AM/Prabhupada 1079 - ብሀገቨድ ጊታ በጥሞና እና በጥንቃቄ መነበብ ያለበት መንፈሳዊ ቅዱስ መፅሀፍ ነው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search
Go-previous.png የቀድሞው ገፅ - ቪድዮ 1078
የሚቀጥለው ገፅ - ቪዲዮ 1080 Go-next.png

ብሀገቨድ ጊታ በጥሞና እና በጥንቃቄ መነበብ ያለበት መንፈሳዊ ቅዱስ መፅሀፍ ነው፡፡
- Prabhupāda 1079


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

ይህንንም ብሀገቨድ ጊታ ወይንም የሽሪማድ ብሀገቨታም ቅዱስ መፃህፍት በመንፈሳዊ ግንዛቤ ከተረዳ ሰው ማዳመጥ አንድ ሰው ዓብዩ ጌታን ለ24 ሰዓት ለማስታወስ እንዲችል ልምዱን ይሰጠዋል፡፡ ይህም ወደ "አንታ ካሌ" ወይንም ዓብዩ ጌታን ሁሌ እንዲያስታውስ ይረዳዋል፡፡ ከዚም በኋላ በሞት አፋፍ ላይ ሲሆን የመንፈሳዊ ሕይወትን ለማግኘት ይችላል፡፡ ይህም የመንፈሳዊ ሕይወት ከዓብዩ ጌታ ጋር እንዲሆን ያበቃዋል፡፡ ስለዚህም ዓብዩ ጌታ እንዲህ ብሏል "አብሂያስያ ዮጋ ዩክቴና ቼታሳ ናንያ ጋሚና" "ፓራማም ፑሩሻም ዲቭያም ያቲ ፓርትሀኑቺታያን" (ብጊ፡ 8 8) "አኑቺንታያን" ዓብዩ ጌታን ሁሌ ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም አስቸጋሪ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ይህንንም መማር ያለበት ልምዱ ካለው መንፈሳዊ አገልጋይ ነው፡፡ "ታድ ቪግያናርትሀም ሳ ጉሩም ኤቫብሂጋቼት" (ሙኡ፡ 1 2 12) አንድ ሰው መቅረብ ያለበት የመንፈሳዊ አገልግሎት ልምድ ያለውን የዓብዩ ጌታ አገልጋይን ነው፡፡ ይህም "አብህያሳ ዮጎ ዩክቴና" ይህም "አብህያሳ ዮጋ" ይባላል፡፡ "አብህያስያ" ዓብዩ ጌታን እንዴት አድርገን ለማስታወስ እንደምንችል፡፡ "ቼታስ ናንያ ጋሚና" ሀሳባችን ሁልግዜ ወዲህ እና ወዲያ እንደተሯሯጠ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ሀሳባችን እንዴት አድርገን በመቆጣጠር የዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ፎርም ላይ እንዴት እንደምናተኩር መግራት ያስፈልገናል፡፡ ወይንም ድምፅን በመጠቀም፣ ስሙን በማስታወስ በቀላሉ ለማስታወስ መጣር ይኖርብናል፡፡ ሀሳባችን እረፍት የለውም፡፡ ወዲህ እና ወዲያ በየሴኮንዱ ሲመላለስ ይገኛል፡፡ አንድ ቦታ ላይ ለማተኮርም ያዳግተዋል፡፡ ቢሆንም ግን ጆሮአችንን ወደ ሽሪ ክርሽና ድምፅ ላይ በማሰማራት ሀሳባችንን ለመግራት እንችላለን፡፡ ይህም "አብይያሳ ዮጋ“ ይባላል፡፡ ”ቼታሳ ናንያ ጋሚና ፓራማም ፑሩሳም ዲቭያም“ ”ፓራማም ፑሩሻ“ በመንፈሳዊው ዓለም የሚገኘው ዓብዩ የመላእክት ጌታ በመንፈሳዊው ዓለም ”አኑቺንታያን“ መቅረብ ይችላል፡፡ ይህም በተደጋጋሚ ዓብዩ ጌታን ማስታወስ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ዓብዩ ጌታን የማስታወስ ስርዓቶች ሁሉ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልፀውልናል፡፡ እነዚህም ስርዓቶች ለማንም ሰው የታገዱ አይደሉም፡፡ እነዚህም ስርዓቶች የቀረቡት ለተወሰነ ሕብረተሰብ ብቻ ዓይደለም፡፡ ሽሪ ክርሽናን ማስታወስ በማንም ሰው ነው፡፡ ስለ ሽሪ ክርሽናም ማዳመጥ በማንም ሰው የሚቻል ነው፡፡ ዓብዩ ጌታም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ እንዲህ ብሏል፡፡ ”ማም ሂ ፓርትሀ ቭያፓሽሪትያ ዬ ፒ ስዩህ ፓፓ ዮናያህ“ ”ስትሪዮ ቫይሽያስ ታትሀ ሹድራስ ቴ ፒ ያንቲ ፓራም ጋቲም“ (ብጊ፡ 9 32) ”ኪም ፑናህ ብራህማናሀ ፑንያ ብሀክታ ራጃርሳያስ ታትሀ“ ”አኒትያም አሱክሀም ሎካም ኢማም ፓራፕያ ብሀጃስቫ ማም“ (ብጊ፡9 33) ዓብዩ ጌታ እንደገለፀው ከሕብረተቡ መሀከል በዝቅተኛ ደረጃ እንኳን የሚገኘው ሰው ይህም ከተከበረ ቦታ የወደቀች ሴት፣ ነጋዴ፣ የቀን ሰራተኛ ማለትም የነጋዴው ህብረተሰብ፣ የቀን ሰራተኞች ወይንም የሴቶች ሕብረተሰብ የመንፈሳዊው አእምሮዋቸው ብዙውን ግዜ የዳበረ ባለመሆኑ በአንድ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ቢሆንም ግን ዓብዩ ጌታ እንደገለፀው እነሱም ሆኑ ከእነሱ በታችም የሚገኙ መንፈሳቸው ዝቅ ያለ ሰዎች ”ማም ሂ ፓርትሀ ቭያፓሽሪትያ ዬ ፒ ስዩህ" (ብጊ፡ 9 32) እነዚህም ሆኑ ከእነርሱ በታችም መንፈሳቸው ዝቅ ያለ ሰዎች ሁሉ ማንም ሰው ቢሆን የዓብዩ ጌታን የትሁት አገልግሎት ወይንም ብሀክቲ ዮጋን መለማመድ ይችላል፡፡ ይህም ለማናቸውም ሰው የተሰጠ እድል ነው፡፡ በዚህም ስርዓት ዓብዩ ጌታን የሕይዋታችን ሁሉ መድረሻ ማድረግ ይገባናል፡፡ ከፍተኛው መድረሻችን ወይንም ከፍተኛው ጐላችን መሆን ይገባዋል፡፡ “ማም ሂ ፓርትሀ ቭያፓሽሪትያ ዬ ፒ ስዩህ ቴ ፒ ያንቲ ፓራም” ይህም “ፓራም ጋቲም” ወይንም ታላቁ መድረሻችን የመንፈሳዊው ቤተ መንግስት በመንፈሳዊው ሰማይ ውስጥ የሚገኘው ነው። ይህንንም መድረሻ ማናቸውም ትሁት ሰው ሊቀርበው ይችላል፡፡ ማድረግ የሚገባውም ስርዓቱን መከተል ብቻ ነው፡፡ ይህም ስርዓት በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ በጥሩ መንገድ ተገልፆልናል፡፡ ይህንንም ስርዓት በመከተል አንድ ሰው ሕይወቱን ፍፁም በሆነ መንገድ የተሳካ ለማድረግ በመቻል ለሕይወቱ ዘለዓለማዊ መፍትሄ ለማግኘት ይችላል፡፡ የብሀገቨድ ጊታም የነጠረው ማብራርያ ይኅው ነው፡፡ ስለዚህ መደምደሚያው ብሀገቨድ ጊታ በጣም ጠቃሚ የመንፈሳዊ መፅሀፍ መሆኑን ተረድተን በጥንቃቄ ማንበብ እና መረዳት ይኖርብናል፡፡ “ጊታ ሻስትራም ኢዳም ፑንያም ያህ ፓትሄት ፓራያትሀ ፑማን” አንድ ሰው ይህንንም ስርዓት በትክክል የሚከተል ከሆነ ውጤቱ በሕይወት ልናይ ከምንችለው መከራዎች ሁሉ ነፃ እንወጣለን፡፡ ከሕይወትም ጭንቀት ሁሉ ነፃ እንወጣለን፡፡ “ብሀያ ሾካዲ ቫርጂታሀ” (ጊታ ማሃትምያ 1) በዚህ ሕይወታችን ከፍርሀት ነፃ መሆን ብቻ ሳይሆን በሚቀጥለው ሕይወታችንም መንፈሳዊ ሕይወት እናገኛለን፡፡ “ጊታድህያና ሺላስያ ፕራናያማ ፓራስያ ቻ ናይይቫ ሳንቲ ሂ ፓፓኒ ፑርቫ ጃንማ ክርታኒ ቻ” (ጊታ ማሃትምያ፡ 2) የብሀገቨድ ጊታን በጥሞና ማንበብ ሌላው ጥቅሙ ይህም በትሁትነት እና ጥልቅ በሆነ መንገድ የሚያነብ ሰው በዓብዩ ጌታ ቸርነት ከዚህ በፊት ካደረጋቸው ሀጥያቶች ሁሉ ነፃ በመውጣት የሀጥያቱን ፍሬ ለመቅመስ አይጋለጥም፡፡