AM/Prabhupada 0195 - በገላ ጥንካሬ ያለው፡፡ በሀሳብ ጥንካሬ ያለው፡፡ በውሳኔው ጥንካሬ ያለው፡፡
Lecture on SB 7.6.5 -- Toronto, June 21, 1976
ፕራጁምና፡ ትርጉም፡ “ሰለዚህም በቁሳዊው ዓለም ላይ በመኖር እያለ ”ብሀቫም አሽሪታሀ“ ደግ እና መጥፎውን ለይቶ ለማወቅ የሚችል አዋቂ ሰው ከፍተኛ የተባለውን የሕይወታችንን ዓላማ ለመምታት ጥረቱን ማድረግ የገባዋል፡፡ ይህም ገላችን ጠንካራ እና አቅም ያለው ከሆነ እና በእርጅና ያልተጠቃ ከሆነ ነው፡፡
ፕራብሁፓድ፡ ”ታቶ ያቴታ ኩሻላ ሴምያ ብሀቫም አሽሪታሀ ሻሪራም ፖሩሻም ያቫን ና ቪፓድዬታ ፑስካላም“ (ሽብ 7 6 5) የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ሁሉ እንደዚህ መሆን አለበት፡፡ ”ሻሪራም ፖሩሳም ያቫን ና ቪፓድዬታ ፑስካላም“ ጠንካራ እና ብቁ እስከኖንን ድረስ መስራት እንችላለን፡፡ ጤንነታችን ደህና እስከሆነ ድረስ ተጠቀሙበት፡፡ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ለሰነፍ ሰው አይደለም፡፡ መሆን ያለበትም ለጠንካራ ሰው ጠንካራ ገለ ያለው ጠንካራ ሀሳብ ያለው ወሳኝነቱ ጠንካራ የሆነ ሁሉም ነገሩ ጠንካራ የሆነ እና አእምሮውም ጠንካራ የሆነ ሰው ይፈለጋል፡፡ ይህም እንቅስቃሴ ለእንደዚህ አይነት ሰው ነው፡፡ ምክንያቱም ማንቀሳቀስ የሚገባን ከሁሉም በላይ የሆነውን አላማ ለመምታት ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን የሕይወታችን ከፍተኛው ዓላማ ምን እንደሆነ አያውቁም፡፡ በዚህ በሰለጠነው ግዜ ...... ሁል ግዜ የሰለጠኑ አይደሉም፡፡ አሁን በጣም ግልፅ ነው፡፡ ህዝቡ የሕይወታችን ዓላማ ምን እንደሆነ አያውቅም፡፡ በዚህ ቁሳዊ ምድር ላይ ያለ ሰው ሁሉ የለው በማያ (ምትሀት) ውስጥ ነው፡፡ ይህም ማለት የሕይወታችን ዓላማ ምን እንደሆነ ስለማያውቅ ነው፡፡ “ናቴ ቪዱህ” አያውቁትም “ስቫርታ ጋቲም ሂ ቪሽኑ” “ስቫርታ ጋቲ” ሁሉም ሰው ሰለ እርሱ ለማወቅ መፈለግ ይገባው ነበር፡፡ እራስን ለማወቅ ሊኖርብን የሚገባው ፍላጎት የመጀመሪያው የተፈጥሮ ሕግ ነው፡፡ ነገር ግን እራስን ማወቅ ምን እንደሆነ አልተረዱም፡፡ ይህም ያልተረዳ ሰው ወደ ቤት ወደ አብዩ አምላክ መኖርያ ከመሄድ ይልቅ (የግል ጥቅሙ) በሚቀጥለው ሕይወቱ ውሻ ሆኖ ሊወለድ ይችላል፡፡ ታድያ ይህ የግል ጥቅሙ ነውን? የፍጥረት ህግጋት እንዴት እንደሚሰሩ እውቀቱ የላቸውም። “ናቴ ቪድህ” “አዳንታ ጎብሂር ቪሻታም ታሚስራም ማቲር ና ክርሽኔ ፓራታሀ ስቫቶ ቫ” ማቲር ና ክርሽኔ ፓራታሀ ስቫቶ ቫ ሚትሆ ብሂፓድዬታ ግርሀ ቭራታናም አዳንታ ጎብሂር ቪሻታም ታኪስራም ፑናህ ፑናስ ቻርቪታ ቻርቫናናም (ሽብ፡7 5 30) ያም ክርሽና ንቃት ”ማቲር ና ክርስኔ“ ሰዎች ክርሽና ንቃትን ለመውሰድ ቅር ይላቸዋል፡፡ ለምን? "ማቲር ና ክርሽኔ ፓራታሀ ስቫቶ ቫ” በሌሎች ትእዛዝ ልክ እንደኛ የክርሽናን ንቃት ለመላው ዓለም ለማስፋፋት ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ ስቫቶ ስቫቶ ማለት በግል ማለት ነው፡፡ በግል ጥረት ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ ብሀገቨድ ጊታን ወይንም ሽሪማድ ብሀገቨታምን እና ሌሎች ቬዲክ መፃህፍቶችን አነባለሁ፡፡ ሰለዚህ “ማቴር ና ክርሽኔ ፓራታሀ ስቫቶ ቫ ሚትሆ ቫ ሚትሆ ቫ ማለት” በውይይ ማለት ነው፡፡ በአሁኑ ግዝ ኮንፈረንስ ለማድረግ በጣም የታወቀ ነገር ነው፡፡ ሰለዚህ አንድሰው በእራሱ ጥረት ብቻ የክርሽና ንቃት ሊኖረው አይችልም፡፡ ወይንም ከሌላ ሰው ምክር በመውሰድ ወይንም ታላላቅ ኮንፈረንሶችንም በመዘጋቸት ሊኖን ይችላል ለምን? “ግርሃ ቭራታናም” ምክንያቱም ትክክለኛው የኑሮው ዓላማ “በዚህ ቤት ውስጥ እቀመጣለሁ” ግርሀ ቭራታናም ግርሀ ማለት የመኖርያ ቤት ማለት ነው፡፡ ግርሀ ማለትም ደግሞ ይህ ገላችን ማለት ይቻላል፡፡ ግርሀ ማለትም ደግሞ የትእይንተ ዓለም ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ ግርሀዎች አሉ፡፡ ትልቅም ሆኑ ትናንሽ፡፡