AM/Prabhupada 0075 - ወደ ጉሩ ወይንም መምህር መሄድ ይገባችኋል፡፡

From Vanipedia


ወደ ጉሩ ወይንም መምህር መሄድ ይገባችኋል፡፡
- Prabhupāda 0075


Lecture on SB 1.8.25 -- Mayapur, October 5, 1974

አንድ ሰው ከፍተኛው የሕይወታችን ዓላማ ምን እንደሆነ መጠየቅ ሲጀምር፤ ይህም ”ብራህማ ጂግናሳ“ ይባላል፡፡ በዚህም ግዜ ጉሩ ወይንም መንፈሳዊ መምህር መቅረብ ይገባዋል፡፡ ”ታስማድ ጉሩም ፕራፓድዬታ“”አሁን ስለከፍተኛው የሕይወትህ ዓላማ ምን እንደሆነ መጠየቅ ስለጀመርክ፤ ጉሩ ወይንም መምህር መቅረብ ይገባሀል፡፡“ ”ታስማድ ጉሩም ፕራፓድዬታ“ ማንን መቅረብ ይገባናል? "ጂግናሱ ሽሬያ ኡታማም” “ኡታማም” ይህ ኡታማም ማለት ከድንቁርና በላይ የሆነ ማለት ነው፡፡ መላ ዓለም በድንቁርና ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ከዚህ ከድንቁርና በላይ ለመሆን ከፈለገ፤ “ታማሲ ማ ጅዮቲር ጋማ” የቬዲክ ምክር እንዲህ ይላል፡፡ “እራስህን በዚህ ድንቁርና ውስጥ አታስቀምጥ፡፡ ብርሀንም ወዳለበት ቦታ ሂድ፡፡” ይህም ብርሀን “ብራህማን” ወይንም መንፈሳዊነት ነው፡፡ “ብራህማ ጂግናሳ” ይህም ማለት፤ የሕይወት ከፍተኛ ዓላማ ምን እንደሆነ የሚጠይቅ ማለት ነው፡፡“ኡታማ” “ዱድጋታ ታማ ያስማት” “ኡድጋታ ታማ” ታማ ማለትድንቁርና ማለት ነው፡፡ በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ምንም ድንቁርና የለም፡፡ “ግያና” የማያቫዲ ፈላስፋዎች “ግያና“ ብቻ ብለው ያወራሉ፡፡ ”ግያናቫን“ ቢሆንም ግን ”ግያና“ (የመንፈሳዊ እውቀት) የተወሰነ ዓይደለም፡፡ የተለያዩ ዓይነት ግያናዎች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ በቭርንዳቫን የሽሪ ክርሽና የትውልድ ቦታ ላይ ”ግያና“ ነበር፡፡ ነገር ግን የነበሩት መንፈሳዊ ንቃት እና እውቀቶች የተለያዩ ነበሩ፡፡ ለምሳሌ አንዱ እንዴት ሽሪ ክርሽናን በፍቅር እንደሚያገለግል ንቃቱ እና እውቀቱ ነበረው፡፡ ሌላው ሽሪ ክርሽናን እንደጓደኛው አድርጐ ለመውደድ ፍላጎት ነበረው፡፡ ሌላው የሽሪ ክርሽናን ወሰን የሌለው ሀብት ለማወደስ ፍላጎት ነበረው፡፡ ሌላው ሽሪ ክርሽናን እንደ አባት ወይንም እንደ እናት ሆኖ ፍቅሩን ለማሳየት ፍላጐቱ ነበረው፡፡ ሌሎቹ ሽሪ ክርሽናን በመንፈሳዊነት የተመሰረተ የፍቅር ጓደኛቸው አድርገው ለመውደድ ፍላጎት ነበራቸው፡፡ ይህም ከትዳራቸውም ውጪ ሊሆን ይችላል፡፡ ሌሎች ሽሪ ክርሽናን እንደ ጠላት አድርገው በመቅረብ የመቅረብ ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ይሹ ነበር፡፡ ለዚህም ምሳሌው ”ካምሳ“ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም በቭርንዳቫን ታሪክ ውስጥ ተተንትኖ የቀረበ ነው፡፡ እርሱም ስለ ሽሪ ክርሽና ከማሰላሰል ያቆመበት ግዜ አልነበረም፡፡ ይህም እንዴት አድርጐ ሽሪ ክርሽናን ለመግደል እንደሚችል ነው፡፡ ”ፑታና“ የምትባለውም ክርሽናን ወዳ የቀረበች አስመስላ የመጣች ናት፡፡ ይህም ጡትዋን እንዲጠባ በሕፃንነቱ እያለ በመቅረብ ነው፡፡ በልቧ የነበረው ዓላማ ግን በተመረዘው ጡቷ ሽሪ ክርሽናን ለመግደል ነበረ፡፡ ቢሆንም ግን ይህ አቀራረብ ለክርሽና ጡቷን በማቅረብ በመሆኑ በሽሪ ክርሽና አቀራረቧ የፍቅር አቀራረብ ሆኖ በተለየ መንገድ ተወስዶ ነበረ፡፡ ”አንቫያት“ ስለዚህ ሽሪ ክርሽና ”ጃጋድ ጉሩ“ ወይንም የሕዋ መምህር ይባላል፡፡ እርሱም የመላ ሕዋ እና የመጀመሪያው መምህር ነው፡፡ ይህም የመጀመሪያው መምህር በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ትምህርቱን ሰጥቶን ይገኛል፡፡ እኛ ተንኮለኞች ሆነን ግን ይህንን ትምህርት ስንወስድ አንታይም፡፡ አያችሁን? ስለዚህ እኛ ”ሙድሀ“ ወይንም ድንቁርና እንደተሞላባቸው ሰዎች እንቆጠራለን፡፡ ከጃጋድ ጉሩ ወይንም ከመንፈሳዊ መምህሩ ትምህርትን በመውሰድ በጥሞና የማይከታተል ሰው ሁሉ እንደ ሙድሀ ወይንም እንደ ደንቆሮ ይቆጠራል፡፡ ለዚህም መለኪያችን አንድ ሰው ሽሪ ክርሽናን የማያውቅ ከሆነ ነው፡፡ ሽሪ ክርሽናን የማያውቅ ከሆነ እንዴት አድርጎ ብሀገቨድ ጊታን ለመከተል ይችላል? ይህንንም ዓይነት ሰው እንደ ተንኮለኛ እንወስደዋለን፡፡ ይህም ምንም እንኳን የአገሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆንም እንኳን ነው፡፡ ወይንም የፍርድ ቤት ዋነኛው ዳኛም ሊሆን ይችላል፡፡ጠቅላይ ሚኒስቴርም ሆነ ወይንም የፍርድ ቤቱ ታላቁ ዳኛ ሁሉም እንደ ”ሙድሀ“ ወይንም ደንቆሮ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ይህስ?" እንዴት-ሊሆን: (BG 7.15). "ቻለ ”ማያ ፓህርታ“ (ብጊ፡ 7 15). ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ስለ ሽሪ ክርሽና ምንም እውቀት የሌላቸው እና በማያ ወይንም በሀሰት እይታ ዓይናቸው የተሸፈነ ሰዎች ናቸው፡፡." ”ማያያፓህርታ-ጅያና አሱራም bhāvam āśritāḥ. C'est pourquoi il est mūḍh ይታወቃሉ፡፡ (በድንቁርና ውስጥ የሚገኙ፡፡)a. ይህም በቀጥታ ትምህርቱን ስናቀርበው ነው፡፡ ቢሆንም ግን ለሕዝብ ስናስተምር በለሰለሰ አነጋገር መሆን ይገባዋል፡፡ አለበለዛ አድማጩን ለመረበሽ እንበቃ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሽሪ ክርሽናን እንደ ጃጋድ ጉሩ ወይንም ዓብዩ መምህር የማይቀበል ሁሉ፤ ወይንም ትምህርቱን የማይቀበል ሁሉ እንደ ተንኮለኛ ይታያል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሙድሀ ወይንም ተንኮለኛ በጃገናት ፑሪ ከተማ ውስጥ ነበረ፡፡ እንደዚህም ብሎ ይናገር ነበር፡፡ ”የወደፊት ትውልድህን ስታገኝ እንዲህ ማድረግ ትችላለህ...“ ይህም የሙድሀ ወይም የተንኮለኛ አስተሳሰብ ነው፡፡ ለምን? ምክንያቱም በድንቁርና ውስጥ እያለ እራሱን እንደ ጃጋድ ጉሩ ወይንም ዓብይ መምህር አድርጎ ስለሚያስብ ነው፡፡ እንዲህም ሲል ይገኛል፡፡ ”እኔ ጃጋድ ጉሩ ወይንም የመላ ሕዋ መምህር ነኝ፡፡“ ነገር ግን ጃጋድ ጉሩ የመሆን ብቁነት የለውም፡፡ ጃጋድ ወይንም ሕዋ ምን እንደሆነ እንኳን ያላየ ሰው ነው፡፡ አስተሳሰቡም እንደ እንቁራሪት ይቆጠራል፡፡ ሆኖም ግን እኔ ጃጋድ ጉሩ ነኝ ብሎ ያስባል፡፡ ስለዚህ ሽሪ ክርሽና እንደገለፀው ይህ ዓይነቱ ሰው ”ሙድሀ“ ወይንም ደንቆሮ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሙድሀ ተብሎ የሚታወቀውም የሽሪ ክርሽናን ትምህርት የተረዳ እና ያልተቀበለ በመሆኑ ነው፡፡