AM/Prabhupada 0588 - የፈለጋችሁትን ነገር በሙሉ ክርሽና ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡

From Vanipedia


የፈለጋችሁትን ነገር በሙሉ ክርሽና ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡
- Prabhupāda 0588


Lecture on BG 2.20 -- Hyderabad, November 25, 1972

አንድ ሰው የትንሽ ቅንጣፊ ያህል እንኳን የቁሳዊ ዓለም ምኞት ካለው "ልክ እንደ ጌታ ብራህማ ብሆን ወይንም ንጉስ ብሆን ልክ እንደ ጃዋሃርላል ኔህሩ" በዚህም ፍላጎት ምክንያት እንደገና ቁሳዊ ገላ ይዘን እንድወለድ ያስገድደናል፡፡ በዚህም ፍላጎት ብቻ ክርሽና የተመጣጠነ ውሳኔ ያደርጋል፡፡ ይህም በሩህሩህነቱ ነው፡፡ የወደደነውን ነገር ሁሉ ክርሽና ይሰጠናል፡፡ "ዬ ያትሀ ማም ፕራፓድያንቴ" (ብጊ፡ 4.11) ክርሽና ይሰጠናል፡፡ ከክርሽናም መውሰድ... ለምሳሌ ክርስቲያኖች እንዲህ እያሉ ይፀልያሉ፡፡ "ኦ ጌታ ሆይ የቀን እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ" ታድያ የቀን ዳቦዋችንን ለመስጠት ይህ ለክርሽና አስቸጋሪ ስራ ነውን? ይህንንም እየሰጠን ይገኛል፡፡ ይህንንም የቀን ዳቦ ለሁሉም እየሰጠ ይገኛል፡፡ ሰለዚህ ይህ አግባብ ያለው ፀሎት አይደለም፡፡ የእነርሱ ፀሎት ነው፡፡ ቼታንያ መሀፕራብሁ እንደጠቀሰውም “ማማ ጃንማኒ ጃንማኒሽቫሬ ብሀቫታድ ብሀክቲር አሆይቱኪ ትቫዪ” (ቼቻ አንትያ 20 29 ሺክሳስታካ 4) በዚህም ፀሎት ምንም ነገር እየጠየቅን አንገኝም፡፡ ክርሽና አብዩ ጌታ በዚህ ዓለም የሚያስፈልገንን ነገር በሙሉ ሰጥቶን ይገኛል፡፡ ፑናስያ ፑርናም አዳያ ፑርናም ኤቫ አቫሺሽያቴ (ኢሾ መጥርያ ጥቅስ) ነገር ግን ሀጥያተኛ ሆነን ስንገኝ በተፈጥሮ አማካኝነት ሲጎልብን ይታያል፡፡ ከሀዲዎች ስንሆን ወይንም ሰይጣናዊ ባህርይ ስንገነባ አምላክ የሚሰጠን ነገር ሁሉ እየጐደለብን ሲሄድ እናየዋለን፡፡ ከዚይም ደግሞ ማልቀስ እንጀምራለን “ኦ ዝናብ የለም፡፡ ይህ የለም ይህ ጎደለ ....“ ይህም በተፈጥሮ እንዲያንስ ሆን ብሎ የተደረገ ነው፡፡ ነገር ግን አብዩ ጌታ እንዳቀረበው ከሆነ በመላ ዓለም በቂ ምግብ ለሁሉም ቀርቦ ይገኛል፡፡ ”ኤኮ ባሁናም ቪዳድሀቲ ካማን“ ክርሽና ለሁሉም እያቀረበ ይገኛል፡፡ በዚህም ቁሳዊ ዓለም የቅንጣፊ ያህል እንኳን ፍላጎታችንን ለሟሟላት ፕላን ካለን ከዚያም የቁሳዊ ገላ ይዘን እንደገና መወለዳችን የማይቀር ነው፡፡ ይህም "ጃንማ” ይባላል፡፡ አለበለዛ ግን ነፍስ አትወለድም አትሞትም፡፡ አሁን ይህ መወለድ እና መሞት... እነዚህ ነፍሳት እንደ እሳት ቅንጣፊ ሆነው ይመሰላሉ፡፡ አብዩ ጌታ ደግሞ እንደ ትልቁ እሳት ሆኖ ይመሰላል፡፡ ይህም ትልቁ እሳት ነው፡፡ ከዚህም ጋር ሊመሰል ይችላል፡፡ ትናንሾቹም የእሳት ቅንጣፊ እራሳቸው እሳቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ እሳቶች ዘለው ከትልቁ እሳት ይወጣሉ፡፡ የእኛም በዚህ ዓለም መወለድ እንደዚህ መውደቅ ይመሰላል፡፡ መውደቅ ማለትም ወደ እዚህ ቁሳዊ ዓለም መጣን ማለት ነው፡፡ ለምን? ይህም ቁሳዊ ዓለምን ለመደሰት ነው፡፡ ይህም ክርሽናን ለመምሰል ነው፡፡ ክርሽና አብዩ ተደሳች ነው፡፡ እኛ ደግሞ ትሁት አገልጋዮቹ ነን፡፡ አንዳንድ ግዜ አገልጋዩ ልክ እንደ ጌታው መደሰት ይፈልጋል፡፡ ይህም በተፈጥሮ ያለ ነው፡፡ ይህም አስተሳሰብ በጭንቅላታችን ውስጥ ሲገባ ይህም ማያ ይባላል፡፡ ምክንያቱም እኛ ከክርሽና ውጪ ተደሳቾች ልንሆን አንችልም፡፡ ይህ የሀሰት ደስታ ይሆናል፡፡ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ላይም ደስተኛ ልሆን እችላለሁ ብለን የምናስብ ከሆነ ይህም የተሳሳተ ፈለግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ሁሉም የቁሳዊው ዓለም ደስተኛ ለመሆን ሲጥር ይገኛል፡፡ ከሁሉም መጨረሻ እና የበላዩ ወጥመድ ደግሞ አንድ ሰው እንዲህ ሲያስብ ነው፡፡ “አሁን አብዩ አምላክ ለመሆን እችላለሁ፡፡” ይህ የከፍተኛው ወጥመድ ነው፡፡ በመጀመሪያም ደረጃ አስተዳዳሪ ወይንም የንብረት ባለቤት መሆን እንፈልጋለን፡፡ ከዚያም ጠቅላይ ሚኒስቴር ከዚያም ይህንን ወይንም ያንን ለመሆን እንፈልጋለን፡፡ ሁሉም ነገር ግራ ሲጋባን ደግሞ አንድ ሰው “አሁን ጌታ መሆን እፈልጋለሁ፡፡” ብለን እናስባለን፡፡ ይህም ማለት ያው አንድ ዓይነቱ አዝማምያ ነው፡፡ ጌታ ለመሆን እና ክርሽናን ለማስመሰል ነው፡፡