AM/Prabhupada 0630 - በሀዘን መመሰጥ አያስፈልግም ምክንያቱም ነፍስ ሁልግዜ ህያው ናት፡፡



Lecture on BG 2.28 -- London, August 30, 1973

ድቮቲ፡ ትርጉም ”በዚህ ቁሳዊ ዓለም የሚገኙት እያንዳንዳቸው ነፍሳት በመጀመሪያ ደረጃ በትእይንት የቀረቡ አይደሉም በመሀከል ደግሞ በትእይንት የሚታዩ ናቸው፡፡“ ”መላ ዓለም በአብዩ አምላክ ስትጠፋ ደግሞ እንደገና ከትእይንት ይጠፋሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ በሀዘን መመሰጥ ምን ፋይዳ አለው?“

ፕራብሁፓድ፡ ነፍስ ዘለዓለማዊ ናት፡፡ ስለዚህ በሞት ግዜ በሀዘን መመሰጥ ምንም አስፈላጊነት የለውም፡፡ ምክንያቱም ነፍስ ስለማትሞት ነው፡፡ ገላችንም ሲበላሽ ወይንም ሲሞት ነፍስ ባለመሞትዋ ሀዘን ሊገባን አስፈላጊ አይደለም፡፡ ይህንንም ፍፁም እውነት የማይረዱ ሰዎች እና እንዲህ የሚሉ ”ነፍስ የለንም በመጀመሪያም ደረጃ ሁሉም ነገር ባዶ ነበረ፡፡“ በመጀመሪያ ባዶ ከነበረ በመሀከል ደግሞ በትእይንት ከቀረበ በመጨረሻ ደግሞ ባዶ ከሆነ እና ከባዶ ተነስቶ ወደ ባዶ ከገባ ሀዘን አስፈላጊነቱ ምን ላይ ነው? ክርሽና ያቀረበውም የተቀናቀነ ሀሳብ ይህ ነው፡፡ በሁለቱም አቀራረብ ብናየው ሀዘን የሚያስፈልግበት ነገር የለም፡፡ ፕራጁምና፡ (ገለጻ)፡ ይህንንም በከሀዲያን የተውጠነጠነውን ሀሳብ ብንቀበል እንኳን ለሀዘን ምንም መነሻ አይኖረንም፡፡ ምንም እንኳን ነፍስ ከቁሳዊ አካል ውጪ ለመኖር ብትችልም የቁሳዊ ዓለም ንጥረ ነገሮች ዓለም ከመፈጠርዋ በፊት በትእይንት ሳይቀርቡ ይኖራሉ፡፡ ከዚህም ከትእይንት ስውር ደረጃ ወደ ትእይንት መቅረብ ይመጣል፡፡ ለምሳሌ ከሰማይ ቀጥሎ አየር ይፈጠራል ከአየር እሳት ይፈጠራል ከእሳት ቀጥሎ ደግሞ ውሀ ይፈጠራል ከውሀ ቀጥሎ ደግሞ አፈር ይፈጠራል ከመሬት ደግሞ ብዙ የተለያዩ ፍጥረቶች ይከሰታሉ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ የተፈጥሮ አፈጣጠር ሂደቱ እንደዚህ ነው፡፡ ከሰማይ ወደ አየር ከዚያም እሳት ከዚያም ውሀ ከዚያም አፈር፡፡ የተፈጥሮ አፈጣጠር ሂደቱ እንደዚህ ነው፡፡ ፕራዱይምና፡ ”ለምሳሌ ትልቅ የሚታይ ህንፃ በትእይንታችን የቀረበው ከመሬት ነው፡፡“ ህንፃውም ሙሉ በሙሉ ከፈረሰ እና ከተገነጣጠለ በትእይንት ቀርቦ የነበረው ከትእይንታችን ይጠፋል፡፡ ወደ አቶሞች እና ወደ መጣበት ኬሚካሎች ይመለሳል፡፡ የተፈጥሮ ሀይልን እና የኮንሰርቬሽን ህግጋቶችን ተከትሎ ይሄዳል፡፡ በግዜ በኋላ ግን እንደገና በትእይንት ቀርበው በኋላ ደግሞ ከትእይንት ሊጠፉ ይችላሉ፡፡ ይህ ነው ልዩነቱ፡፡ ስለዚህ በትእይንት ኖረ አልኖረም የሀዘን መነሻው ምንድን ነው? በአብዩ ሀይል አማካኝነት የቁሳዊው ዓለም ከትእይንት መሰወር ሁሉም ነገር ጠፋ ማለት አይደለም፡፡ በዚህም ሂደት በመጀመሪያ እና በመጨረሻ ደረጃ ሁሉም ነገር ከትእይንት ተሰውረው ይገኛሉ፡፡ ለትእይንት የሚቀርቡትም በመሀከለኛ ደረጃ ነው፡፡ ይህም ምንም ዓይነት የቁሳዊ ለውጥ አያመጣም፡፡ በብሀገቨድ ጊታ የተጠቀሰውን የቬዲክ እውቀት ድምደማ መቀበል ይኖርብናል፡፡ ”አንታቫንታ ኢሜ ዴሀ“ ይህም ይህ የቁሳዊ ዓለም ገላችን በግዜ በኋላ ጠፊ ነው፡፡ ”ኒትያስዮክታህ ሻሪሪናህ“ ነገር ግን ነፍስ ዘለዓለማዊ ናት፡፡ ሰለዚህ ሁልግዜ ማስታወስ ያለብን ነገር ቢኖር ገላችን እንደ ልብስ ነው፡፡ ታድያ ይህ ልብስ ሲቀየር ሀዘን ውስጥ የምንገባው ለምንድን ነው? ከዘለዓለማዊው ነፍስ ጋር ሲወዳደር የቁሳዊው አካል ምንም ዘለቄታ ያለው ሕይወት የለውም፡፡ ገላችንም ልክ እንደ ህልም ይቆጠራል፡፡ በህልማችንም ወደ ሰማይ ለመብረር ወይንም እንደ ንጉስ በጋሪ ላይ ለመቀመጥ እንሻ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከህልማችን ስንነቃ በሰማይም ወይንም በንጉስ ጋሪ ላይም እንዳልተቀመጥን እንረዳለን፡፡ ይህም የቬዲክ የእውቀት ብልሀት እራሳችንን የምናውቅበትን መንገድ ይሰጠናል፡፡ የቁሳዊ አካልም ጊዜያዊነት መሰረቱ ምን እንደሆነ ከቬዲክ እውቀቶች እንማራለን፡፡ ሰለዚህ በሁለቱም መንገድ አንድ ሰው በነፍስ መኖር ወይንም አለመኖር ቢያምንም ባያምንም ገላችን በጠፋ ግዜ ምንም ሀዘን እንዲገባን የሚያደረገን ምክንያት አይኖረንም፡፡