Please join, like or share our Vanipedia Facebook Group
Go to Vaniquotes | Go to Vanisource


Vanipedia - the essence of Vedic knowledge

AM/Prabhupada 0052 - በብሀክታ እና በካርሚ በሀከል ያለው ልዩነት፡፡

From Vanipedia


በብሀክታ እና በካርሚ በሀከል ያለው ልዩነት፡፡
- Prabhupāda 0052


Lecture on SB 1.2.9-10 -- Delhi, November 14, 1973

በብሀክቲ እና በካርማ መሀከል ያለው ልዩነት ይህ ነው፡፡ ካርማ ማለት ለዓለማዊ የግል ስሜታዊ ደስታ መጣር ማለት ነው፡፡ ብሀክቲ ማለት ደግሞ ዓብዩ ጌታን ለማስደሰት መጣር ማለት ነው፡፡ እነዚህም የተመሳሰሉ ጥረቶች ናቸው፡፡ ስለዚህም ብዙ ሰዎች በብሀክታ (መንፈሳዊ አገልጋይ) እና በካርሚ (ዓለማዊ ሰው) መሀከል ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ ለማወቅ ያዳግታቸዋል፡፡ ካሪሚ የግል ስሜቱን ለማስደሰት የቆመ ነው፡፡ ብሀክታ ደግሞ የዓብዩ ሽሪ ክርሽናን ስሜት ለማስደሰት የቆመ ነው፡፡ በእነዚህም እንቅስቃሴዎች ስሜቶቻችን ሲረኩ እናያለን፡፡ ቢሆንም ግን የክርሽናን ስሜት ስናረካ ይህ “ብሀክቲ” ይባላል፡፡ "ርሺኬሻ ርሺኬሻ ሴቫናም ብሀክቲር ኡችያቴ" (ቼቻ፡ ማድህያ Madhya 19.170) ርሺካ ማለት ስሜት ወይንም የፀዳ ስሜት ማለት ነው፡፡ ይህንንም ባለፈው ግዜ አስረድቼ ነበር፡፡

"ሳርቮ ፓድሂ ቪኒር ሙክታም ታት ፓራትቬና ኒርማላም ርሺኬና ርሺኬሻ ሴቫናም ብሀክቲር ኡችያቴ"
(ቼቻ፡ ማድህያ Madhya 19.170)

ብሀክቲ ማለት የምትሰሩትን ስራ አቁሙ ማለት አይደለም፡፡ ብሀክቲ እውቀት ባልተሞላበት ስሜታዊ እንቅስቃሴ የተመረኮዘ ሩጫ አይደለም፡፡ ይህ ብሀክቲ አይደለም፡፡ ብሀክቲ ማለት ስሜቶቻችንን ሁሉ የስሜት ሁሉ ጌታ ለሆነው ዓብዩ ጌታ አገልግሎት ማቅረብ ማለት ነው፡፡ ይህ ብሀክቲ ይባላል፡፡ ስለዚህ ክርሽና "ርሺኬሽ" ተብሎ ይታወቃል፡፡ ርሺኬሽ ማለት ስሜት ማለት ነው፡፡ ርሺካ ኢሻ ማለት የስሜቶቻችን ሁሉ ተቆጣጣሪ ማለት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ስሜቶቻችን ለብቻ ተነጥለው ሊንቀሳቀሱ አይችሉም፡፡ ይህንንም ለመረዳት እንችላለን፡፡ ክርሽና ስሜቶቻችንን እየመራ ይገኛል፡፡ "ሳርቫስያ ቻሃም ህርዲ ሳኒቪስቶ ማታህ ስምርቲር ግያነም አፖሀነም ቻ" (ብጊ፡ 15.15) "ማታህ ስምርቲር ግያነም አፖሀነም ቻ" ሳይንቲስት ውጤታማ ስራ የሚሰራው ክርሽና ስለሚረዳው ነው፡፡ ለብቻው ግን ምንም ዓይነት ስራ ለመስራት አይችልም፡፡ ይህም የሚቻል አይደለም፡፡ ሳይንቲስቱ ፍላጎቱ ለምርምር ስለመሆኑ ክርሽና ፍላጎቱን ያሟላለታል፡፡ በዚህም ግዜ ክርሽና የሚያስፈልገውን ሁሉ ያቀርብለታል፡፡ ስራውን የሚሰራው ግን ክርሽና ነው፡፡ እነዚህም በኡፓኒሻድ ውስጥ ተገልፀዋል፡፡ ክርሽና ሳይሰራ፣ ክርሽና ሳያይልን ለማየት እንኳን አንችልም፡፡ ይህም ልክ የፀሀይ ጨረር በብረህማ ሰሚታ ውስጥ ለምሳሌ እንደተጠቀሰው ነው፡፡ “ያክ ቻክሱር ኢሻ ሳቪታ ሳካላ ግራሀናም” ፀሀይ የሽሪ ክርሽና አንዱ ዓይን ናት፡፡ “ያክ ቻክሱር ኢሻ ሳቪታ ሳካላ ግራሀናም ራጃ ሳማስታ ሱራ ሙርቲር አሼሻ ቴጃሀ” “ያስያግናያ ብህራማቲ ሳምብርትታ ካላ ቻክሮ ጎቪንዳም አዲ ፑሩሻም ታም አሀም ብሀጃሚ” ፀሀይ አንዷ የሽሪ ክርሽና ዓይን እንደመሆንዋ... የፀሀይ ጨረርም ስለምትመጣልን እና ፀሀይም ስለምትመለከተን እኛም ለማየት እንችላለን፡፡ ስለዚህም ለብቻችን ያለ ዓብዩ ጌታ ድጋፍ ለማየት አንችልም፡፡ ባለን ዓይኖቻችን በጣም ኮርተን እንገኛለን፡፡ ታድያ ብርሀን በሌለበት ዓይናችን ምን ዋጋ ሊኖረው ይችላል? ያለ ብርሀን ለማየት አንችልም፡፡ የኢሌክትሪክ ሀይል እራሱ የሚመነጨው በፀሀይ ሀይል ነው፡፡ ስለዚህ ክርሽና ሲያየን እኛም ለማየት እንችላለን፡፡ ይህ ነው ደረጃችን፡፡ ስለዚህ ስሜቶቻችን እንደሚከተለው ተገልፀው ይገኛሉ፡፡ በብሀገቨድ ጊታ እንዲህ ተብሎ ተገልጿል፡፡ “ሳርቫታህ ፓኒ ፓዳም ታት” “ሳርቫታ ፓኒ ፓዳ” የክርሽና እጆች እና እግሮች በየቦታው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ምንድን ናቸው? እጆቼ፣ እጆቻችሁ፣ እግሮቻችሁ እነዚህ ሁሉ የክርሽና ናቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በመላ ዓለም ቅርንጫፎች አለኝ ሊል ይችላል፡፡ እነዚህም ቅርንጫፎች የሚተዳደሩት በዋናው በባለቤቱ ቁጥጥር ስር ይሆናል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ክርሽናም ሁሉን ያስተዳድራል፡፡ ስለዚህም ክርሽና “ርሺኬሻ” ተብሎ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ብሀክቲ ማለት የእኛን ርሺኬሻ ወይንም ኢንድሪያ ወይንም ስሜቶቻችንን በጌታ አገልግሎት ላይ ማሰማራት ማለት ነው፡፡ ይህም ለስሜቶቻችን ጌታ አገልግሎትን ማቀረብ ማለት ነው፡፡ ይህም ፍፁም ጥሩ የሆነ ሕይወት ይሰጠናል፡፡ ይህም ትክክል በሆነ መንገድ ላይ መሰማራት ማለት ነው፡፡ ቢሆንም ግን ስሜቶቻችንን ለግል ዓለማዊ ደስታ መጠቀም ስንጀምር ግን ይህ ካርማ ይባላል፡፡ ይም የዓለማዊ ሕይወት ይባላል፡፡ ስለዚህ ለብሀክታ ወይንም አገልጋይ ምንም ዓለማዊ ሕይወት አይኖረውም፡፡ ይህም “ኢሳቫስያም ኢዳም ሳርቫም” (ኢሺ፡ 1) ብሀክታ (አገልጋይ) ሁሉም ነገር የክርሽና እንደሆነ የተረዳ ነው፡፡ “ኢሻቫስያም ኢዳም ሳርቫም ያት ኪንቻ ጃጋታም ጃጋት ቴና ትያክቴና ብሁንጂትሀ” ሁሉም ነገር የሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ይህም ሁሉን ክርሽና የሰጠንን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ይህም ልክ እንደ ባለቤቱ ይቆጠራል፡፡ ባለቤቱ ለሰራተኞቹ የሚያካፍላቸው ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ “ይህንን ወስዳችሁ መደሰት ትችላላችሁ” ይህም ፕራሳድ ሊሆን ይችላል፡፡ “ፕራሳዴ ሳርቫ ዱህክሀናም ሃኒር አስዮፓጃ” ሕይወት ማለት ይህ ነው፡፡ የክርሽና ንቃታችሁን ያዳበራችሁ ከሆነ ሁሉም ነገር የክርሽና ስለመሆኑ በቀላሉ ለመረዳት ትችላላችሁ፡፡ ይህም እጆቼን እና እግሮቼን ሁሉ ይጨምራል፡፡ ሁሉም ነገር የክርሽና ነው፡፡ መላ የገላዬ ወገኖች ሁሉ የክርሽና ናቸው፡፡ ስለዚህም ሁሉንም ነገር በክርሽና አገልግሎት ላይ ማዋል ይገባናል፡፡

“አንያብሂላሲታ ሱንያም ግያና ካርማዲ አናቭርታም አኑኩልዬና ክርሽናኑ ሺላናም ብሀክቲር ኡታማ”
(ብረሰ፡ 1፡1፡11)

ይህንንም አርጁና ፈፅሞታል፡፡ በመጀመሪያ ባለመዋጋት የግሉን ስሜት ለማርካት ፈለገ፡፡ ብሀገቨድ ጊታን ከክርሽና ከሰማ በኋላ ግን ለመዋጋት ፈቃደኛ ሆነ፡፡

“ክርሽና ዓብዩ ጌታ ነው፡፡” “አሀም ሳርቫስያ ፕራብሀቮ ማታህ ሳርቫም ፕራቫርታቴ ኢቲ ማትቫ ብሀጃንቴ ማም ቡድሀ ብሀቫ ሳማንቪታሀ”
(ብጊ፡ 10.8)

እነዚህ ነጥቦች ሁሉ በብሀገቨድጊታ ውስጥ በግልፅ ተተንትነው ይገኛሉ፡፡ ይህም የመንፈሳዊ ትምህርት ሁሉ መሰረታዊ እውቀት ነው፡፡ የብሀገቨድ ጊታም ትምህርት ተረድተን በእምነት የምንከተለው ከሆነ ለሽሪ ክርሽና ሙሉ ልቦናችንን ለመስጠት አያዳግተንም፡፡ ክርሽናም የሚፈልገው ይህንኑ ነው፡፡ “ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ” (ብጊ፡ 18.66) ይህንንም ይፈልገዋል፡፡ ይህንንም ስርዓት መከተል ስንጀምር ይህ “ሽራድሀ” ወይንም እምነት ይባላል፡፡ የሽራድሀ ትርጉም ምንድን ነው? ይህም በካቪራጅ ጎስዋሚ ተተንትኖ ተገልፆልናል፡፡