AM/Prabhupada 0543 - ጉሩ ወይንም ታላቅ መምህር እራሳችሁን ለማስመሰል አትሞክሩ፡፡
Janmastami Lord Sri Krsna's Appearance Day Lecture -- London, August 21, 1973
ቼታንያ መሀፕራብሁ እንዲህ አለ፡፡ ”ያሬ ዴክሀ ታሬ ካሃ ክርሽና ኡፓዴሽ“ (ቼቻ ማድህያ 7.128) ስለዚህ የምጠይቃችሁ ነገር ቢኖር የቼይታንያ መሀፕራብሁን ትእዛዝ ተከተሉ፡፡ እናንተም በየቤታችሁ ጉሩ (መንፈሳዊ መምህር) ሁኑ፡፡ ጉሩ ለመሆን የትልቅ አቀራረብ የግድ ያስፈልጋልችኋል ማለት አይደለም፡፡ አባት ጉሩ መሆነ አለበት፡፡ እናትም ጉሩ መሆን አለባት፡፡ እንዲያውም በሻሽትራ ቅዱስ መፃህፍት) ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተፅፏል፡፡ ወላጆች ለልጆቹ ጉሩ ለመሆን ካልቻሉ አባት ወይንም እናት መሆን አይገባቸውም፡፡ ”ና ሞቻዬድ ያሀ ሳሙፔታ ምርትዩም“ አንድ ሰው ልጁን ከመወለድ እና ከመሞት ወጥመድ ሊያድነው የማይችል ከሆነ አባት መሆን አይገባውም፡፡ ይህ ትክክለኛ የመውለጃ መቆጣጠሪያ ነው፡፡ ልክ እንደ ውሻ እና ድመት በወሲብ ላይ ተሰማርቶ ልጅ ከተወለደ በኋላ መግደል ወይንም ማስወረድ ይህ ትልቅ ሀጥያት ነው፡፡ ትክክለኛው የመውለድ መቆጣጠርያ እንዲህ ነው፡፡ ልጅህን ከትውልድ እና ከመሞት ወጥመድ ልታድነው የማትችል ከሆነ አባት መሆን አይገባህም፡፡ ይህ የሚያስፈልግ እውቀት ነው፡፡ ፒታ ና ሳ ስያጅ ጃናኒ ና ሳ ስያት ጉሩ ና ሳ ስያት ና ሞቻዬድ ያሀ ሳሙፔታ ምርትዩም፡፡ ልጆቻችሁን ከትውልድ እና ሞት ወጥመድ ልታድኗቸው የማትችሉ ከሆነ ወላጅ አትሁኑ፡፡ ጠቅላላ የቬዲክ ስነፅሁፎችም የሚያስተምሩት ይህንኑ ነው፡፡ ”ፑናር ጃንማ ጃያያሀ“ ምክንያቱም ሰዎች እንዴት የሚመጣውን መወለድ ወይንም የቁሳዊ አካል ይዞ መምጣትን እንደሚያስወግዱ እውቀቱ የላቸውም፡፡ እነዚህም በሞኝነት የተጠቁ ሰዎች ይህንን የቬዲክ ባህል ረስተውታል፡፡ የቬዲክ ባህል ምን እንደሆነ ዘንግተውታል፡፡ የቬዲክ ባህል ማለት የሚመጣውን የቁሳዊ አካል ትውልድ እንደምናስወግድ የሚያስተምረን ባህል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ለሚቀጥለው ሕይወት ትውልድ እንዳለ አያምኑም፡፡ ወደ 91 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ሀቬዲክ ባህል መመሪያዎች ወደ ታች ወድቀው ይገኛሉ፡፡ በብሀገቨድ ጊታም ይኅው ፍልስፍና ተገልጾ ይገኛል፡፡ ትያክትቫ ዴሀም ፑናር ጃንማ ናይቲ ማም ኢቲ ኮንቴያ (ብጊ፡ 4.9) የቬዲክ ባህል ማለት ይኅው ነው፡፡ የቬዲክ ባህል ማለት በኢቮሉሽን ስርዓት ወደ እዚህ ወደ ሰው ሕይወት ላይ ደርሰናል፡፡ የሰው ልጅ የመሆን እድል ስናገኝም ይህንንም የነፍስ ከአንድ ቁሳዊ ገላ ወደ ሌላ ቁሳዊ ገላ የመዘዋወርን መከራ ለማቆም እንችላለን ማለት ነው፡፡ “ታትሀ ዴሀንታራ ፕራፕቲር” በሚቀጥለው ትውልዴ ምን ዓይነት ገላ እንደማገኝ አላውቅም፡፡ የሚቀጥለው የትውልድ ገላዬ ጠቅላይ ሚኒስቴር ለመሆን የሚችል ገላ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይንም በተፈጥሮ ሕግጋት መሰረት ውሻ ሆኜ ልወለድ እችል ይሆናል፡፡ ፕራክርቴ ክሪያማናኒ ጉናይህ ካርማኒ ሳርቫሻሀ አሀንካራ ቪሙድሀትማ ካርታሃም ኢቲ ማንያቴ (ብጊ፡ 3.27)
ይህንንም አያውቁትም፡፡ ባህሉንም ረስተውታል፡፡ ይህንንም የሰው ልጅ ትውልድ ያለ አግባብ ሲጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ ይህም ልክ እንደ እንስሶች በመብላት በመተኛት በወሲብ እና በመከላከል ጊዜያቸውን ሲያባክኑ ይታያሉ፡፡ ይህም የሰው ልጅ ስልጣኔ አይደለም፡፡ ስልጣኔው እንዲህ መሆን አለበት፡፡ “ፑናር ጃንማ ጃያያህ” እንዴት የሚቀጥለውን የቁሳዊ ዓለም ትውልድ እንደምናሸንፍ ነው፡፡ ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበራችን እንቅስቃሴ የሚያስተምረው ነው፡፡ ሰለዚህም እኛ ብዙ መጻህፍቶችን እያቀረብን እንገኛለን፡፡ እነዚህም መጻህፍቶች በመላ ዓለም ተቀባይነትን ያገኙ ናቸው፡፡ በተለይ በትምህርት አዋቂዎች፡፡ ስለዚህ ይህን እንቅስቃሴ ተሳተፉበት፡፡ በዚህም ከተማ ቅርንጫፍ ለመክፈት የትሁት ሙከራ አድረገናል፡፡ ማንም ሰው ምቀኝነት እንዲኖረው አያስፈልግም፡፡ ትሁት መንፈሳችሁን አቅርቡልን፡፡ ይህም የእኛ የትሁት ሙከራችን ነው፡፡ እናንተም ይህንን እድል ተጠቀሙበት፡፡ የምንጠይቃችሁም ይህንን ብቻ ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡