AM/Prabhupada 0503 - ጉሩን ወይንም መንፈሳዊ መምህርን መቀበል ማለት ስለ ፍፁም እውነት መጠየቅ እና መረዳት ማለት ነው፡፡



Lecture on BG 2.15 -- Hyderabad, November 21, 1972

የሽሪማድ ብሀገቨታም ገለፃ “ቬዳንታ ሱትራ” ተብሎ ይታወቃል፡፡ ጂቫስያ ታትቫ ጂግናሳ ጂቫስያ ታትቫ ጂግናሳ ይህ ሕይወታችን ነው፡፡ ጂቫስያ የሁሉም ፍጥረታት፡፡ የሁሉም ፍጥረታት ማለትም በተለይ የሰው ልጅ ዘር ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ደመቶች እና ውሾች ሰለ ብራህማን ወይም ሰለ ፍፁም እውነት ለመጠየቅ አይችሉም፡፡ ስለዚህ መደምደም የምንችለው የሰው ልጅ ሕይወት እንደ እንስሳ በመሰለ ኑሮ መባከን አይገባውም። ይህም ግዜን ማባከን ይሆናል፡፡ ስለ ፍፁም እውነትም መጠየቅ ይገባዋል፡፡ “አትሀቶ ብራማ ጂግናስያ” ይህንንም ለመረዳት መሞከር ይገባዋል፡፡ “ታድ ቪድሂ ታትቫ ዳርሺብሂህ” ይህም ከ“ታትቫ ዳርሺ” መሆን አለበት፡፡ ”ግያኒናህ ታትቫ ዳርሺናህ“ ቃላቶቹ እነዚህ ናቸው፡፡ በሰው ልጅ ህብረተሰብ እንደምናየው ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ወይንም ወደ ኮሌጅ ለትምህርት ሲሄዱ እናያለን፡፡ እንደዚህም ሁሉ ለመንፈሳዊ ትምህርት “ታድ ቪጅያናርትሀም ሳ ጉሩም ኤቫ አብሂጋቼት (ሙኡ 1 2 12) አብሂጋቼት ማለትም አንድ ሰው ወደ መንፈሳዊ ትምህርት መዞር ይገባዋል ማለት ነው፡፡ ሌላም ምርጫ የለም። አንድ ሰው "መሄድ አልችል ይሆናል” ለማለት አይችልም፡፡ ለመንፈሳዊ ትምህርት የማትሄዱ ከሆነ በቀላሉ ልትታለሉ ትችላላችሁ፡፡ የእኛ የቫይሽናቫ ስርዓት ይኅው ነው፡፡ “አዶ ጉርቫሽራያም” በመጀመሪያ ደረጃ አንድ እውቅና እና ስልጣን ያለውን መንፈሳዊ አባት ጠለላ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ “አዶ ጉርቫሽራያም ሳድ ድሀርማ ፕርቻ” እወስዳለሁ ማለት ብቻ አይበቃም፡፡ “ጉሩ እወስዳለሁ፡፡ ከዚያም ስራዬ አልቋል፡፡ ምክንያቱም ጉሩ አለኝ፡፡” አይደለም፡፡ “ታትቫ ጂግናስያ ታትቫ ጂግናሳ” ጉሩን መቀበል ማለት ከጉሩ ስለ መንፈሳዊ ርእሶች እና ስለ ፍፁም እውነት መጠየቅ ማለት ነው፡፡ “ጂግናሱ ሽሬያ ኡታማም” የቬዲክ መመሪያዎች እነዚህ ናቸው፡፡ አንድ ሰው ጂግናሱ ነው ማለት የሚጠይቅ ነው ማለት ነው፡፡ ”ጂግናሱ ሽሬያ ኡታማም“ ሽሬያህ ማለት ጠቃሚ ማለት ነው፡፡ “ኡታማም” ማለት ደግሞ የበላይ ወይንም ዋና ጠቃሚ ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ስለ ሕይወት ዋናው ጠቃሚ ነገሮች የሚጠይቅ ማለት ነው፡፡ ለእርሱም ጉሩን መቀበል ያስፈልገዋል፡፡ ታስማድ ጉሩም ፕራፓድዬታ ጂግናሱህ ሽሬያ ኡታማም ሻብዴ ፓሬ ቻ ኒስናታም ብራህማኒ ኡፓሻማሽራያም (ሽብ፡ 11.3.21)

ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴያችን ነው፡፡ ሰዎች የሕይወትን ዋና ጥቅም በትክክል እንዲረዱ ጥረት እያደረግን ነው፡፡ በተለይም የመንፈሳዊ ሕይወት ጥቅምና የብሀገቫታ ልዩ ጥቅምን "ድሀርማን ብሀገቨታ ኢሀ" ይህም የመንፈሳዊ ሕይወትን መትክክል በመረዳት ይመጣል፡፡ የእራሳችንንም መሰረታዊ ደረጃ ምን እንደሆነ በመረዳት በንቃታችን የዳበርን ልንሆን እንችላለን፡፡ መረዳት የሚገባንም የሕይወት ዓላማ ምን እንደሆነ የሕይወት ዋናው ሀለፊነታችን ምንድነው የሕይወትስ ትርጉሙ ምንድነው? ይህም የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡ ሀሬ ክርሽና