AM/Prabhupada 1066 - የአስተሳሰባቸው አእምሮ ዝቅ ብሎ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ አብዩ ጌታ ሰብአዊ ባህርይ እንዳለው አይረዱም፡፡

From Vanipedia


የአስተሳሰባቸው አእምሮ ዝቅ ብሎ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ አብዩ ጌታ ሰብአዊ ባህርይ እንዳለው አይረዱም፡፡
- Prabhupāda 1066


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

በዚህ ትእይንተ ዓለም ውስጥ ከሚገኙት ነገሮች ሁሉ ከፍጥረታት ሁሉ በሀከል የሚገኘው ወይንም ደስታ እንዲቀርብለት የሚገባው ሀይል በመሀከላችን የሚገኘው ዓብዩ ጌታ ብቻ ነው፡፡ ሌሎች ነፍሳት ሁሉ እርሱን ለማገልገል ወይንም ለማስደሰት የተፈጠሩ ናቸው፡፡ በዚህም አገልግሎታቸው እራሳቸውም ደስታ ያገኙበታል፡፡ ይህም በመሀከላችን ያለው ግኑኝነት ልክ እንደ ጌታ እና እንደ አገልጋይ ሊታይ ይችላል፡፡ ይህም ማለት የቤቱ ጌታ ደስተኛ ከሆነ አገልጋዮቹም ሁሉ ደስተኞች ይሆናሉ፡፡ ይህ ነው ሂደቱ፡፡ ሰለዚህ ዓብዩ የመላእክት ጌታን ሁሌ ለማስደሰት መጣር አለብን፡፡ ምንም እንኳን ይህንን ዓለም ለመደሰት እና በዚህ ዓለም ውስጥ ምርምር በማድረግ እንደ ጌታ ለመፍጠር አዝማሚያ ሊኖረው የቻለው ይህ አዝማሚያ በዓብዩ ጌታ ውስጥ ሰለሚገኝ እና በእኛም አንደበት ውስጥ ሰለሚገኝ ነው፡፡ ይህ የትእይነተ ዓለም የተፈጠረው በዓብዩ የመላእክት ጌታ ነው፡፡ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥም ስለእነዚህ ፍጥረታት እና ስለተሟላው ፍጥረት ተገልጾልናል፡፡ እነዚህም የተሟሉ ፍጥረታት የሚያጠቃልሉት፣ ዓብዩ ዋናው ተቆጣጣሪውን፣ በቁጥጥር ስር ያሉትን ነፍሳት፣ የመላ ትእይንተ ዓለምን እንዲሁም ዘለዓለማዊው ግዜን እና የነፍሳትን እንቅስቃሴ እና ስራዎች እንደሚያጠቃልል በጥልቅ ተገልጿል፡፡ ይህም ሁሉ በአጠቃላይ ፍፁም እውነትን የምንለውን የያዘ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ስለዚህ በተሟላ መንገድ የሚገኘው አብዩ የመላእክት ሁሉ ጌታ ሽሪ ክርሽና ዓብዩ እና ፍጹም የሆነ እውነትን የያዘ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ብሎ እንደገለጽኩትም በዚህ በቁሳዊ ዓለም ውስጥ የምናየው ክስተት ሁሉ ከእርሱ የተለያየ ሀይላት የመነጩ ናቸው፡፡ እርሱም የተሟላ ይዘት ያለው ነው፡፡ ሰብዓዊ ያልሆነው እና "ብራህማን" ተብሎ የሚታወቀው የጌታ ፎርም ወይንም ቅርጽ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልጿል፡፡ ይህም ሰብዓዊ ባህርይ የሌለው የአብዩ ጌታ ፎርም ሙሉ ከሆነው የዓብዩ ጌታ ፎርም የበታችነት ያለው ክስተት ነው፡፡ "ብራህማኖ ሃም ፕራቲስትሀ (ብጊ 14.27) ሰብዓዊነት የሌለው የብራህማን ክስተት ይህ ሰብዓዊነት የሌለው የብራህማን ክስተት በብራህማ ሱትራ ውስጥ በፀሀይ ጮራ እንደሚመሰል በምሳሌ ተገልጿል፡፡ ልክ የፀሀይ ፕላኔት እና የፀሀይ ጮራ እንደሚገኙም ሁሉ እንደዚህም ሁሉ ሰብዓዊነት ይዘት የሌለው የጌታ የብራህማን አካል ልክ እንደ ፀሀይ ጮራ ይመሰላል፡፡ ይህም ከዓብዩ የመላእክት ጌታ ወይንም ከዓብዩ ብራህማን የሚመነጭ ነው፡፡ ስለዚህ ሰብዓዊነት የሌለውን የዓብዩ ጌታን የብራህማን አካል በማወቅ ብቻ ሙሉውን ዓብዩ ጌታን ልንረዳው አንችልም፡፡ እንደዚህም ሁሉ ሰለ ፓራማትማ ወይን በልባችን ስለሚገኘው የአብዩ ጌታ አካል "ፑሩሾታም ዮጋ" ተብሎ በሚታወቀው የብሀገቨድ ጊታ መፅሀፍ ውስጥ ተገልጿል፡፡ "ፑሩሾታም ዮጋ" ተብሎ የሚታወቀውን የብሀገቨድ ጊታ ቅዱስ መጽሀፍ ምዕራፍ ስናነብ "ፑሩሾታም" ዓብዩ የመላእክት ሁሉ ጌታ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ይህም "ፑሩሾታም" ሰብዓዊነት ከሌለው የ"ብራህማን" የጌታ ቅርጽ እና በልባችን ውስጥ ከሚገኘው ከ "ፓራፓትማ" የበላይ እንደሆነ ለመረዳት እንችላለን፡፡ ዓብዩ የመላእክት ጌታ "ሳት ቺድ አናንዳ ቪግራሀህ" ተብሎ ይታወቃል፡፡ (ብሰ 5 1) በብራህማ ሰሚታ መፅሀፍም ውስጥ የመጀመሪያው ጥቅስ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፣ "ኢሽቫራ ፓራማ ክርሽና ሳክ ቺድ አናንዳ ቪግራሀ፣ አናዲር አዲር ጎቪንዳ ሳርቫ ካራና ካራናም (ብሰ 5 1) "ጐቪንዳ" ወይንም ክርሽና የመነሻዎች ሁሉ መነሻ ነው፡፡ እርሱም ቀዳማዊው ጌታ ነው፡፡ ስለዚህ አብዩ የመላእክት ጌታ "ሳክ ቺት አናንዳ ቪግራሀ" ተብሎ ይታወቃል፡፡ "ብራህማን" ተብሎ የሚታወቀው እና የሰብዓዊነት ባህርይ የሌለው የጌታ ቅርጽ ወይንም ወገን ዓብዩ ጌታ ዘለዓለማዊ ወይንም "ሳት" መሆኑን እንድንረዳ የሚያስችለን ነው፡፡ "ፓራማትማ" ተብሎ የሚታወቀው እና በልባችን ውስጥ የሚገኘው የዓብዩ ጌታ አካል ደግሞ ዘለዓለማዊነትን እና ሙሉ እውቀትን የያዘ የአምላክ አካል እንደመሆኑ ልንረዳ ያስችለናል፡፡ (ሳት ቺት) ነገር ግን ሽሪ ክርሽናን እንደ አብዩ የመላእክት ጌታ መረዳት ማለት ስለ ዓብዩ ጌታ መላ የመንፈሳዊ ባህርዮቹን ሁሉ መረዳት ማለት ነው፡፡ እነዚህም “ሳት” “ቺት” እንዲሁም “አናንዳ” ናቸው፡፡ እነዚህም መላውን ቅርፅ ያሟላሉ፡፡ “ቪግራሀ” ማለት ፎርም ወይንም ቅርፅ ማለት ነው፡፡ “አቭያክታም ቭያክቲም አፓናም ማንያቴ ማም አቡድሀያ (ብጊ 7.24) አእምሮዋቸው በመንፈሳዊ እውቀት ያልተሞላ ሰዎች ዓብዩ ጌታ ፎርም ወይንም የሰብአዊ ባህርይ ያለው ዓብይ ሰው እንደሆነ አይረዱትም፡፡ ዓብዩ የመላእክት ጌታ ሰው ነው፡፡ ፍፁም መንፈሳዊ እና ዓብይ ሰው ነው፡፡ ይህም በመላ የቬዲክ ሥነጽሁፎች ሁሉ ተረጋግጦ ተፅፏል፡፡ ”ኒትዮ ኒትያናም ቼታናሽ ቼታናናም“ (ካትሀ ኡፕኒሻድ 2 2 13) እኛም የግል ህይወት ያለን ሰዎች እንደመሆናችን ሁሉ ሁሉም ሰው የእራሱ የሆነ የግል ሕይወት አለው፡፡ ሁላችንም የግል የሆነ ሕይወት አለን፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አብዩ የመላእክት ጌታ የበላይ የሆነ ሰው ነው፡፡ ይህንንም ዓብዩ ጌታን እንደ የበላይ ፍፁም ሰው መሆኑን መረዳት ማለት መላ መንፈሳዊ ባህርዩን መረዳት ማለት ነው፡፡ የመላው ቪግራሀ ወይንም ፎርም (ቅርፅ) ሳት ቺት አናንዳን አሟልቶ የያዘ ነው፡፡ ቪግራሀ ማለት ፎርም ወይንም ቅርጽ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የዓብዩ ጌታ አካል ፎርም የሌለው አይደለም፡፡ ዓብዩ ጌታ ፎርም የሌለው ከሆነ ወይንም ከምንም ነገር ቢሆን ያነሰ ከሆነ ዓብዩ ጌታ በሁሉም ነገር የተሟላ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ ዓብዩ ጌታ ሁሉንም አሟልቶ የያዘ መሆን አለበት፡፡ ይህም በምናውቀውም ሆነ በግምታችን አሻግረን በማናውቀው ነገር ሁሉ አሟልቶ የቀረበ መሆን አለበት፡፡ አለበለዛ ግን ሙሉ ባህርይ ይዞ የሚገኝ ሊሆን አይችልም፡፡ የተሟላ ፎርም ያለው ዓብዩ የመላእክት ጌታ በመጠን ሊገመት የማይችል ሀይላት አሉት፡፡ "ፓራሽያ ሻክቲር ቪቪድሀይቫ ሽሩያቴ" (ቼቻ ማድህያ 13 65 ገለፃ) ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልጿል፡፡ በነዚህም ጥቅሶች ውስጥ እንዴት የተለያዩ ሀይላት እንዳለው ተገልጿል፡፡ ይህም የምንኖርበት ቁሳዊ ዓለም እራሱ የተሟላ ሆኖ የተፈጠረ ነው፡፡ "ፑርናም ኢዳም" ተብሎም ይታወቃል፡፡ (ሺሪ ኡፕኒሻድ የመጀመሪያው ጥቅስ) በሳንክያ ፍልስፍና እንደተገለፀው፣ ይህ ዓለም ከ24 ንጥረ ነገሮች የተፈጠረ ነው፡፡ ይህም ከ24 ንጥረ ነገሮች የተፈጠረው የቁሳዊው ዓለም ጊዜያዊ ክስተት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ቢሆንም ግን በዚህ ቁሳዊው ዓለም እና ህዋ ውስጥ ለመኖርም ሆነ እራሳችንን ለመንከባከብ የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ቀርቦልን ይገኛል፡፡ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ ከቀረበልንም በላይ ሌላ ምንም ዓይነት ነገር በሌላ ሀይል እንዲቀርብልን የጐደለ ነገር የለም፡፡ ይህ ቁሳዊው ዓለም በግዜው ተዘጋጅቶ እና ተሟልቶ በዓብዩ የመላእክት ጌታ የቀረበልን ነው፡፡ የተፈቀደለትም ጊዜ ሲያበቃ ይኅው የተፈጠረው የቁሳዊው ዓለም በዓብዩ ጌታ ሊደመሰስ ይበቃል፡፡