AM/Prabhupada 1062 - የዚህ የቁሳዊ ዓለም ጌታ ወይንም ዋና ተቆጣጣሪ መሆን የመፈለግ አዝማምያ አለን፡፡

From Vanipedia


We Have the Tendency of Controlling Over the Material Nature - Prabhupāda 1062


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

ይህም ስህተት ነው፡፡ በዚህ ትእይንተ ዓለም ውስጥ ብዙ የሚያስደንቁ ነገሮች ባየንም ቁጥር በዚህም የትእይንተ ዓለም ፍጥረት ውስጥ በጣም የሚያስደንቅ ክስተት ባየንም ቁጥር የዋና ተቆጣጣሪዉ የጌታ እጅ እንዳለበት መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ምንም ዓይነት ነገር ቢሆን ያለ ዋና ተቆጣጣሪ ሊከሰት አይችልም፡፡ የተቆጣጣሪንም እጅ ከክስተቶች ጀርባ ለማየት አለመቻል እንደ ልጅነት ይቆጠራል፡፡ ይህም በመንገድ ላይ እንደሚታየው ቆንጆ እና ፈጣን መኪና ሊመሰል ይችላል፡፡ ይህም በመንገድ ላይ የሚሽከረከረው ጥሩ የሜካኒካል ኢንጂኔሪንግ ብልሀት ሰለተጨመረበት ነው፡፡ ትንሽ ልጅ ግን "ይህ መኪና እንዴት ነው ለመሮጥ የሚችለው?" ብሎ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ "ምንም ፈረስ ወይንም የሚጎትተው ነገር ሳይኖር እንዴት ሊንቀሳቀስ ይችላል?" ብሎ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን አዋቂ ሰው ወይንም ጠና ያለሰው ምንም እንኳን መኪናው በሜካኒካል ኢንጂኔሪንግ የተቀነባበረ ቢሆንም መኪናው ያለ ሾፌር መንቀሳቀስ አይችልም፡፡ ምንም እንኳን መኪናው የኢንጂኔሪንግ ብልሀት ቢሮረውም እንኳን በአሁኑ ዘመን ብዙ ማሽኖች ሲሰሩ እናያለን፡፡ ቢሆንም ግን እነዚህን ማሽኖች ሁሉ የሚቆጣጠር ወይንም ከእነዚህ የሚያስደንቁ ማሽኖች ጀርባ የሚያንቀሳቅሳቸው ሰው ወይንም ሾፌሮች እንደአሉ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አብዩ ጌታ ዋናው ተቆጣጣሪ ነው፡፡ ”አድህያክሻ“ አብዩ ጌታ ዋናው የበላይ ተቆጣጣሪ ሲሆን በእርሱም ስር ሁሉም ነገር ሲተዳደር ይገኛል፡፡ ጂቫ ወይንም እያንዳንዱ ነፍሳት በብሀገቨድ ጊታ ምዕራፎች ሁሉ እንደተጠቀሰው የአምላክ ቅንጣፊ አካላት መሆናቸውን እንረዳለን፡፡ ይህም በተከታታዩ ምእራፎች ውስጥ ተገልጿል፡፡ ማማኢቫምሾ ጂቫ ብሁታ (ብጊ፡15 7) አምሻ ማለት ወገን እና ቅንጣፊ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ የወርቅ ቅንጣፊ አካል ወርቅ ነው፡፡ የውቅያኖስ ጠብታ ውሀም የጨውነት ባህርይ አለው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛ ህያዊ ነፍሳት የአምላክ ወይንም የዋናው ተቆጣጣሪ (ኢሽቫራ) የክርሽና ቅንጣፊ አካላት ነን፡፡ ኢሽቫራ ብሀገቫን ወይንም ጌታ ሽሪ ክርሽና ለማለት የፈለግሁትም አይነታችን ተመሳሳይ ሆኖ ሲገኝ ኃይል እና መጠናችን ግን የደቀቀ እና ያነሰ ሆኖ ይገኛል፡፡ እኛም ምንም እንኳን ለመቆጣጠር የምንሻ ብንሆንም ደረጃችን በአቅሙ ያነሰ ተቆጣጣሪ ወይንም ትንሹ ኢሽቫራ ተብለን እንታወቃለን፡፡ ለምሳሌ በአሁኑ ግዜ ፍጥረተ ዓለምን በቁጥጥራችን ስር ለማድረግ እንሞክራለን፡፡ የትእይንተ ዓለምን ወይንም ፕላኔቶችንም ለመቆጣጠር እንሞክራለን፡፡ የአርቲፊሻል ፕላኔቶችንም ለማንሳፈፍ ጥረት ስናደርግ እንታያለን፡፡ ስለዚህ ይህ የመቆጣጠር እና የመፍጠር አዝማምያ በአንደበታችን ውስጥ ያለ ባህርይ ነው፡፡ ምክንያቱም በመጠኑ እንደ አብዩ ጌታ የመቆጣጠር እና የመፍጠር አዝማምያ ስላለን ነው፡፡ መረዳት ያለብን ነገር ቢኖር ግን ይህ አይነቱ ባህርያችን ለእኛ በቂ ሆኖ አይታይም፡፡ ባህርያችን አልፎ ተርፎም መላ የቁሳዊ ዓለምን በቁጥጥራችን ስር ለማድረግ ጥረት ስናደርግ እንታያለን፡፡ ነገር ግን እኛ ዋናው የበላይ ተቆጣጣሪ እንዳልሆንን ግልፅ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ እውነታዎች ሁሉ በብሀገቨድ ጊታ ቅዱስ መፅሀፍ ውስጥ ተተንትነው ይገኛሉ፡፡ ታድያ ይህ ቁሳዊ ዓለም ምንድን ነው? ይህም ፍጥረት በደንብ ተገልጿል፡፡ ይህም ቁሳዊ ዓለም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ እንደ ዝቅተኛው የአምላክ ሀይል ወይንም ፕራክርቲ ተብሎ ተገልጿል፡፡ ሕይወት ያላቸው ነዋሪ ነፍሳት ሁሉ ደግሞ እንደ ከፍተኛው ኃይላት ወይንም ከፍተኛው ፕራክርቲ ተበለው ተገልፀዋል፡፡ ፕራክርቲ ማለት በቁጥጥር ስር ያለ ማለት ነው፡፡ የፕራክርቲ ትክክለኛ ትርጉሙ የሴት ፆታ ወይንም ሴት ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ባል ሚስቱን ሲደግፍ እና ሲቆጣጠር ይታያል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ፕራክርቲ ማለት በቁጥጥር ስር ያለች ማለት ነው፡፡ አብዩ የመላእክት ሁሉ ጌታ ዋናው ተቆጣጣሪ ነው፡፡ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ የሚገኙትም ፕራክርቲዎች ማለትም ነዋሪ ነፍሳቶች እና የቁሳዊው ዓለም በአብዩ ጌታ ቁጥጥር ስር የሚገኙ የተለያዩ ዓይነት ፕራክርቲዎች ናቸው፡፡ በብሀገቨድ ጊታም ህያው ነፍሳት የአምላክ ቅንጣፊ አካላት ይሁኑ እንጂ ፕራክርቲ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ በሰባተኛው ምዕራፍ እና በአምስተኛው ጥቅስ ላይ በግልፅ ተጠቅሷል፡፡ “አፓሬያም ኢታስ ቱ ቪድሂ አፓራ” (ብጊ፡7 5) ይህ የቁሳዊው አለም ፕራክርቲ ”አፓራያም“ ወይንም የእኔ የዝቅተኛው ኃይል ነው፡፡ ”ኢታስ ቱ“ ከዚህም ባሻገር ሌላ ዓይነት ፕራክርቲ አለ፡፡ ይህስ ፕራክርቲ ምንድን ነው? ”ጂቫ ብሁታ“ ይህም ፕራክርቲ በሶስት አይነት ባህርይ ወይንም ስልቶች ተመድቦ ይገኛል፡፡ እነዚህም የጥሩ እና ረጋ ያለ ባህርይ ረጋ ያላለ ወይንም የመቅበዝበዝ ባህርይ እና የድንቁርና ባህርዮች ናቸው፡፡ ከእነዚህም ሶስት ዓይነት ባህርዮች በላይ ማለትም ረጋ ያለ የመቅበዝበዝ እና የድንቁርና ባህርዮች በላይ ዘለዓለማዊ ግዜ አለ፡፡ እነዚህም ሶስት ዓይነት ባህርዮች ተቀላቅለው እና በዘለዓለማዊው ግዜ ቁጥጥር ስር ሆነው እያለ ብዙ ዓይነት እንቅስቃሴ ይኖራቸዋል፡፡ እነዚህም እንቅስቃሴዎች ”ካርማ“ ይባላሉ፡፡ እነዚህም እንቃስቃሴዎች በግዜ ለመተመን በማይቻል ርዝመት ሲካሄዱ የቆዩ ናቸው፡፡ እኛም ነዋሪ ነፍሳት የእንቅስቃሴያችንን ወይንም የስራችንን ውጤት እየተረከብን ስንደሰት ወይንም መከራ ስንቀበልበት እንታያለን፡፡