AM/Prabhupada 0100 - እኛ ከክርሽና ጋር የዘለዓለም ግኑኝነት አለን፡፡



Lecture on SB 6.1.8 -- New York, July 22, 1971

ከሽሪ ክርሽና ጋር ለዘለዓለም የተዛመድን ነን፡፡ ይህም ዝምድናችን በአሁኑ ግዜ ተረስቷል ወይንም ወደታች ተገፍቶ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት ከሽሪ ክርሽና ጋር ምንም ግኑኝነት ወይም ዝምድና የለንም ብለን እናስባለን፡፡ ይህ ግን እውነት አይደለም፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዳችን የክርሽና ወገን እና ከፊል ነን፡፡ ግኑኝነታችን ወይም ዝምድናችንም ዘለዓለማዊ ነው፡፡ ማድረግ የሚገባን ግን ይህንን ዝምድና ማነቃቃት ብቻ ነው፡፡ ይህም የክርሽና ንቃት ይባላል፡፡ የክርሽና ንቃት ማለትም አሁን ካለን የዓለማዊ ንቃት የተለየ ማለት ነው፡፡ እኔ ሕንድ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡፡ ሌላው ደግሞ እኔ አሜሪካዊ ነኝ ብሎ ያስባል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ ይህ ነኝ ወይም እንዲህ ነኝ በማለት ያስባሉ፡፡ ትክክለኛው አስተሳሰብ ግን “እኔ የሽሪ ክርሽና ነኝ” ማለቱ ነው፡፡ ይህም የክርሽና ንቃት ነው፡፡ “እኔ የክርሽና ነኝ” በዚህም ከክርሽና ጋር ባለን ዝምድና ክርሽና የሁሉም በመሆኑ እኔም የሁሉ እሆናለሁ፡፡ ይህንንም መረዳት ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ በሕንድ አገር ውስጥ አንዲት ልጃገረድ አንድ ወንድ ልጅን ስታገባ በእናንተም አገር ወይም በማንኛውም አገር ይህ ስርዓት ያለ ነው፡፡ ይህም የወንድም ልጅ ያገባችውን ሴት አክስቴ ብሎ ይጠራታል፡፡ እርስዋም በትዳሯ አክስት ሆነች ማለት ነው፡፡ ይህም ከባሏ ጋር ባላት ዝምድና ምክንያት ነው፡፡ ከትዳሯ በፊት ግን አክስት አልነበረችም፡፡ ነገር ግን ከባሏ ጋር በትዳር ስትዛመድ ግን አክስት ለመሆን በቃች፡፡ የባሏም ወንድም ልጅ የእርሷ ወንድም ልጅ ለመሆን በቃ፡፡ ይህንን ምሳሌ ለመረዳት ሞክሩ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ቀድሞ ከሽሪ ክርሽና ጋር የነበረንን ግኑኝነት ወይንም ዝምድና ብናጠናክር ክርሽና ለሁሉም እንደመሆኑ እኛም ለሁሉ ለመሆን እንበቃለን፡፡ ይህም ትክክለኛው የትእይንተ ዓለም ፍቅር ነው፡፡ ይህ ሰው ሰራሹ የዓለም ዓቀፉ ፍቅር የሚባለው ከክርሽና ጋር ያለንን ዝምድና ካላጠናከርን ይህ ፍቅር ሊቋቋም አይችልም፡፡ ለምሳሌ እናንተ አሜሪካዊ ናችሁ፡፡ ለምን? ምክንያቱም የተወለዳችሁበት አገር በመሆኑ ነው፡፡ እንደዚሁም ሌላው አሜሪካዊ የአገራችሁ ሰው እና ወገናችሁ ነው፡፡ ነገር ግን ዜግነታችሁን ብትቀይሩ ከሌላው አሜሪካዊ ጋር ያላችሁ የዜጋ ግኑኝነት ይቋረጣል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ከሽሪ ክርሽና ጋር ያለንን ግኑኝነት እንደገና ማቋቋም እና ማጠናከር ይኖርብናል፡፡ ይህንንም ካደረግን ዓለም አቀፉ ወንድማማችነት፣ ፍትህ፣ ሰላም እና ብልፅግና ይሰፍናል፡፡ አለበለዛ ግን ይህ ሁሉ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህም በመሀል መገኘት የሚገባው ዓብዩ አምላክ ባለመኖሩ ነው፡፡ ይህም ከጐደለ እንዴት ፍትህ እና ሰላም ሊኖር ይችላል? ይህ የማይቻል ነገር ነው፡፡ ስለዚህ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ የሰላም ፎርሙላ ተሰጥቷል፡፡ ይህም የሰላም ፎርሙላ ክርሽና ብቻ የደስታ ተቀባይ መሆኑን መገንዘብ ነው፡፡ ለምሳሌ በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ በመሀከል የሚገኘው ሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ምግብ ብናዘጋጅ ለሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ለራሳችን ደስታ ምግብ አናዘጋጅም፡፡ ምንም እንኳን ዞሮ ዞሮ ምግቡን የምንመገብ ብንሆንም የምናዘጋጀው ግን ለሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ምግብ ስናዘጋጅ ለራሳችን ነው ብለን አናስብም፡፡ ምግቡን የምናዘጋጀው ግን ለሽሪ ክርሽና ደስታ ነው፡፡ ወደ ውጪ በመውጣትም ገንዘብ ስንሰበስብ ለሽሪ ክርሽና ደስታ ነው፡፡ ገንዘብ ለመሰብሰብ የወጡትም የኪርታን ግሩፕ ለግላቸው የሆነ ጥቅምን በማሰብ ስለሆነ አይደለም፡፡ ይህ አይደለም፡፡ ነገር ግን ገንዘብ የሚሰበስቡት እና መፃህፍትን የሚያድሉት የክርሽናን ንቃት ለሰዎች በማደል ክርሽናን ለማስደሰት ብለው ነው፡፡ የተሰበሰበውም ገንዘብ ክርሽናን ለማገልገል እና ለማስደሰት ይውላል፡፡ ይህንንም በመሰለ መንገድ ይህንን ስርዓት ስንከተል ማለትም ሁሉም ነገር ለክርሽና ሲሆን ይህ የክርሽና ንቃት ይባላል፡፡ ይህም ማለት የምናደርገውንም መቀየር አያስፈልገንም፡፡ መቀየር የሚገባን ግን ንቃታችንን ወይንም አስተሳሰባችንን ነው፡፡ “የማደርገው ነገር ሁሉ ለእኔ ሳይሆን ለክርሽና ደስታ መሆን አለበት” በዚህም መንገድ የክርሽና ንቃታችንን ከፍ ብናደርግ ወደ ዋነኛው ንቃታችን ተመለስን ማለት ነው፡፡ በዚህም መንገድ ደስተኞች ለመሆን እንችላለን፡፡ ወደዚህም ወደ ዋነኛው የሽሪ ክርሽና ንቃታችን ካልተመለስን በተለያየ ዲግሪ እንደሚገኝ የማይረባ ሰው እንሆናለን፡፡ ማናቸውም ሰው ቢሆን በክርሽና ንቃት ያልበለፀገ ከሆነ አንደበቱ እንዳልተስተካከለ እብድ ሰው ይቆጠራል፡፡ ምክንያቱም ንግግሩ እና ስራው ሁሉ ለጊዜያዊ እና ለሚያልፍ ነገር ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ዓለማዊ ነገር ሁሉ የሚያልፍ ነው፡፡ ነገር ግን ነፍስ ዘለዓለማዊ ናት፡፡ ስለዚህ ጊዜያዊ የሆነ ስራ ሁሉ ዋነኛው ስራችን አይደለም፡፡ ዋነኛው ስራችን ግን ለሚያዛልቀን እና ዘለዓለማዊ ጠቀሜታ ላለው ነገር መሆን ይገባዋል፡፡ ይህም ዘለዓለማዊ እንቅስቃሴ ሽሪ ክርሽናን ማገልገል ነው፡፡ ለምሳሌ ይህ ጣቴ የገላዬ ወገን ነው፡፡ የጣቴም ዘለዓለማዊ ስራ ገላዬን ማገልገል ነው፡፡ ከዚህም ውጪ ሌላ ምንም ዓይነት ስራ ሊኖረው አይችልም፡፡ ይህም የጣቴ ትክክለኛው ደረጃ ነው፡፡ መላ ገላዬንም ለማገልገል ካልቻለ ሕመምተኛ ጣት ነው ማለት ነው፡፡ ክርሽና ዘለዓለማዊ እንደመሆኑ እኛም እንደዚሁ ዘለዓለማዊ ነን፡፡ “ኒትዮ ኒትያናም ቼታናስ ቼታናናም (ካትሀ ኡፓኒሻድ 2 2 13) እነዚህ የቬዲክ ትእዛዞች ናቸው፡፡ ዓብዩ ዘለዓለማዊው ጌታ ሽሪ ክርሽና ነው፡፡ እኛም እንደ እርሱ ዘለዓለማዊ ነን፡፡ እኛ ከእርሱ ስር የምንገኝ እንጂ እንደ እርሱ ዓብይ አይደለንም፡፡ ”ኒትዮ ኒትያናም ቼታናስ ቼታናናም“ እርሱ የሁሉም ነዋሪ ዓብዩ ጌታ ሲሆን እኛ ደግሞ ከእርሱ ስር የምንገኝ ነን፡፡ ”ኤኮ ዮ ቪዳድሃቲ ካማን“ ይህም ማለት አንድ ነዋሪ ጌታ፣ አንድ ዘለዓለማዊ ጌታ ለመላ ነዋሪ ፍጥረታት ሁሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሲያቀርብ ይገኛል፡፡ ኤኮ ባሁናም ማለት በቁጥር ሊተመኑ የማይችሉ ነዋሪ ፍጥራታት ማለት ነው፡፡ ለመቁጠር በእርግጥ ያዳግታል፡፡ “ባሁናም” ይህ ነው የእኛም ዝምድና፡፡ ስለዚህ የዓብዩ ጌታ ወገን እንደመሆናችን ሽሪ ክርሽናን ማገልገል ይገባናል፡፡ ምክንያቱም በእርሱ ስር ስለምንገኝ ነው፡፡ የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ ሲያቀርብልን ይገኛል፡፡ ታላቁ አባታችንም እርሱው ነው፡፡ ይህ ዓይነቱም ኑሮ ትክክለኛ እና ነፃነት ያለው ሕይወት ነው፡፡ ከዚህም ከክርሽና ንቃት ውጪ የሆነ ሕይወት ሁሉ የሀጥያት ሕይወት ነው፡፡