AM/Prabhupada 0492 - የቡድሀ ፊሎሶፊ ማለት ይህንን ገላ መገነጣጠል ማለት ነው፡፡ "ኒርቫና"



Lecture on BG 2.14 -- Germany, June 21, 1974

ይህ ገላ ምንድን ነው? ይህ ገላ የቁሳዊ ንጥረ ነገሮች ክምችት ነው፡፡ ይህም የአፈር ውሀ አየር እሳት ሰማይ ሀሳብ አእምሮ እና ኢጎ ስምንት ዓይነት ቁሳዊ ነገሮች አሉ 5 ጎላ ያሉ እና 3 ድብቅ የሆኑ ናቸው፡፡ ይህም ገላ በእነዚህ ሁሉ የተገነባ ነው፡፡ የቡድሀ ፍልስፍና ይህንን ገላ ገነጣጥለው ነው "ኒርቫና" ለምሳሌ ይህ ቤት በድንጋይ በሸክላ በእንጨት እና በተለያዩ ቁሳቁሶች የተሰራ ነው፡፡ ይህንንም ቤት ብታደቁት የሚተርፍ ድንጋይ እና ሸክላ አይኖርም፡፡ ይህም ወደ መሬት ሁሉም ነገር ይደባለቃል፡፡ ወደ መሬት ስትደባልቁት ቤት ተብሎ የነበረው ሁሉ ይጠፋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ዜሮ ከሆንን ከማናቸውም ይሚያም እና የሚያስደስት ነገር ሁሉ ነፃ እንሆናለን፡፡ ይህ ነው የቡዲስቶች ፍልስፍና፡፡ ኒርቫና ፍልስፍና፡፡ "ሱንያቫዲ" ሁሉን ዜሮ አድረገው፡፡ ይህ ግን የሚቻል አይደለም፡፡ ይህ ሊደረግ አይችልም፡፡ ምክንያቱም እኛ መንፈስ ነን፡፡ ይህም ይገለፃል፡፡ እኛ ዘለዓለማዊ ነን፡፡ ዜሮ ልንሆን አንችልም፡፡ ይህም እንዲህ ተገልጿል፡፡ "ና ሀንያቴ ሃንያማኔ ሻሪሬ" (ብጊ፡ 2.20) ይህንን ገላ ልክ እርግፍ አድርገን ስንሄድ ወዲያውኑ ሌላ ገላ ውስጥ እንገባለን፡፡ ታድያ ይህ ገላን መገነጣጠል የሚባል ነገር የት አለ? በተፈጥሮ አቀነባበር ሌላ ገላ ታገኛለህ፡፡ የቁሳዊ ዓለምንም ደስታ ለማግኘት ሰለፈለግህ በዚህ ዓለም ላይ ለመወለድ መጥተሀል፡፡ መጠየቅም አያስፈልግም፡፡ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ “እኔ በዚህ ዓለም ላይ እገኛለሁ፡፡ እዚህም እያለሁ ሙሉ በሙሉ ለመደሰት መሞከር ይገባኛል፡፡” አንድ ሰው ግን ከዚህ ሕይወት ባሻገር ሌላ ሕይወት እንዳለ የማያውቅ ካለ እንዲህ ብሎ ማሰብ ይጀምራል፡፡ “ይህ ገላ የቁሳዊ ነገሮች ማለትም የአፈር የውሀ የአየር የእሳት ክምችት ነው፡፡” ገላውም ሲበላሽ ሁሉም ነገር ሊቆም ይችላል፡፡ ”ሰለዚህ ይኅው እድል እስከአለኝ ድረስ ሙሉ በሙሉ መደሰት ይገባኛል“ በማለት ያስባል፡፡ ይህም የቁሳዊ ዓለም አስተሳሰብ ይባላል፡፡ ከሀዲያን እነዚህም ከሀድያን ነፍስ ዘለዓለማዊ እንደሆነች አያውቁም፡፡ ገላችንንም ብቻ እንደምንቀይር ነው የሚያውቁት፡፡ ከሀዲያኖችም እንዲህ ያስባሉ .....በዚህም በአውሮፕያን አገር ውስጥ ትላልቅ ፕሮፌሰሮች አሉ፡፡ እነርሱም ራሳቸው በዚህ አይነት ድንቁርና ውስጥ ናቸው፡፡ ቁሳዊ ገላችንም ሲያከትምለት እነርሱም እራሳቸው የሚጠፉ ይመስላቸዋል፡፡ ይህም ትክክል አይደለም፡፡ ሰለዚህ ይኀው እራሱ የትእዛዞች ሁሉ መጀመሪያ ነው፡፡ ዴሂኖ ስሚን ያትሀ ዴሄ ኮማራም ዮቫናም ጃራ (ብጊ፡ 2.13) የተለያየን ገላ እየቀያየርን እንገኛለን፡፡ ገላውንም በመጨረስህ አንተም ተጨረስክ ማለት አይደለም፡፡