AM/Prabhupada 0076 - ክርሽናን በሁሉም ቦታ ለማየት ሞክሩ፡፡

From Vanipedia


See Kṛṣṇa Everywhere - Prabhupāda 0076


Ratha-yatra -- San Francisco, June 27, 1971

አይኖቻችን በአምላካችን ፍቅር የተሞሉ ሲሆኑ፡ አምላክን የትም ቦታ ቢሆን ለማየት እንችላለን፡፡ ይህ የ “ሻስትራ” መጽሃፈ ቅዱሶች መመሪያ ነው፡፡ የአምላክን ፍቅር በማዳበር፡ የመንፈሳዊ ዓይኖቻችንን ኃይል መገንባት ይኖርብናል፡፡ “ፕሬማንጃና ቹሪታ ብሃክቲ ቪሎቻኔና” (ብጊ 5 38) የአንድ ሰው የክርሽና ንቃት በደንብ ሲዳብር፡ አምላክን በየደቂቃው፡ በልቡም ሆነ በየቦታው፡ የማየት ችሎታ ይኖረዋል፡፡ ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበር የተቋቋመው፡ ይህንን ለማበርከት ነው፡፡ መላው ህዝብ እንዴት አምላክን ወይንም ክርሽናን ለማየት እንደሚችል ለማስተማር ነው፡፡ ይህን ትምህርት በተግባር ብናውለው፡ ክርሽናን ለማየት ያበቃናል፡፡ ክርሽናም እንዲህ ብሏል፡ “ራሶ ሃም አፕሱ ኮንቴያ” (ብጊ 7 8 ) ክርሽና እንዲህ ብሏል፡ “እኔ የውሃ ቅምሻ ባህሪው ነኝ” ሁላችንም ውሃ በቀን በቀን እንጠጣለን፡፡ አንዴም ብቻ ሳይሆን፡ ከአንዴም፡ ሁለት ሶስቴም፡ ከዚያም በላይ፡፡ ውሃም ስንጠጣ፡ የውሃ ቅምሻና የጥም እርካታችን፡ ክርሽና መሆኑን ብቻ እንኳን ብንገነዘብ፡ ወዲያውኑ የክርሽና ንቃታችን ሊዳብር ይችላል፡፡ የክርሽናን ንቃት ማደበር በጣም አስቸጋሪ ነገር አይደለም፡፡ ልምምድ ማደረግ ብቻ ነው የሚያስፈልገን፡፡ ይህም የውሃ ጥም ርካት፡ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ የክርሽናን ንቃታችንንም ለማዳበር፡ ጥሩ ምሳሌ ሆኖ ይገኛል፡፡ ውሃ በጠጣን ቁጥር፡ ጠጥተንም እንዳበቃን፡ የውሃ ጥማችን ወዲያውኑ ይረካል፡፡ በዚህም ግዜ የእርካታው ሃይል የሚመጣው፡ ከክርሽና መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ “ፕራብሃስሚ ሻሺ ሱራዮህ” ክርሽና እንዲህ ይላል፡ “እኔ የፀሃይ ነጸብራቅ ነኝ፡፡ እኔ የጨረቃም ነጸብራቅ ነኝ፡፡” በቀን ላይ ፀሃይ ስትወጣ፡ ሁላችንም ለማየት እንችላለን፡፡ ፀሃይም በቀን ላይ ስትወጣ፡ ክርሽናን ወዲያውኑ ለማስታወስ እንችላለን፡ “ይኅው ክርሽና” ጨረቃም በማታ ስትወጣ፡ ወዲያውኑ ክርሽናን ለማስታወስ እንችላለን፡፡ “ይኅው ክርሽና” እንዲህም እያሰላሰልን፡ በተለያዩ መንገዶች ክርሽናን ለማሰታወስ እንችላለን፡፡ በብሃጋቨድ ጊታም በ 7 ኛው ምዕራፍ ብዙ ይህንን የመሰሉ ምሳሌዎች ተሰጥተዋል፡፡ ይህንንም የመሰለ የክርሽናን ንቃትም በደንብ ለመለማመድ፡ ምዕራፉን በጥሞና ማንበን ይገባችኋል፡፡ ይህንንም ፈለግ በመከተል እና የክርሽናንም ፍቅር እያዳበራችሁ ስትመጡ፡ ክርሽና ሁሉ ቦታ ለማየት ትችላላችሁ፡፡ ማንም ክርሽናን እንድታዩ ሊረዳችሁም አያስፈልግም፡፡ በእራሳችሁ ፍቅር እና ትጉህነት፡ ክርሽና እራሱን እናንተ ፊት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ይህም ካላችሁ ፍቅር እና አገልግሎታችሁ የመነጨ ነው፡፡ “ሴቮንሙክሄ ሂ ጂቫዶ ስቫያም ኤቫ ስፕሁራቲ አዳሃ” (ብሰ 1 2 234) አንድ ሰው፡ ክርሽናን በማገልገል በልቦናው የተመሰጠ ከሆነ፡ እንዲህ ብሎም ሲረዳ፡ “እኔ ለዘልአለም የክርሽና አገልጋይ ነኝ” በዚህም አይነት የቅን ልቦና ይዘት፡ ክርሽና ለመታየት እድሉን ይሰጠናል፡፡ ይህም በብሃገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልጾልናል፡፡ ቴሻም ሳታታ ዩክታናም ብሃጃታም ፕርቲ ፑርቫካም ዳዳሚ ቡድሂ ዮጋም ታም ዬና ማም ኡፓያንቲ ቴ (ብጊ 10 10)