AM/Prabhupada 1058 - የብሃገቨድ ጊታ መልእክት የመነጨው ከጌታ ሽሪ ክርሽና ነው፡፡

From Vanipedia


The Speaker of the Bhagavad-gita is Lord Sri Krishna - Prabhupāda 1058


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

ክርሽና ብቻ ሳይሆን በመላ ታላላቅ አቻርያዎችም (ተግባራዊ መንፈሳዊ አባቶች) ጭምር ነው፡፡ እነዚህም መንፈሳዊ መምህራን እንደ ሻንካራ አቻርያ ራማኑጃ አቻርያ ማድሀቫ አቻርያ ኒምባርካ ስዋሚ ሽሪ ቼይታንያ መሀፕራብሁ እና ሌሎች ብዙሀን የህንድ አገር የቬዲክ እውቀት ባለቤት የሆኑ አባቶች ናቸው፡፡ በህንድ አገር ውስጥ በርካታ ስልጣን ያላቸው መምህራን እና አቻርያዎች ይገኙ ነበረ፡፡ ይህም ማለት የቬዲክ እውቀት ባለስልጣኖች ማለት ነው፡፡ እነዚህም ሁሉ እንደ ሳንካራ አቻርያ የመሳሰሉት ሁሉ ሽሪ ክርሽናን አብዩ የመላእክት ጌታ እንደመሆኑ ተቀብለው ሲያስተምሩ የቆዩ ናቸው፡፡ ጌታ ክርሽናም ቢሆን የራሱን አብይ ፈጣሪ አምላክነቱን ማዕረግ በብሃገቨድ ጊታ ውስጥ ገልጾታል፡፡ ይህም የአምላክነት ማዕረጉ በተለያዪ ታላላቅ መንፈሳዊ ሥነፅሁፎች ተገልፀዋል፡፡ እነዚህም ሥነ ፅሁፎች እንደ ብራህማ ሰሚታ መላ ፑራናዎች በተለይ ብሀገቨት ፑራን ተብሎ የሚታወቀው ሽሪማድ ብሀገቨታም (ክርሽና ቱ ብሀገቫን ስዋያም) የመሳሰሉትን እና ሌሎችንም ይጨምራል፡፡ (ሽብ 1 3 28) ስለዚህም ብሀገቨድ ጊታን መቀበል ወይንም መረዳት ያለብን ምንም አይነት የግል አስተያየት ባለመስጠት ልክ ጌታ ክርሽና እንዳስቀመጠው እንደዘመረው ወይንም እንደተናገረው መሆን አለበት፡፡ በብሀገቨድ ጊታ በአራተኛው ምዕራፍ ላይ ጌታ ክርሽና እንዲህ ብሎ ገልጿል፡፡ ኢማም ቪቫስቫቴ ዮጋም ፕሮክታቫን አሀም አቭያያም ቪቫስቫን ማናቬ ፕራሀ ማኑር ኢክስቫካቬ ብራቪት (ብጊ፡ 4 1) ኤቫም ፓራምፓራ ፕራፕታም ኢማም ራጃርሻዮ ቪዱህ ሳ ከሌኔሀ ማሃታ ዮጎ ናስታህ ፓራንታፓ (ብጊ፡4 2) ሳ ኤቫያም ማያ ቴ ድያ ዮጋህ ፕሮክታህ ፑራታናህ ብሀክቶ ሲሜ ሳክሃ ቼቲ ራሃስያም ሂ ኤታድ ኡታማም (ብጊ፡4 3) በዚህም ምዕራፍ ጌታ ክርሽና ለአርጁና እንዲህ ብሎ ይገልፅለታል፡፡ “ይህ የዮጋ ስርአት ወይንም ብሀገቨድ ጊታ ለመጀመሪያ ግዜ በእኔ የተገለፀው ለታላቁ የፀሃይ ጌታ ቪቫሽቫን ነው፡፡ የፀሀይ ጌታም ለማኑ ገለፀለት ማኑ ደግሞ ለኢክስቫኩ ገለፀለት፡፡ በዚህም ሲወርድ ሲዋረድ በቀጠለ የድቁና ስርአት ይህ የዮጋ መልእክት ለብዙ ትውልድ ሲተላለፍ ቆየ፡፡ ቢሆንም ግን ከብዙ ዘመን በኋላ ይህ መንፈሳዊ እውቀት ሊጠፋ ችሏል”፡፡ "በዚህም አጋጣሚ እኔ (ጌታ ክርሽና) ይህንን መልእክት እንደገና ለመናገር በቅቻለሁ፡፡" ይህም ቀድሞ ተገልጾ የነበረው የዮጋ ስርዓት ብሀገቨድ ጊታ ወይንም ጊቶ ኡፓኒሻድ ተብሎ የታወቀውን ነው፡፡ ለአንተ የገለፅኩልህም (አርጁና) አንተ ትሁት አገልጋዬ እና የቅርብ ጓደኛዬ በመሆንህ ነው፡፡ ሰለዚህም አንተ ይህንን ስርዓት በትክክል ልትረዳው ትችላለህ፡፡ የዚህም ገለፃ ፍቺ የብሀገቨድ ጊታ የነጠረ እና ትኩረት ያለው መልእክት የተዘጋጀው ለጌታ ክርሽና ትሁት አገልጋዮች ነው፡፡ ላይ ሶስት አይነት በመንፈሳዊ አቅዋም የላቁ ሀይማነተኞች ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ግያኒ ዮጊ እና ብሃክታ ተብለው ይታወቃሉ፡፡ እነዚህም ሶስቱ አምላክን እንደ ሀይል እንጂ እንደ አብይ ሰው አነጣጥረው ለማየት የሚያዳግታቸው (ኢምፐርሰናሊስትስ) በልበ አምላክ ጥልቅ ሀሳብ የሚያተኩሩ (ሜዲቴተርስ) እና የአምላክ ትሁት አገልጋዮች (ብሃክታ) ተብለው ይታወቃሉ፡፡ በዚህም ውይይት ላይ ጌታ ክርሽና ለአርጁና ሲገልፅለት ይታያል፡፡ በዚህም ውይይት ላይ ጌታ ክርሽና ለአርጁና ሲገልፅለት የመጀመሪያው የትምህርቱ ተቀባይ ወይንም ፓራምፓራ እርሱ እንደሆነ ገልጾለታል፡፡ የዚህም ምክንያት የጥንቱ የድቁና ስርአት ሰለተቋረጠ ነው፡፡ ስለዚህም የጌታ ክርሽና ምኞት አዲስ ሲወርድ ሲዋረድ ሊቀጥል የሚችል (ፓራምፓራ) የድቁና ስርአት ለመመስረት ነበረ፡፡ ይህንንም ስርአት ልክ በፀሀይ ጌታ ተጀምሮ ለዘመናት ቀጥሎ እንደነበረው የትምህርት ይዘት እንዲቀጥል ምኞቱ ነበር፡፡ ይህም ትምህርት አሁን በአርጁና እንደ አዲስ ተጀምሮ እንዲቀጥል ፈለገ፡፡ ይህም የብሀገቨድ ጊታ ስርዓት በአርጁና በኩል እንደገና ለመላ ዓለም እንዲስፋፋ ምኞቱ ነበረ፡፡ አርጁናም ብሀገቨድ ጊታን በደንብ አድርጐ የተረዳ የባለስልጣን ተማሪ እንዲሆንለት ፈልጐ ነበር፡፡ እዚህም እንደምንረዳው ብሀገቨድ ጊታ ለአርጁና በቀጥታ እንደተገለፀለት ነው፡፡ ይህም አርጁና የጌታ ክርሽና ትሁት አገልጋይ እና በቀጥታ የሚገኝ ተማሪው በመሆኑ ነው፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ከሽሪ ክርሽና ጋር በጣም ቅርበት ያለው እና የቅርብ ጓደኛውም በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም ብሀገቨድ ጊታ ሊገለፅልን የሚችለው አንደበታችን ልክ ሽሪ ክርሽና እንደአለው ባህርይ ሲኖረን ብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት አንድ ሰው የጌታ ክርሽና ትሁት አገልጋይ ሆኖ በቀጥታ እና በጥሩ ልቦና የሚያገለግል ከሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት አገልጋዩ ከአብዩ ጌታ ጋር የቀጥታ ግኑኝነት ያለው ከሆነ ነው፡፡