AM/Prabhupada 0069 - እኔ አልሞትም፡፡

Revision as of 06:07, 29 November 2017 by Sahadeva (talk | contribs) (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Conversation Pieces -- May 27, 1977, Vrndavana

ኪርታናናንዳ:አንተ ደህና ካልሆንክ እኛ ደስተኛ ልንሆን አንችልም: ፕራብሁፓዳ:እኔ ሁልግዜ ደህና ነኝ: ኪትታናናንዳ:ለምን እርጅናህን ለእኛ አትሰጠንም? ፕራብሁፓዳ: ሁሉም ነገር ተስተካክሎ እየሄደ ሳይ:እኔ ደስተኛ እሆናለሁ: ይህ ገላ ማለት ምንድን ነው? ገላ ገላ ነው:እኛ ገላ አይደለንም: ኪርታናናንዳ: ወጣትነቱን ለአባቱ የሰጠው “ፑሩዳስ” አይደለምን? ፕራብሁፓዳ:“ህምም?” ራሜሽቫራ:“ያያቲ” ንጉስ ያያቲ እርጅናውን ነገደ: ኪርታናናዳ:ከልጁ ጋር:ይህን ማድረግ ይቻላል: ፕራብሁፓዳ:(ሳቀ) ማን አደረገ? ራሜሽቫራ:“ንጉስ ያያቲ“:ፕራብሁፓዳ:”አሃ ያያቲ“ ይህ አይሆንም:ለምን?እናንተ የእኔ ገላ ናችሁ: እናንተ መኖር ቀጥሉ:ይህ ለውጥ ስለማያመጣ: ልክ እኔ አሁን ስሰራ:የእኔ መንፈሳዊ አባት ”ጉሩ ማሃራጃ“ በአጠገቤ ነው:”ብሃክቲሲድሃንታ ሰረስቨቲ“ በውን አጠገቤ ላይኖር ይችላል:ነገር ግን በየደረጃው ከእኔ ጋር አለ: እንዲያውን ይህንን ሳልጽፈው አለቀርም: ታማላ ክርሽና:አዎን ይህም በብሃገቨታም ውስጥ ተጽፏል:”ከእርሱ ጋር የሚኖር ለዘለአለም ይኖራል“ ”የእርሱንም ቃል የሚያስታውስ:ለዘለአለም ይኖራል“ ፕራብሁፓዳ:ስለዚህ እኔ አልሞትም: ”ኪርቲር ያስያ ሳ ጂቫቲ“ ”አንድ በጣም ጥሩ ያደረገ ሰው ለዘለአለም ይኖራል“ ሊሞትም አይችልም:በዚህ በተግባራዊው ህይወታችን አለ: በእርግጥ ይህች ምድር አለማዊ ናት ”ካርማ ፕሃላ“ አንድ ሰው በዚህ አለም ላይ እንደ አድራጎቱ:ወደፊት ሌላ ገላ ይይዛል: የአማላክ አገልጋይ ግን:እንዲህ ብሎ ነገር የለም: ሁል ግዜ ክርሽናን የሚያገለግልበትን ገላ ይይዛል:ለእርሱ “ካርማ ፕሃላ” የለም: