AM/Prabhupada 0534 - ሽሪ ክርሽና በአርቲፊሻል መንገድ ለማየት አትሞክሩ፡፡
Radhastami, Srimati Radharani's Appearance Day -- London, August 29, 1971
ፕራብሁፓድ፡ የጐስዋሚዎችን የእግር ፈለግ መከተል አለብን፡፡ ይህም እንዴት ክርሽናን ራድሀራኒን እና ቭርንዳቨንን ልናገኝ እንደምንችል ወይንም በልባችን ውስጥ እንዴት እንደምናገኛቸው ነው፡፡ የቼይታንያ መሀፕራብሁ የብሀጃን ስርዓት እንደዚህ ነበረ፡፡ ጥልቅ ናፍቆት መሰማት ”ቪፕራላምብሀ ቪፕራላብሀ ሴቫ“ ልክ እንደ ቼይታንያ መሀፕራብሁ ይሰማው እንደነበረው የክርሽና ጥልቅ ናፍቆት፡፡ በዚህም ናፍቆት በባህር ላይ ይወድቅ ነበር፡፡ በእኩለ ለሊት ከአረፈበትም ክፍል ወይንም ከመኝታ ቤቱ እየወጣ ይሄድ ነበረ፡፡ የሚሄድበትን ማንም ሰው አያውቅም ነበረ፡፡ ይህም ክርሽናን ፍላጋ ሂዶ ወጥቶ ሰለነበረ ነው፡፡ ይህም አይነት የትሁት አገልግሎት ስርዓት በቼታንያ መሀፕራብሁ ትምህርት ተሰጥቶን ነበረ፡፡ እንዲህም በቀላሉ ማለት አይደለም፡፡ ”ክርሽናን እና ራድሀራኒን በራሳ ሊላ ዓይተናቸው ነበረ፡፡“ እንዲህ ማለት ብቻ አይደለም፡፡ ጥልቅ ናፍቆት እንዲሰማን ያስፈልጋል። የክርሽናም ጥልቅ ናፍቆት በተከሰተም ቁጥር በመንፈሳዊ ንቃታችን እርምጃ እየወሰድን ነው ማለት ነው፡፡ ክርሽናንም አርተፊሻሊ ለማየት አትሞክሩ፡፡ በጥልቅ የናፍቆት ስሜት የዳበራችሁ ሁኑ፡፡ ከዚያም ሁሉም ነገር ትክክል ይሆናል፡፡ የጌታ ቼታንያ ትምህርትም እንዲህ ነበረ፡፡ ምክንያቱም በዚህ በቁሳዊ ዓለም ዓይናችን ክርሽናን ለማየት አንችልም፡፡ አታህ ሽሪ ክርሽና ናማዲ ና ብሀቬድ ግራህያም ኢንድሪዬህ (ቼቻ ማድህያ 17.136) በዚህ በዓለማዊ ስሜቶቻችን ክርሽናን ለማየት አንችልም፡፡ የክርሽናን ቅዱስ ስምም ለማዳመጥ አንችልም፡፡ ነገር ግን ”ሴቮን ሙክሄ ሂ ጂቫዶ“ በክርሽና የትሁት አገልግሎት ስንሰማራ ግን ክርሽናን ማየት እና ቅዱስ ስሙን ማጣጣም እንችላለን፡፡ ይህስ ትሁት አገልግሎት የሚጀምረው ከየት ነው? ይህም ትሁት አገልግሎት የሚጀምረው ከምላሳችን ነው፡፡ ከእግር ከዓይን ከጆሮ ሳይሆን ከምላስ ነው፡፡ ሴቮን ሙክሄ ሂ ጂቫዶ ይህንንም አገልግሎት ከምላሳችሁ ከጀመራችሁ ይህስ እንዴት ነው? ምላሳችሁን በመጠቀም የክርሽናን ቅዱስ ስም ሀሬ ክርሽናን ዘምሩ፡፡ ሀሬ ክርሽና ሀሬ ክርሽና ክርሽና ክርሽና ሀሬ ሀሬ ሀሬ ራማ ሀሬ ራማ ራማ ራማ ሀሬ ሀሬ የክርሽናንም ፕራሳድ ተመገቡ፡፡ በዚህም ስርዓት ይህ ምላስ ቡለት ስራ አለው፡፡ ይህም ቅዱስ ስምን ሀሬ ክርሽናን በመዘመር እና ቅዱስ ምግብ ፕራሳዳምን በማጣጣም ነው፡፡ በዚህም ስርዓት ክርሽናን ለመረዳት ትችላላችሁ፡፡
አገልጋዮች፡ ሀሪ ቦል!
ፕራብሁፓድ፡ ክርሽናን ለማየት አትሞክሩ፡፡ ክርሽናን በዚህ በቁሳዊ ዓይናችሁ ለማየት አትችሉም፡፡ በዓለማዊ የመስማት ስሜታችሁም ልትሰሙት አትችሉም፡፡ ልትነኩትም አትችሉም፡፡ ነገር ግን ምላሳችሁን በአብዩ ጌታ አገልግሎት ብታሰማሩ በዚያን ግዜ ክርሽና እራሱ ሊገለጽላችሁ ይችላል፡፡ “እዚህ ነኝ” ይህ አስፈላጊ ነው፡፡ ሰለዚህ የክርሽና ናፍቆት ይኑራችሁ፡፡ ልክ እንደ ራድሀራኒ እና ልክ ጌታ ቼይታንያ እንዳስተማረን፡፡ ምላሳችሁንም በአብዩ ጌታ አሰማሩት፡፡ ከዚያም አንድ ቀን የመንፈሳዊ አንደበታችሁ ሲዳብር ክርሽናን ዓይን ለዓይን ለማየት ትችላላችሁ፡፡ እናመሰግናለን፡፡