AM/Prabhupada 0587 - እያንዳንዳችን መንፈሳዊ ለመሆን የተራብን ነን፡፡



Lecture on BG 2.20 -- Hyderabad, November 25, 1972

እኔ ይህ የለበስኩት ኮት ነኝ ብዬ ባስብ ድንቁርናዬን ብቻ ነው የሚያመለክተው፡፡ ይህም እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ይህም የሰው ልጅ በጐ ተግባር የምንለውም ይህንኑ ኮትን የማጠብ ስራ ነው፡፡ ለምሳሌ ረሀብ ቢሰማችሁ እና እኔም ኮታችሁን በደንብ አድርጌ በሳሙና ባጥብላችሁ ከረሀብ ልትረኩ ትችላላችሁን? አትችሉም፡፡ ይህም ያማይቻል ነው፡፡ እንደዚህም ሁሉ ሁላችንም በመንፈሳዊ ረሀብ የተጠቃን ነን፡፡ እነዚህስ ሰዎች ኮት እና ሸሚዝን በማጠብ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? በዚህ ሰላም ሊኖር አይችልም፡፡ ይህም የሰው ልጅ በጐ አድራጐትም ሁሉ ልብስ እንደማጠብ “ቫሳምሲ ጂርናኒ” ይባላል፡፡ ይኅው ነው፡፡ ሞት ማለት ደግሞ በመፅሀፉ ተገልጿል፡፡ ይኅው ልብሳችን (ገላ) የአንተ ልብስ የእኔ ልብስ ሲያረጅ መቀየር እንገደዳለን። እንደዚህም ሁሉ መወለድ እና መሞት ማለት ልብሳችንን መቀየር ብቻ ነው፡፡ ይህም በግልፅ ተተንትኖ ተገልጿል፡፡ “ቫሳምሲ ጂርናኒ ያትሀ ቪሀያ (ብጊ፡ 2.22) ጂርናኒ ማለት ያረጀ ልብስ ማለት ነው፡፡ ይህም ተጥሎ ሌላ አዲስ ልብስ ይወሰዳል፡፡ እንደዚህም ሁሉ “ቫሳምሲ ጂርናኒ ያትሀ ቪሀያ ናቫኒ ግርህናኒ” አዲስ እና ንፁህ ልብስ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኔ በእርጅና ላይ እያለሁ ከዚህ ቁሳዊ ዓለም ነፃ ካልወጣሁ እና በዚህም ቁሳዊ ዓለም ብዙ ያልተፈፀሙ ፍላጎቶች ካሉኝ ውጤቱ እንደገና መወለድ እና ሌላ ገላ ይዤ ማደግ አለብኝ፡፡ ነገር ግን ወደ እዚህ ቁሳዊ ዓለም እንደገና ለመመለስ ምንም ፍላጎት ከሌለኝ ”ኒስኪንችና“ ይህ ”ኒስኪንችና“ ይባላል፡፡ ኒስኪንቻናስያ ብሀጋቫድ ብሀጃኖን ሙክሀስያ ቼይታንያ መሀ ፕራብሁ እንዲህ ይላል፡፡ ”ኒስኪንቻና“ አንድ ሰው ከቁሳዊ ዓለም ምኞቶች ነፃ መሆን አለበት፡፡ ከዚህም ቁሳዊ ዓለም ምኞቶች ሁሉ ነፃ መሆን አለበት፡፡ ወደ ቁሳዊ ዓለም መመለስን መፀየፍ አለበት፡፡ በዚህም ነፃ የሆነ አስተሳሰብ ወደ መንፈሳዊ ዓለም የመሸጋገሩ ዕድል ይኖራል፡፡