የታወቀ ነው፡፡