AM/Prabhupada 1057 - "ብሀገቨድ ጊታ" ጊታ ኡፕኒሻድ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህም ከቬዲክ እውቀቶች ሁሉ መሰረታዊ ይዘት ያለው ነው፡፡

From Vanipedia


Bhagavad-gita is Known also as Gitopanisad, the Essence of Vedic Knowledge - Prabhupāda 1057


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

ፕራብሁፓድ፡ ለመንፈሳዊ አባቴ የክብር እጅ እነሳለሁ፡፡ በጨለመ ድንቁርና ውስጥ ተወልጄ እያለሁ የመንፈሳዊ አባቴ በእውቀት ፋና አይኖቼን ገለጠ፡፡ ያ ሽሪላ ሩፓ ጎስዋሚ ፕራብሁፓዳ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ የጌታ ቼይታንያን ምኞት ለሟሟላት እና ተልእኮውንም ለመፈፀም ያደራጀው መምህር መቼ ይሆን በሎተስ እፅዋት በመሰለ እግሩ ስር መጠለያውን የሚሰጠኝ? የሎተስ እፅዋት ለመሰለው ለመንፈሳዊው አባቴ እግር በጣም ዝቅ ብዬ የክብር እጅ እነሳለሁ፡፡ ለመላውም የቫይሽናቫዎች እግር በጣም ዝቅ ብዬ የክብር እጅ እነሳለሁ፡፡ ለመላ ቫይሽናቫዎች እና ለስድስቱ ጎስዋሚዎችም የክብር እጄን እነሳለሁ፡፡ ለሽሪላ ሩፓ ጎስዋሚ ለታላቅ ወንድሙ ሳናታን ጎስዋሚ ለራጉናት ዳስ ጎስዋሚ ለራጉናት ባታ ጎፓላ ባታ እና ለጂቫ ጎስዋሚ የሎተስ እፅዋት ለመሰለው እግራቸው በጣም ዝቅ ብዬ እጅ እነሳለሁ፡፡ ለጌታ ኒትያናንዳ ለአድቬይታ አቻርያ በጣም ዝቅ ብዬ የክብር እጅ እነሳለሁ፡፡ ለጌታ ክርሽና ቼይታንያ እና በሽሪቫስ ለሚመሩት ለሌሎች የቅርብ ባልደረቦቻቸው ሁሉ በጣም ዝቅ ብዬ የክብር እጅ እነሳለሁ፡፡ ከዚያም የሎተስ እፅዋት ለመሰለ ለጌታ ክርሽናም እግር የክብር እጄን እነሳለሁ፡፡ እንዲሁም ለሽሪማቲ ራድሀራኒ እና በላሊታ እና በቪሻካ ለሚመሩት ለመላ ጐፒዎች ሁሉ የክብር እጄን እነሳለሁ፡፡ የእኔ ውድ ክርሽና ሆይ አነተ ለተጨነቀው ሁሉ የቅርብ ጓደኛ እንዲሁም የፍጥረታት ሁሉ መነሻ ነህ፡፡ አንተ የጐፓዎቹ ሁሉ ጌታ የጐፒዎቹ እንዲሁም የራድሃራኒ አፍቃሪ ነህ፡፡ ለአንተ በጣም ዝቅ ብዬ የአክብሮት እጅ በመንሳት ለአንተ ያለኝን ፍቅር እገልፅልሀለሁ፡፡ የገላዋ ቅርጽ የቀለጠ ወርቅ ለመሰለው እና የቭርንዳቫን ንግስት ለሆነችው ራድሃራኒ ለጥ ብዬ የክብር እጅ እነሳለሁ፡፡ አንቺ የንጉስ ቭርሻቫኑ ልጅአገረድ ነሽ እንዲሁም ለሽሪ ክርሽና በጣም ውድ የሆንሽ ነሽ፡፡ ለጌታ የፍቅር አገልግሎታቸውን ለሚሰጡ ለመላው ቫይሽናቫዎች ሁሉ በጣም ዝቅ ብዬ የክብር እጅ እነሳለሁ፡፡ እነዚህም ቫይሽናቫዎች ልክ እንደ ምኞት ዛፍ የሁሉን ምኞት የሚያሟሉ እንዲሁም ለወደቁት ነፍሳት ሩህሩህነት የተሞላባቸው ናቸው፡፡ ለሽሪ ክርሽና ቼይታንያ ፕራብሁ ኒትያናንዳ በጣም ዝቅ ብዬ የክብር እጅ እነሳለሁ፡፡ ሽሪ አድቬይታ ጋዳድሃራ ሽሪቫሳ እንዲሁም ለተረፉት በጌታ የፍቅር አገልግሎት በተመሰጠ መስመር ለተሰማሩት ሁሉ በጣም ዝቅ ብዬ የክብር እጅ እነሳለሁ፡፡ የማፈቅርህ የመንፈዋዊ ሀይል የተሞላበት ጌታዬ ሆይ በፍቅር አገልግሎትህ እንድሰማራ በረከቱን ስጠኝ፡፡ እኔ በዚህ በዓለማዊ ኑሮ ህፍረት ተጠምጄ እገኛለሁ፡፡ እባክህ ፍቅር በተሞላበት አገልግሎትህ እንድሰማራ በረከቱን አውርድልኝ፡፡ በ ኤ ሲ ብሀክቲቬዳንታ ስዋሚ የቀረበ የጊታ ኡፕኒሻድ መግለጫ የሽሪማድ ብሀገቨታም የቀላል የፕላኔቶች ጉዞ ደራሲ እንዲሁም የ"ወደ አብዩ ሰማያት መመለስ" አታሚ፡፡ "ብሃገቨድ ጊታ" ጊታ ኡፕኒሻድ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህም ከቬዲክ እውቀቶች እና ስነጽሁፎች ሁሉ መሰረታዊ የሆነ እንዲሁም ከመላ ኡፓኒሻድ ስነፅሁፎች ሁሉ በጣም በአስፈላጊነት ደረጃ ላይ የሚገኝ የቬዲክ ሥነ ፅሁፍ ነው፡፡ በእርግጥም በአሁኑ ግዜ ብዙ የእንግሊዘኛ ብሃገቨድ ጊታ ሀተታ ወይንም ገለፃዎች ይገኛሉ፡፡ ስለዚህም አንድ ሰው ለምን ይህ ህትመት አስፈለገ ብሎ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ የዚህም የአሁኑ ህትመት አላማ በሚከተሉት ነጥቦች ተገልጿል፡፡ አንድ በቅርብ ግዜ ውስጥ አንዲት የአሜሪካዊት ሴት (ሚስስ ቻርሎት ለብላንክ) ወደ እንግሊዘኛ የተተረጐመ የትኛውን የብሃገቨድ ጊታ መፅሃፍ መውሰድ ወይንም ማንበብ እንዳለባት ሃሳቡን እንድሰጣት ጠይቃኝ ነበር፡፡ በእርግጥም በአሜሪካ ውስጥ በወቅቱ የሚገኙ ብዙ የብሃገቨድ ጊታ ህትመቶች ይገኙ ነበር፡፡ ነገር ግን እኔ እንዳየሁት ከሆነ በአሜሪካ ብቻ ሳይሆን በህንድ አገርም ጭምር ማንኛቸውም ህትመቶች በጥብቅ ዋናውን መልእክት የተከተለ ሥልጣናዊ ይዘት አላቸው ለማለት ያዳግታል፡፡ ምክንያቱም በብዙ ህትመቶች ውስጥ ፀሀፊያኑ የራሳቸውን አስተያየት እና እምነት ወይንም አመለካከት እየጨመሩ የብሃገቨድ ጊታን ጥልቅ መንፈስ እንደተዘመረው ሳይዳስሱ መዝግበውታል፡፡ የብሃገቨድ ጊታ ጥልቅ መንፈስ በእራሱ በብሃገቨድ ጊታ መዝሙር ውስጥ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ አንድ መድሀኒትን ለመውሰድ ብንፈልግ በመድሃኒቱ ወረቀት ላይ የተጻፈውን ትእዛዝ ወይንም መመሪያ መከተል ይገባናል፡፡ መድሃኒቱን መውሰድ ያለብን ለመድሃኒቱ የተፃፈውን ትእዛዝ ተከትለን ወይንም የሃኪሙን ትእዛዝ ተከትለን መሆን አለበት፡፡ መድሃኒቱን እንደ ፍላጎታችን መውሰድ ወይንም ከሀኪሙ የተለየ የጓደኛ ምክር ለመውሰድ አንችልም፡፡ መድሃኒቱን መውሰድ ያለብን ለመድሃኒቱ የተፃፈውን ትእዛዝ ተከትለን ወይንም የሃኪሙን ትእዛዝ ተከትለን መሆን አለበት፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ብሃገቨድ ጊታን መቀበል ወይንም መረዳት ያለብን ልክ የመልእክቱ ተናጋሪ እንደ አስቀመጠው ወይንም እንደገለፀው መሆን አለበት፡፡