AM/Prabhupada 0711 - የጀመራችሁት ሁሉ እንዳታቆሙ፡፡ በደስታ ላይ በመሰማራት ቀጥሉበት፡፡
Speech Excerpt -- Mayapur, January 15, 1976
ፕራብሁፓድ፡ በዚህም የሚገኘው ትልቁ ደስታ .... የብሀክቲቪኖድ ታኩር ምኞት ነው፡፡ ይህም አውሮፓውያኖች አሜሪካኖች እና ህንዶች ሁሉም በአንድነት በደስታ ሲደንሱ እና “ጐውራ ሀሪ” እያሉ ሲዘምሩ ነው፡፡ ይህም ቤተ መቅደስ “ማያፑር ቻንድሮዳያ ቤተ መቅደስ” የተቋቋመው ለመንፈሳዊ የተባበሩት መንግስታት ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት የወደቀበት ዓላማ በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ ተሳክቶ እናየዋለን፡፡ ይህም ቼታንያ መሀፕራብሁ የሰጠንን ስርዓት በመከተል ነው፡፡ ፕሪቲ ቪቴ አቼ ናጋራዲ ግራም ሳርቫትራ ፕራቻራ ሆይቤ ሞራ ናማ (ቼብ፡አንትያ ክሀንዳ 4 126) እናንተም ከመላው ዓለም መጥታችሁ እዚህ ተሰባስባችሁ ትገኛላችሁ፡፡ በዚህም ቤተ መቅደስ በአንድነት በመኖር ላይ ትገኛላችሁ፡፡ እነዚህንም ትንንሽ ልጆች አስተምሯቸው፡፡ እነዚህንም ትንንሽ ልጆች በማየቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ እዚህም የተሰባሰብነው ከተለያዩ አህጉራት ነው፡፡ ይህም ከህንድ ከቤንጋል ወዘተ ሁላችንም በአንድነት የቁሳዊ እና የዓለማዊ አስተሳሰባችንን ረስተን እንገኛለን፡፡ የዚህም እንቅስቃሴያችን ትልቁ ውጤታችን ይኅው ነው፡፡ ይህም ሁላችንም የቁሳዊ ዓለምን በገላ የተመሰረተውን አስተሳሰባችንን ትተነው እንገኛለን፡፡ እዚህ መጥቶ ማንም ሰው እኔ “አውሮፓዊ ነኝ አሜሪካዊ ነኝ ህንድ ነኝ እስላም ነኝ ክርስቲያን ነኝ ብሎ የሚያስብ የለም፡፡ እነዚህንም ማእረግ ወይንም ማንነት ረስተውት ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ግዜም የሀሬ ክርሽናን ቅዱስ ስም በአንድነት በመዘመር ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ይህንን የጀመራችሁትን መልካም ተግባር አትስበሩት፡፡ በደስታ እና በፍንጠዛ ቀጥሉበት፡፡ ቼታንያ መሀፕራብሁ የማያፑር ጌታም በእናንተ በጣም ደስተኛ ይሆናል፡፡ በመጨረሻም ደረጃ ወደ ቤት ወደ አብዩ አምላክ ቤተ መንግስት ትሄዳላችሁ፡፡ እናመሰግናለን፡፡