AM/Prabhupada 1064 - አብዩ አምላክ አካል በእያንዳንዳችን የልብ ማዕከል ውስጥ ሆኖ ይኖራል፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

አብዩ አምላክ አካል በእያንዳንዳችን የልብ ማዕከል ውስጥ ሆኖ ይኖራል፡፡ - Prabhupāda 1064


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

ይህም በብሀገቨድ ጊታ እንደተገለፀው አብይ ንቃት ያለው አምላክ ነው፡፡ በዚህም ምእራፍ ውስጥ በጂቫ (ነፍስ) እና በኢሽቫራ (አብዩ ጌታ) መሀከል ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ ተገልጿል፡፡ "ሼቴራ ሼትራ ግያ" ይህም "ሼትራ ግያ" ተገልጿል፡፡ ይህም አብዩ ጌታ “ሼትራ ግያ” ወይንም አብይ ንቃት እንደአለው ነው፡፡ ነፍሳትም ወይንም ጂቫዎችም ንቃት አላቸው፡፡ ነገር ግን ልዩነታቸው በምድር ላይ ያሉት ነፍሳት ያላቸው ንቃት በገላቸው ብቻ የተወሰነ ነው፡፡ አብዩ ጌታ ሰለእያንዳንዱ ነፍሳት ገላ ሙሉ ንቃት ይዞ ይገኛል፡፡ “ኢሽቫራ ሳርቫ ብሁታናም ህርዴሼ አርጁና ቲስትሀቲ” (ብጊ፡ 18 61)

አብዩ ጌታ በእያንዳንዱ ነፍሳት የልብ ማእከል ውስጥ ይኖራል፡፡ ሰለዚህ የእያንዳንዱን ጂቫ ወይንም ነፍሳት ንቃት መንፈስ እና እንቅስቃሴ ሁሉ ለይቶ ያውቃል፡፡ ይህንንም መዘንጋት የለብንም፡፡ እንደተገለፀውም ፓራማትማ ወይም አብዩ የመላእክት ጌታ በእያንዳንዱ ነፍሳት የልብ ማእከል ውስጥ እንደ “ኢሽቫራ” ሆኖ ይኖራል፡፡ ይህም እንደ ዋናው ተቆጣጣሪ ሆኖ ሲሆን መመሪያም ለነፍሳት ሲሰጥ ይገኛል፡፡ መመሪያ ሲሰጥ ይገኛል፡፡ “ሳርቫስያ ቻሀም ህርዲ ሳኒቪስቶህ” (ብጊ፡ 15 15) በሁሉም ነፍስ ውስጥ በመገኘት እንደ ፍላጎቱ መመሪያ ሲሰጥ ይገኛል፡፡ ነዋሪ ነፍሳት ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ሲረሱ ይገኛሉ፡፡ ነፍሳት በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ነገር ለማድረግ ውሳኔ ያደርጋሉ፡፡ በዚህም ስራ በመወሳሰብ ላይ ይገኙና ለሚያደርጉትም ስራ እንደሚገባቸው “ካርማ” ውጤቱን ሲያገኙ ይታያሉ፡፡ የያዘውንም የፍጥረት ገላ በህልፈተ ህይወት ግዜ ትቶ ሂዶ ወደ ሌላ የተለየ ገላ ገብቶ ሲወለድ ይገኛል፡፡ ይህም ልክ እንደምንቀያይረው ክዳናችን ወይንም ልብሶቻችን ይመሰላል፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተገልጿል፡፡ “ቫሳምሲ ጂርናኒ ያትሀ ቪሀያ” (ብጊ፡ 2 22) አንድ ሰው የተለያየ ክዳኑን በየግዜው እንደሚቀያይረው ሁሉ መላ ነፍሳትም ገላቸውን በየግዜው ሲቀያይሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ሂደት ህያው ነፍስ አዲስ ገላ ይዞ በተፈጠረ ግዜ ሁሉ ባለፈው ህይወቱ በተከሰቱት እንቅስቃሴዎቹ አንፃር ደስታውም ሆነ ችግሮቹ ሁሉ ሲፈራረቁበት ይገኛሉ፡፡ እነዚህም የቀድሞ እንቅስቃሴዎች ወይንም ድርጊቶች ውጤት ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡ ይህም ሊከሰት የሚችለው ህያው ነፍስ በጥሩ አንደበት ስትሰማራ ነው፡፡ ወይንም ምን አይነት እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሰማራት እንዳለባት ስትረዳ ነው፡፡ በዚህም አይነት በትክክለኛ መስመር ከተሰማራን ያለፉት ኑሮዎቻችን ክፉ እቅስቃሴዎች ውጤት ሁሉ ልንቀይረው እንችላለን ወይንም ለችግር ሊያጋልጡን አይችሉም፡፡ ስለዚህም ካርማ ዘለአለማዊ አይደለም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ከጠቀስናቸው አምሰት ነገሮች (ኢሽቫራ ጂቫ ፕራክርቲ ካላ እና ካርማ) አራቱ ዘለአለማዊ ሲሆኑ አንዱ (ካርማ) ደግሞ ዘለአለማዊ አይደለም፡፡ ™ የላቀ እና አብይ ንቃት ያለው ኢሽቫራ ከህያው ነፍስ ጋር ይህንን የመሰለ ተመሳሳይነት አለው፡፡ የላቀው ዓብዩ ጌታ እና የነፍስም ልዩነት እንደሚከተለው ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ የነፍስ ደረጃ እንዲህ ነው፡፡ ሁለቱም ዓብዩ ጌታ እና ነፍሳት ንቃት ያላቸው ናቸው፡፡ ይህም የተፈጥሮ ንቃታቸው መንፈሳዊ ነው፡፡ ይህም ንቃት የመጣው በቁሳዊ ነገሮች አማካኝነት አይደለም፡፡ ይህም ስህተታዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ ንቃት ሊፈጠር የሚችለው በዚህ ቁሳዊ አለም ውሰጥ በሚገኙ ንጥረ ነገሮች ግኑኝነት ነው የሚለው ያልተጨበጠ ሀሳብ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተቀባይነት የለውም፡፡ መንፈሳዊ አንደበታችን በዓለማዊ አስተሳሰብ ተሸፍኖ ተጣሞ እንደሚያንጸባርቅ ብርሃን ሁኖ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ብርሃን በቀለማዊ መስታወት ሲያልፍ ብርሀኑ ቀለማዊ ይመስላል፡፡ የጌታ ክርሽና አንደበት እንደዚሁ ምሳሌ በአለማዊ ይዘቶች ሊበገር አይችልም፡፡ ጌታ ክርሽናም እንዲህ ብሏል፡፡ “ማያድህያክሼና ፕራክርቲ” (ብጊ፡ 9 10) ጌታ ክርሽና ወደ እዚህ ዓለማዊ ምድር ሲመጣ አንደበቱ በዓለማዊ ይዘቶች አይበከልም፡፡ በዚህም ዓለማዊ አንደበት የሚጠቃ ቢሆን ኑሮ በብሃገቨድ ጊታ የሚገኘውን የላቀ መንፈሳዊ ርእሰ ትምህርቶች ለመግለጽ ብቁ አይሆንም ነበር፡፡ አንድ ሰው ከዓለማዊ አስተሳሰብ እና አንደበት ነፃ ካልሆነ ስለ መንፈሳዊው ዓለም በጥልቅ ተገንዝቦ ለመናገር አይችልም፡፡ ከዓለማዊ አስተሳሰብ እና አንደበት ነፃ ካልሆነ ለመንፈሳዊ ንቃት ብቁ አይሆንም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አብዩ ጌታ በዓለማዊው አንደበት የተበረዘ አይደለም፡፡ የእኛ አንደበት ግን በዓለማዊ አስተሳሰብ የተበከለ ነው፡፡ ብሀገቨድ ጊታም የሚያሰተምረንም ይህንኑ ነው፡፡ የተበከለ ዓለማዊ አስተሳሰባችንን እንዴት ልናፀዳው እንደምንችል ያስተምረናል፡፡ አንደበታችን ንጹህ ሲሆን የምንሰራቸው ስራ ሁሉ ከኢሽቫራ ወይንም ከጌታ ምኞት ጋር የተዋሀደ ይሆናል፡፡ ይህም በጣም ደስታኛ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ከክፉም ለመቆጠብ ብለን ሁሉን አይነት እንቅስቃሴዎችንም ማቆም አለብን ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን የምንሰራቸውን ስራዎች ሁሉ ንጹህ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይህም ንጹህ እና መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ብሀክቲ ይባላል፡፡ በብሀክቲ መንፈስ የምንሰራው ስራ ሁሉ ልክ እንደ ተራ ስራ መስለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ስራዎች በዓለማዊ አንደበት የተበከሉ ስራዎች አይደሉም፡፡ በመንፈስ የጠሩ ስራዎች ናቸው፡፡ አንድ ድንቁርና የተሞላበት ሰው ሌላው ትሁት የጌታ አገልጋይ የሚሰራውን ስራ እንደ ተራ ዓለማዊ ስራ አድርጐ ሊያየው ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ የጥሩ መንፈስ አስተሳሰብ የጐደለው ሰው የዚህ የጌታ ትሁት አገልጋይ አንደበት በዓለማዊና ንጹህ ባልሆነ አስተሳሰብ ያልተበከለ መሆኑን አይረዳም፡፡ በዓለማዊም መንፈስ የተበከሉ ስራዎች አይደሉም፡፡ እነዚህ የጥሩ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎ ች ከሶስቱ የቁሳዊ ፍጥረት ባህሪዎች አልፈው የላቀ የመንፈሳዊ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ ቢሆንም ግን መረዳት ያለብን ነገር ቢኖር በአሁኑ ግዜ በዚህ ዓለም ላይ የሚገኘው ህልውናችን በተበከለ ደረጃ እንደሚገኝ ነው፡፡