AM/Prabhupada 0462 - "ቫይሽናቫ አፐራድ" ማለት ለቫይሽናቭ አክብሮት የሌለው ደፋር ማለት ነው፡፡
Lecture on SB 7.9.7 -- Mayapur, February 27, 1977
ፕራብሁፓድ፡ ቫይሽናቫን መተንኮል ትልቅ ነውር ነው፡፡ አምባሪሽ መሀራጅ ትሁት የጌታ አገልጋይ ነበረ፡፡ ዱርቫሳ የተባለው ባህታዊ ደግሞ በነበረው የዮጋ ሀይል በጣም የኮራ ነበረ፡፡ አምባሪሽ መሀራጅንም አንድ ግዜ ተነኮለው፡፡ ክርሽናም በሱዳርሻን ቻክራ መቅጫ መሳሪያው ቀጥቶት ነበረ፡፡ ይህም ባህታዊ ከብዙ ሀይል ካላቸው መላእክቶች እርዳታ ፈልጎ ነበር፡፡ እነዚህም እንደ ብራብማ ቪሽኑ የመሳሰሉትን ነው፡፡ በነበረው ሀይልም በቀጥታ ወደ ቪሽኑሎካ ፕላኔት የመሄድ ሀይል ነበረው፡፡ ነገር ግን ምህረት አልተደረገለትም፡፡ በመጨረሻም ወደ ቫይሽናቫው ወደ አምባሪሽ መሀራጅ መጥቶ እግር ላይ በመውደቅ ይቅርታ ጠየቀ፡፡ እርሱም ቫይሽናቭ እንደመሆኑ ወዲያውኑ ይቅርታ አደረገለት፡፡ ስለዚህም ይህ የቫይሽናቫ አፐራዳ (መተንኮል) ትልቅ ነውር ነው፡፡ "ሀቲ ማታ" ሰለዚህም ቫይሽናቭ አፐራድ በጣም መጠንቀቅ አለብን፡፡ አርቼ ቪሽኑ ሺላ ድሂር ጉሩሱ ናራ ማቲር ቫይሽናቫ ጃቲ ቡድሂህ (ፓድማ ፑራና) የቫይሽናቫ ጃቲ ቡድሂህ እራሱ ሌላ ዓይነት ትልቅ ተንኮለኝነት ነው፡፡ እንደዚህም ሁሉ ጉሩን እንደ ተራ ሰው አድርጎ ማየት እራሱ ሌላ ነውር የሆነ ተንኮለኝነት ነው፡፡ የሚሰገድላቸውን ሙርቲዎችም እንደ ብረት ድንጋይ አድርጐ ማየትም ሌላ ነውር የሆነ ተንኮለኝነት ነው፡፡ "ሳ ናካሪ" ሰለዚህም በጣም መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ ይህም በሚሰጠን መመሪያዎች እና የቫይሽናቫዎችንም የእግር ፈለግ መከተል ይገባናል፡፡ "ማሃጃኖ ዬና ሳ ጋታሀ" ፕራህላድ መሀራጅ ተራ ሰው ነው ብላችሁ እንዳታስቡ፡፡ ከፕራህላድ መሀራጅም እንዴት አድርገን በትሁት አገልግሎታችን እንደምንገፋ መማር ይኖርብናል፡፡ እናመሰግናለን፡፡
አገልጋዮች፡ ጃያ ፕራብሁፓድ