AM/Prabhupada 0041 - የአሁኑ ሕይወታችን እርግማን የተሞላበት ነው፡፡



Lecture on BG 9.1 -- Melbourne, June 29, 1974

ሙሉ እውቀት: ብሃገቫድ ጊታን ብታነቡ: ሙሉ በሙሉ የሆነ እውቀት ታገኛላችሁ:: ታድያ ብሃጋቫድ ጊታ ምን ይለናል? "ኢዳም ቱ ጉህያታማም ፕራቫክሽያሚ አናሱያቬ" (ብጊ 9 1) ብሃጋቫን ክርሽና እንዲህ እያለ አርጁናን እያስተማረው ነው:: በዘጠነኛውም ምዕራፍ: እንዲህ ይላል: "ውድ አርጁና ሆይ" "አሁን የምነግርህ ከእውቀቶች ሁሉ በጣም ምስጥራዊ የሆነውን ነው::" "ጉህያታማም" "ታማም" ማለት እጅግ በጣም ጥሩ: እርግጠኛ እና የማያጠራጥር: እንዲሁም የበለጠ ደረጃ ያለው: ማለት ነው:: በሳንስክሪት ቋንቋ: "ታራ ታማ" ማለት: "ታራ" ማለት ተወዳዳሪ: "ታማ" ማለት ደግሞ: የበለጠ ደረጃ ያለው ማለት ነው: እዚህም ላይ: ብሃጋቫን: እንከን የሌለው ፍጹም አምላካችን እንዲህ አለ "ኢዳም ቱ ቴ ጉህያታማም ፕራቫክሽያሚ" "አሁን የምናገረው እውቀት ከሁሉም እውቀት በላይ: በጣም ምስጢራዊ የሆነውን እውቀት ነው:" "ግያናም ቪግናና ሳሂታም" ይህም እውቀት የሃሳብ ግምት ያልሆነ: ሙሉ እውቀት ያለው ነው: "ግናናም ቪግናና ሳሂታም" ቪግናና ማለት: "ሳይንስ" ወይንም ተግባራዊ የሆነ ማስረጃ ማለት ነው:: ስለዚህ "ግናናም ቪግናናም ሳሂታም ያጅ ግናትቫ" ይህን ትምህርት ብትማሩ: "ያጅ ግናትቫ ሞክስያሴ ሱብሃት" "አሹብሃት" ሞክስያሴ ማለት ነፃ ትወጣለህ ማለት ነው:: አሹብሃት ማለት ደግሞ ተስፋ የሌለው ማለት ነው:: ተስፋ የሌለው: የአሁኑ ህይወታችን እና በአሁኑ ግዜ: ይህንን አለማዊ ገላ እስከያዝን ድረስ: የአሁኑ ህይወታችን ተስፋ ቢስ የሆነ ደረጃ ላይ ነው ያለው:: ሞክስያሴ አሹባት: አሹባት ማለት ተስፋ የሌለው ማለት ነው::